የመስፍን ወደ ደንበኛን ያማከለ ስኬት ጉዞ
የ23 ዓመት ወጣት የአዲስ አበባ ነዋሪ ስራ ፈጣሪ የሆነው መስፍን ሁልጊዜም የእውነተኛውን ዓለም ችግሮች የመፍታት ህል አለው፡፡ ሰው በሚበዛበት የከተማ መንደር ውስጥ ያደገው መስፍን ብዙ ቤተሰቦች በተለይም ሀይል በሚቋረጥበት ወይም የጋዝ ሲሊንደሮች ጋዝ በሚጨርሱበት ወቅት ምግብ የማብሰል ችግሮች እንደሚያጋጥማቸው ተመልክቷል፡፡ በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ በመነሳሳት መስፍን በልዩ ሁኔታ ለከተማ ነዋሪዎች የሚዘጋጁ በዋጋ ተመጣጣኝ፣ ለአያያዝ ቀላል የሆኑ የኤለሌክትሪክ የምግብ ማብሰያዎችን የሚያቀርብ የንግድ ስራ ለመጀመር ይወስናል፡፡
ደረጃ 1: የትኩረት ደንበኞቹን መለየት
መስፍን ወደ ምርት ዝግጅቱ ከማለፉ በፊት እጩ ደንበኞቹን በጥልቀት መረዳት እንዳለበት ያውቃል፡፡ ትኩረት የሚያደርግባቸውን ደንበኞች በሥነ ህዝብ፣ በባህሪና ፍላጎቶች መመደብ ይጀምራል፡
- የከተማ ነዋሪዎች: ውሱን ቦታ ባላቸው አፓርታማዎች ውስጥ የሚኖሩ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች፡፡
- ስነ ሕዝብ: ወጣት ባለሙያዎች፣ አነስተኛ ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፡፡
- ባህሪ: ዘመናዊ፣ ቦታ የማይፈጁ የምግብ ማብሰያዎችን ይመርጣሉ፤ በእጅጉ በኤሌክትሪክ ላይ ጥገኛ ናቸው፡፡
- ልዩ ፍላጎቶች: ምቹነት፣ ሀይል ቆጣቢነትና ስታይል ያላቸው ዲዛይኖች፡፡
- በሴት እማወራ የሚመሩ ቤተሰቦች፡ ከፍተኛ ጊዜያቸውን ለቤተሰቦቻቸው ምግብ ለማብሰል የሚያውሉ ሴቶች፡፡
- ሥነ ህዝብ: የቤት ውስጥ ስራዎችን የሚሰሩ እናቶች፡፡
- ባህሪ: በየዕለቱ የተለያዩ ምግቦችን ያበስላሉ፣ ከባህላዊ ምድጃዎች ለሚወጣ ጭስ ይጋለጣሉ፡፡
- ልዩ ፍላጎቶች: ጊዜ ቆጣቢ ባህሪያት፣ እና ለመጠቀም ቀላልነት፡፡
- አረጋውያን ተጠቃሚዎች፡ ለቀላልነትና ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጡ በእድሜ የገፉ አዋቂ ሰዎች፡፡
- ሥነ ሕዝብ: ለብቻቸው ወይም ከትዳር አጋራቸው ጋር የሚኖሩ ጡረታ የወጡ ግለሰቦች፡፡
- ባህሪ: ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን አይፈልጉም፣ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ዋጋ ይሰጣሉ፡፡
- ልዩ ፍላጎቶች: ቀላል ቁጥጥሮች፣ ጠንካራ አሰራርና አነስተኛ ጥገና፡፡
ደረጃ 2: ልዩ ችግሮችን መረዳት
መስፍን እያንዳንዱን ምድብ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለማረጋገጥ በመላው አዲስ አበባ ለ50 ቤተሰቦች ቃለ መጠይቆችን እና የዳሰሳ ጥናቶችን ያካሂዳል፡
- የከተማ ነዋሪዎች በጣም ብዙ ቦታ በሚወስዱ ትላልቅ እና ውጤታማ ባልሆኑ ምድጃዎች ተሰላችተዋል፡፡
- በሴት እማወራ የሚመሩ ቤተሰቦች የቤት ውስጥ አየር መበከል እና ምግብ ለማብሰል የሚወስድባቸውን ጊዜ ችግሮች ገልጸዋል፡፡
- አረጋውያን ተጠቃሚዎች ዘመናዊ የምግብ ማብሰያዎች ግራ አጋቢ ስለሆኑባቸው ቀጥተኛ ዲዛይኖችን ይፈልጋሉ፡፡
ደረጃ 3: መፍትሄዎች ማዘጋጀት
እነዚህን ግንዛቤዎች በማግኘት መስፍን የእያንዳንዱን ቡድን ልዩ ፍላጎቶች የሚያሟሉ ሶስት የተለያዩ ለአያያዝ ቀላል የሆኑ የኤሌክትሪክ የምግብ ማብሰያዎችን ያዘጋጃል፡
- ለከተማ ነዋሪዎች፡ እንደ የሙቀት መቆጣጠሪያ እና አውቶማቲክ መዝጊያ ያሉ የተሻሻሉ ባህሪያት ያሉት ቀጭን፣ ቦታ የማይፈጅ ሞዴል፡፡ ምርቱ ለዘመናዊ አኗኗር እንደ “ስማርት የማድ ቤት ፍላጎት” ይሸጣል፡፡
