የባህርዳር፣ ኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነው የ28 ዓመት ወጣቱ ስራ ፈጣሪ ዓለም ገብሬ ሁልጊዜም የማህበረሰቡን የቴክኒክ ችግሮች የመፍታት ምኞት አለው፡፡ አለም በስፋት የተንሰራፋውን እና ለደን መጨፍጨፍ እና ለቤት ውስጥ አየር መበከል አስተዋጽኦ የሚያደርገውን በባህላዊ ማገዶና የከሰል ምድጃዎች ላይ ጥገኛ መሆን ከተገነዘበ በኋላ ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆነና ከጭስ ነጻ የሆኑ የኤሌክትሪክ የምግብ ማብሰያዎችን የሚሸጥበት የንግድ ስራ ለመጀመር ይወስናል፡፡ ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ንጹህ የማብሰያ ምርት ማቅረብ ብቻ በቂ እንዳልሆነና በተወዳዳሪ ገበያው ውስጥ ልቆ ለመውጣት ትኩረት ሳቢ ልዩ የእሴት ዕቅድ (ዩቪፒ) ማዘጋጀት እንዳለበት ይገነዘባል፡፡
ደረጃ 1: ዋና ችግሩን መለየት
አለም በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በማጥናት ይጀምራል፡፡ በቃለ መጠይቆች እና የዳሰሳ ጥናቶች አማካኝነት ሶስት ዋና ዋና ችግሮችን ይለያል፡
- ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች: ቤተሰቦች የገቢያቸውን ከፍተኛ ድርሻ የሚያወጡ ለማገዶ እንጨት ወይም ከሰል ነው፡፡
- የጤና ስጋቶች: ከባህላዊ ምድጃዎች የሚወጣው ጭስ በተለይም በሴቶች እና ህጻናት ላይ የመተንፈሻ አካል ችግሮችን ያስከትላል፡፡
- የአካባቢ ጉዳት: ከመጠን ያለፈ የማገዶ እንጨት መጠቀም የደን ጭፍጨፋን እና የአፈር መሸርሸርን ያስከትላል፡፡
አለም የኤሌክትሪክ የምግብ ማብሰያዎቹ እነዚህን ችግሮች እንደሚፈቱ ያውቃል፣ ነገር ግን ደንበኞች ከነባር አማራጮች ይልቅ ለምን የእርሱን መርጥ መጠቀም እንዳለባቸው በግልጽ ማብራት ይኖርበታል፡፡
ደረጃ 2: ተፎካካሪዎችን መተንተን
አለም የሱን መፍትሄ ልዩ ለማድረግ የተፎካካሪ ትንተና ቴምፕሌትን በመጠቀም የተፎካካሪ ትንተና ያካሂዳል፡፡
የራሱን ምርት ከባህላዊ ምድጃዎች፣ የጋዝ ምድጃዎች እና የሶላር ምድጃዎች ጋር ያነጻጽራል፡
|
ተፎካካሪ |
ምን እንደሚያቀርቡ |
ጥንካሬዎች |
ደካማ ጎኖች |
የእርስዎ እንዴት እንደሚለይ |
|
ባህላዊ ምድጃዎች |
ርካሽ ሆኖም ለጤና ጎጂ ናቸው |
ዋጋቸው ተመጣጣኝ ነው፣ በስፋት ይገኛሉ |
የጤና ስጋቶች፣ የደን መጨፍጨፍ |
ከጭስ ነጻ ነው፣ ለአካባቢ ተስማሚ ነው |
ይህ ትንተና አለምን የእሱን ዋና ዋና ልዩነቶች ማለትም፡ የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለአጠቃቀም ቀላል መሆን እና አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች በፍጥነት ተደራሽ መሆን ለመለየት ይረዳዋል፡፡
ደረጃ 3: ልዩ ጥቅሞችን ማብራራት
አለም የደንበኛ ጥቅም ማወቂያ ቴምፕሌትን በመጠቀም የሱ የኤሌክትሪክ ማብሰያዎች የሚያቀርቧቸውን ጥቅሞች በመዘርዘር ለትኩረት ደንበኞቹ ለምን ጠቃሚ እንደሆኑ ያብራራል፡
|
ጥቅም |
ለምን ለደንበኞች ጠቃሚ እንደሆነ |
እንዴት የእርስዎ መፍትሄ ይህን እንደሚያቀርብ |
|
የወጪ ቁጠባዎች |
የቤተሰብ ወጪዎችን ይቀንሳል |
ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው የኤሌክትሪክ ሀይል ይጠቀማል፣ ምንም የማገዶ ወጪ አያስወጣም፡፡ |
