የ22 ዓመት ወጣቷ የአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ነዋሪ የኮሌጅ ተማሪ ሶፊያ በአካባቢ ጥበቃ ላይ ሁልጊም ፍላጎት አላት፡፡ እንደ የመጨረሻ ዓመት ፕሮጀክቷ አንድ ክፍል የከተማ ቤተሰቦችን የሚያጋጥሟቸውን እንደ ከፍተኛ የነዳጅ ወጪዎች እና የቤት ውስጥ አየር መበከል ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የፈጠራ ለአያያዝ ቀላል የሶላር የምግብ ማብሰያ ታዘጋጃለች፡፡ በጥናቷ በመነሳሳት ሶፊያ ሀሳቧን ወደ ንግድ ስራ ለመቀየር ትወስናለች፡፡ ሆኖም ብዙም ሳትቆይ የገቢ ማግኛ መንገዶችን መለየትና ወጪዎችን ማስተዳደር የንግድ ስራዋን የገንዘብ ዘላቂነት ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ ትገነዘባለች፡፡
ለመጀመር ሶፊያ ሊሳኩ የሚችሉ የገቢ ምንጮችን ለማጥናት የገቢ ማግኛ መንገዶችን መለያ ቴምፕሌትን ትጠቀማለች፡፡ ሶስት ዋና ዋና የገቢ ማግኛ መንገዶችን ትለያለች፡
- ቀጥተኛ ሽያጮች፡ የሶላር የምግብ ማብሰያዎቹን በአካባቢ ገበያዎችና የኦንላይን ፕላትፎርሞች በኩል በቀጥታ ለከተማ ቤተሰቦች መሸጥ፡፡
- ትብብሮች: ምርቷን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ አነስተኛ ገተቢ ላላቸው ቤተሰቦች ድጎማ ለማድረግ ከአካባቢ ኤንጂኦ ጋር በትብብር መስራት፡፡
- የአገልግሎት ክፍያዎች፡ ማብሰያዎቹን እንዴት ውጤታማ በሆነ መንገድ እንደሚጠቀሙ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ወይም ስልጠና ለሚፈልጉ ደንበኞች አማራጭ የጥገና መርሀግብሮችን ማቅረብ፡፡
ቀጥላም ሶፊያ የወጪ መዋቅር ትንተና ቴምፕሌትን በመጠቀም ወጪዎቿን ትተነትናለች፡፡ ወጪዎቿን በቋሚ እና ተለዋዋጭ ወጪዎች ትመድባለች፡
- ቋሚ ወጪዎች: የአነስተኛ ቤተ ሙከራ ኪራይ፣ የኦንላይን ሽያጮች ወርሀዊ የኢንተርኔት ወጪዎች እና መሰረታዊ መሳሪያ መግጠሚያ ወጪ (ብር 200 በወር)፡፡
- ለዋዋጭ ወጪዎች፡ እንደ የሶላር ፓኔሎችና ካስቲንግ፣ ማሸጊያ እና አቅርቦት ያሉ የጥሬ እቃዎች ወጪዎች (ብር 30 በምርት)፡፡
- የመጀመሪያ ኢንቨስትመንት፡ የመጀመሪያ ሙከራ፣ የማረጋገጫ ክፍያዎች እና የመጀመሪያ ንብረት ማምረቻ (ብር 1,000 የአንድ ጊዜ ወጪ)፡፡
ሶፊያ ትርፋማነቷን ለማረጋገጥ የገቢ ማግኛ ነጥብ ትንተና ቴምፕሌትን በመጠቀም የገቢ ማግኛ ነጥቧን ታሰላለች፡፡ በአንድ ምርት የመሸጫ ዋጋ ብር 50 እና ተለዋዋጭ ወጪዎች ብር 30 ቋሚ ወጪዎቿን ብር 200 ለመሸፈን እና ትርፍ ማግኘት ለመጀመር በወር ቢያንስ 40 ምርቶችን መሸጥ እንዳለባት ትወስናለች፡፡ ትንተናው ተጨባጭ የሽያጭ ኢላማዎችና የገበያ ስትራቴጂ እቅዷን ውጤታማ በሆነ መልኩ እንድታዘጋጅ ይረዳታል፡፡
ሶፊያ ተደራሽቷን ለማስፋትና ወጪዎቿን ለመቀነስ የምታደርጋቸውን ትብብሮች ታጠናለች፡፡ የትብብር ዕድል ማወቂያ ቴምፕሌትን በመጠቀም ደንበኞችን በተከፋፈሉ ክፍያዎች የሶላርየምግብ ማብሰያዎቿን መግዛት እንዲችሉ ለደንበኞች የገንዘብ ድጋፍ አማራጮችን ለማቅረብ ፍላጎት ያለው የአካባቢ ማይክሮፋይናንስ ተቋም እንዳለ ታውቃለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምርቶቿን አገልግሎት ለተነፈጉ ማህበረሰቦች በማከፋፈል የደንበኛ አድማሷን ለማስፋት ከኤንጂኦ ጋር ትብብር መስርታለች፡፡
በመጨረሻም ሶፊያ ሁሉንም ዋና ዋና ክፍሎች ከግምት ውስጥ ማስገባቷን ለማረጋገጥ የገንዘብ ዘላቂነት ማረጋገጫ ዝርዝሩን ትገመግማለች፡፡ የገቢ ማግኛ መንገዶቿ ከትኩረት ደንበኞቿ ፍላጎቶች ጋር እንደሚስማሙ፣ ወጪዎቿን በአግባቡ እንደተቆጣጠረች እና የገቢ ማግኛ ነጥቧ የሚሳካ እንደሆነ ታረጋግጣለች፡፡ የንግድ ስራዋን በጀመረች በስድስት ወራት ውስጥ ከ200 በላይ ምርቶች በስኬት በመሸጥና የገቢ ማግኛ ነጥቧን በማሳካት ትርፎቿን የምርት መስመሯን ለማስፋት ኢንቨስት ማድረግ ጀምራለች፡፡
በአሁኑ ወቅት የሶፊያ የንግድ ሥራ እያደገ ከመሆኑም ባለፈ እንደ ለገጠር ቤተሰቦች ትእዛዝን መሰረት ያደረጉ የማገዶ አቅርቦት አገልግሎቶች የመሳሰሉ አዳዲስ እድሎችን እያጠናች ነው፡፡ የሶፊያ ጉዞ በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ የገንዘብ አዋጭነት ያለው የንግድ ሥራ ለመመስረት የገቢ ማግኛ መንገዶችን የመለየት፣ ወጪዎችን የመተንተን እና ትብብሮችን የማጎልበት አስፈላጊነትን ያሳያል፡፡