- በሴት እማወራ ለሚመሩ ቤተሰቦች፡ ፈጣን የማብሰያ ዝግጅቶች እና ከጭስ ነጻ የሆነ ቴክኖሎጂ ያሉት ለተጠቃሚ ተስማሚ ሞዴል፡፡ መስፍን በተጨማሪም ሴቶችን ስለ ምርጡ የጤናና የጊዜ ቆጣቢነት ጥቅሞች ለማስተማር ነጻ የስልጠና ክፍለ ጊዜዎችን አካቷል፡፡
- ለአረጋውያን ተጠቃሚዎች፡ ትላልቅ በተኖችና ግልጽ ጠቋሚዎች ያሉት እና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል ተደርጎ የተሰራ ቀላል ሞዴል፡፡ ምርቱ ለመረፋት ቀላል ከሆነ ዝርዝር የአማርኛ መመሪያ ጋር እንደተዘጋጀ ያረጋግጣል፡፡
ደረጃ 4: ሙከራ እና ግብረ መልስ
መፍትሄዎቹ ለደንበኞች ተስማሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ መስፍን ከእያንዳንዱ ምድብ በ10 ቤተሰቦች ላይ የመጀመሪያ ሙከራዎችን አካሂዷል፡፡ የተደራጀ የዳሰሳ ጥናትን በመጠቀም ግብረ መልስ ከመሰብሰቡም በተጨማሪ በእነዚህ ጥቆማዎች ላይ ተመስርቶ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡
- የከተማ ነዋሪዎች ከማድ ቤት ማስዋቢያቸው ጋር ለማስማማት ተጨማሪ የከለር አማራጮችን ጠይቀውታል፡፡
- በሴት እማወራ የሚመሩ ቤተሰቦች ስልጠናውን ያደነቁለት ቢሆንም ቀጣይነት ላለው ድጋፍ መመሪያ ሰጪ ቪዲዮዎችን እንዲያካትት ጥቆማዎችን ሰጥተውታል፡፡
- አረጋውያን ተጠቃሚዎች ቀላልነቱን የወደዱት ቢሆንም በቀላሉ ለመያዝ እጄታ እንዲገጥምለት ጠይቀውታል፡፡
ደረጃ 5: መጀመር እና ማሳደግ
መስፍን ምርቶቹን ካጠራ በኋላ የንግድ ስራውን ስማርት ኩክ በሚል ስም ጀምሯል፡፡ ትኩረት ያደረገባቸውን ደንበኞች ለመድረስ ከአካባቢ የምግብ ማብሰያ መደብሮች እና የኦንላይን ፕላትፎርሞች ጋር በትብብር እየሰራ ነው፡፡ ተደራሽነቱን በተጨማሪ ለማሻሻል አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች በጊዜ የተከፋፈሉ የክፍያ እቅዶችን ለማቅረብ ከማይክሮፋይናንስ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ነው፡፡
በስድስት ወራት ውስጥ መስፍን ከ300 በላይ ምድጃዎችን በመሸጥ ከደንበኞች ብሩህ ግምገማዎችን አግኝቷል፡፡ ደንበናን ያማከለ አቀራረቡ የተቀባይነት ደረጃዎችን ማሳደግን ብቻ ሳይሆን ትኩረት ባደረገባቸው ደንበኞች ዘንድ እምነትና ታማኝነትን እንዲገነባ አስችሎታል፡፡
ከመስፍን ታሪክ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች
- የደንበኛ ምደባ፡ የተለያዩ የደንበኛ ቡድኖችን በመግለጽ እና በመረዳት መስፍን መፍትሄዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ አዘጋጅቷል፡፡
- ፍላጎቶችን መሰረት ያደረገ ዝግጅት፡ የእያንዳንዱን ምድብ ልዩ ችግሮች በመፍታት ምርቶቹ አግባብነት ያላቸው እና ውጤት አምጪ እንደሆኑ አረጋግጧል፡፡
- ተደጋጋሚ ግብረ መልስ: ቀጣይነት ባለው መልኩ የደንበኛ ግብረ መልስ መሰብሰቡ እና እርምጃ መውሰዱ አቅርቦቶቹን እንዲያጠራና የደንበኛ እርካታን እንዲያሻሽል ረድቶታል፡፡
- ትብብሮች: መስፍን ከአካባቢ ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራቱ ትኩረት ላደረገባቸው ደንበኞች ተደራሽነቱን እና የዋጋ ተመጣጣኝነቱን አሻሽሎለታል፡፡
በአሁኑ ወቅት የመስፍን የንግድ ስራ እያደገ ከመሆኑም በተጨማሪ የምርት መስመሩን በማስፋፋት ለገጠር ቤተሰቦች በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ ማብሰያዎችን ለማካተት አቅዷል፡፡ “የደንበኞቼን ፍላጎቶች መረዳቴ ለስኬቴ ዋነኛው ምክንያት ነው” የሚለው መስፍን“ ደንበኞችን ስናዳምጥ ወደ ትክክለኛው መፍትሄ ይመሩናል“ በማለት ይግልጻል፡፡