የትምህርቱ ዓላማ
በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች በንፁህ ማብሰያ ዘርፍ ላይ የንግድ ሥራ ሃሳቦቻቸውን ስልታዊ በሆነ መንገድ ለመቅረፅ ዘጠኙን የመነሻ ነጥቦች በመጠቀም የመጀመሪያውን የመጀመሪያውን የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቃቸውን ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡
ተሳታፊዎች እንዴት ዋና ዋና የደንበኛ ችግሮችን እንደሚለዩ፣ እንዴት ትኩረት የሚደረግባቸው የደንበኛ ምድቦችን እንደሚገልጹ፣ እንዴት ልዩ የዕሴት እቅድን እንደሚገልጹ፣ እንዴት የገቢ ማግኛ መስመሮችን እንደሚዘረዝሩ፣ እና እንዴት የወጪ መዋቅሮችን እንደሚገመግሙ ያውቃሉ፡፡
ይህ የተግባር ትምህርት አዳዲስ የስራ ፈጣሪዎችን እሳቤዎቻቸውን የሚያረጋግጡበት፣ በተጨባጭ የገበያ ፍላጎቶች ላይ የሚያተኩሩበት እና ለውጤታማ የሀብት ምደባ ቅድሚያ የሚሰጡበት ተግባራዊ ማዕቀፍን በማሳወቅ የንግድ ሥራ ሀሳቦቻቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ማህበረሰቦችን ተጨባጭ ተግዳሮቶች/ ችግሮች በመፍታት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ያስችላቸዋል፡፡