ለጀማሪ የቢዝነስ መስራቾች ስልጠና

ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ እንደ ጀማሪ መስራች ለዘላቂ የንግድ ስራ እድገት ወሳኝ የሆኑ ክህሎቶችን ያስተምርዎታል፡፡ ግልጽ ግቦችን ስለመወሰን፣ ጊዜዎን ውጤታማ በሆነ መልኩ ስለመጠቀም እና ከፍተኛ ውጤት ለሚያስገኙ ስራዎች ቅድሚያ ስለመስጠት ይማራሉ፡፡ ዝግጁነትዎን ያጎለብታሉ፣ የእድገት አስተሳብ ይላበሳሉ እንዲሁም እርግጠኝነት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ በመረጃ የተደፉ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ፡፡ ቡድኖችን ለመምራት እና የድጋፍ ሥርዓትዎን ለማስፋት ግንኙነት፣ ትስስር እና ክህሎቶች ምደባ ያዘጋጃሉ፡፡ ችግሮችን በፈጠራ ለመፍታት የግጭት አፈታት እና የችግር አፈታት ችሎታዎችን ያገኛሉ፡፡ በመጨረሻም የማህበረሰብ ችግሮችን በመፍታት የአካባቢ ዘላቂነትን፣ የጤና መሻሻልን እና የጾታ አቅም መጎልበትን የሚያሳድግ ደንበኛን ያማከለ፣ ዝግጁ የንግድ ስራ የሚያዘጋጁባቸው ስትራቴጂዎችን ያውቃሉ፡፡ በኦንላይን የራስ ማስተማሪያ አማካኝነት በንጹህ ማብሰያ ዘርፉ ውስጥ ዘላቂ ውጤት ለማምጣት የሚያስችሉ የተግባር መሳሪያዎችን ያገኛሉ፡፡

Scroll to Top