አለም የዋጋ ተመጣጣኝነትን፣ የጤና ጥቅሞችን እና የአካባቢ ዘላቂነትን አንድ ላይ ማጣመር ምርቱን በከፍተኛ ደረጃ ለገጠር እና የከተማ ቤተሰቦች ማራኪ እንደሚያደርገው ይገነዘባል፡፡
ደረጃ 4: ዩቪፒ ማዘጋጀት
አለም ይህን መረጃ በመያዝ የዩቪፒ ማዘጋጃ ቴምፕሌትን በመጠቀም የራሱን ልዩ የእሴት እቅድ ያዘጋጃል፡
- ዋና ችግር: ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች፣ የጤና ስጋቶች እና በባህላዊ የምግብ ማብሰያ ዘዴዎች ምክንያት የሚደርስ የአካባቢ ጉዳት፡፡
- መፍትሄ: በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው፣ ከጭስ ነጻ የሆኑ የኤሌክትሪክ የምግብ ማብሰያዎች፡፡
- ልዩ ጥቅሞች: የወጪ ቁጠባዎች፣ የጤና ማሻሻያዎች፣ የአካባቢ ዘላቂነት፡፡
- ልዩነት: ከሶላር የምግብ ማብሰያዎችና የጋዝ ምድጃዎች ጋር ሲነጻጸሩ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ በቀላሉ መጠቀም እና ለአካባቢ ተስማሚ ዲዛይን፡፡
- የትኩረት ደንበኛ: የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ የከተማና ከፊል ከተማ ቤተሰቦች፡፡
የዩቪፒ መግለጫ:
“የኤሌክትሪክ የምግብ ማብሰያዎቻችን በዋጋ ተመጣጣኝ፣ ከጭስ ነጻና ለአካባቢ ተስማሚ ስለሆኑ ገንዘብ ይቆጥባሉ፣ የቤተሰብዎን ጤና ይጠብቃሉ እንዲሁም እንዲሁም የኢትዮጵያን ደኖች ከመጨፍጨፍ ይታደጋሉ፡፡“
ደረጃ 5: ዩቪፒውን መሞከርና ማጥራት
አለም ዩቪፒው ለደንበኞች የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ የዩቪፒ ሙከራ ግብረ መልስ ቅጽን በመጠቀም ዩቪፒውን ይሞክራል፡፡
መግለጫውን ለ10 ቤተሰቦች አጋርቶ ግብረ መልሳቸውን ይሰበስባል፡
|
ጥያቄ |
መልስ |
ግንዛቤዎች/እርምጃዎች |
|
ዩቪፒያችን ጠቀሜታውን በግልጽ ያብራራል? |
አዎ |
ደንበኞች ጥቅሞቹን ተረድተዋል፡፡ |
በግብረ መልሱ ላይ ተመስርቶ አለም ዩቪፒውን የዋጋ ተመጣጣኝነት በሚፈታ መልኩ በማጥራት በመልዕክቱ ውስጥ ልዩ የዋጋ ዝርዝሮችን ያካትታል፡፡
ውጤት
የንግድ ስራውን በጀመረ በስድስት ወራት ውስጥ አለም ከ200 በላይ የኤሌክትሪክ ምድጃዎችን በመሸጥ ከደንበኞች የአድናቆት አስተያየቶችን አግኝቷል፡፡ ያዘጋጀው ግልጽና ትኩረት ሳቢ ዩቪፒ ለምርቱ ልዩነት መፍጠር ብቻም ሳይሆን በትኩረት ደንበኞቹ ዘንድ እምነትና ተአማኒነት እንዲገነባ አስችሎታል፡፡ በአሁኑ ወቅት አለም ስራዎቹን ወደ አጎራባች ከተሞች ለማስፋት እያቀደ ሲሆን ዩቪፒው የደንበኛ ተቀባይነትነት እያስገኘለት እንደሚቀጥል በራስ መተማመን አለው፡፡
ከዓለም ታሪክ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች
- ችግርን ከመፍትሄ ማስማማት: የአለም ዩቪፒ እንደ ከፍተኛ ወጪዎችና የጤና ስጋቶች የመሳሰሉ የተረጋገጡ የደንበኛ ችግሮችን በቀጥታ ፈቷል፡፡
- ልዩነት መፍጠር: ተፎካካሪዎችን በመተንተን አለም ምርቱን ምን ልዩ እና የላቀ እንደሚያደርገው ለይቷል፡፡
- የደንበኛ ጥቅሞች: እንደ የወጪ ቁጠባዎች እና የጤና ማሻሻያዎች ያሉ ተጨባጭ ጥቅሞችን ማብራራት ዩቪፒውን ከደንበኞች ጋር ለማስማማት አስችሎታል፡፡
- ሙከራና መደጋገም: ግብረ መልስ መሰብሰቡ አለምን ዩቪፒውን እንዲያጠራ እና ግልጽ መሆኑን፣ ትኩረት መሳቡን እና የተግባር መሆኑን እንዲያረጋግጥ አስችሎታል፡፡