የሰላማዊት የንግድ ሀሳብ – ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎች የመጀመር ጉዞ
የሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነችው የ22 ዓመት ዕድሜ ያላት ሰላማዊት ከበደ ሁልጊዜም በማህበረሰቧ ውስጥ ለውጥ የማምጣት ህልም አላት፡፡ ሰላማዊት ያደገችው የማገዶች እንጨት በሚጠቀሙ ባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ እንደመሆኑ የማገዶ እንጨት በመሰብሰብ ሰዓታትን የሚያባክኑ እና በቤት ውስጥ የአየር መበከል ጎጂ ተጽእኖዎች የተነሳ የሚሰቃዩ ሴቶች እና ህጻናትን የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች የመጀመሪያ ምስክር ነች፡፡ ለውጥ ለማምጣት የቆረጠችው ሰላማዊት ጤናን የሚያሻሽሉ፣ ጊዜ የሚቆጥቡ እና የአካባቢ ጉዳትን የሚቀንሱ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችን የምትሸጥበት የንግድ ሥራ ለመጀመር ትወስናለች፡፡
ችግሩን መለየት
ሰለማዊት በቀጥታ ወደ የንግድ ሥራ ሀሳቧ ከመግባቷ በፊት ትኩረት የምታደርግባቸውን ደንበኞች ልዩ ችግሮች መረዳት እንዳለባት ታውቃለች፡፡ ስራዋን ለ15 የመኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች ቃለ መጠይቅ በማድረግ የጀመረች ሲሆን በዚህም ስለ ምግብ ማብሰል ልማዶቻቸው፣ ችግሮቻቸውና ምርጫዎቻቸው የተመለከቱ ጥያቄዎችን ትጠይቃቸዋለች፡፡ በእነዚህ ውይይቶች አማካኝነት የሚከተሉት ሶስት ዋና ዋና ችግሮች እንዳሉ ታውቃለች፡
- ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች: ብዙ ቤተሰቦች የቤተሰቡን ከፍተኛ የወጪ ድርሻ የሚወስድባቸውን ከሰል ወይም የማገዶ እንጨት ለመግዛት ይቸገራሉ፡፡
- የጤና ስጋቶች: ከባህላዊ ምድጃዎች የሚወጣው ጭስ በተለይም ብዙ ጊዜያቸውን በቤት ውስጥ በሚያሳልፉት ሴቶችና ህጻናት ላይ የመተንፈሻ አካል ህመሞችን ያስከትላል፡፡
- ጊዜ የሚፈጁ ስራዎች: የማገዶ እንጨት መሰብሰብ የየዕለት የስራ ጫና ሲሆን በአብዛኛው በርቀት ወደሚገኙ ጫካዎች ረጅም ርቀት መጓዝን ይጠይቃል፡፡
ሰላማዊት ግኝቶቿን ለማረጋገጥ በተጨማሪም በማህበረሰብ ስብሰባዎች ወቅት በምግብ ማብሰል አሰራሮች ላይ ምልከታ ታደርጋለች እንዲሁም በገጠሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የኢነርጂ አጠቃቀም የተመለከቱ ሪፖርቶችን ትገመግማለች፡፡ በጥናቷም እነዚህ ችግሮች በእጩ ደንበኞቿ የእለት ከዕለት አኗኗር ውስጥ በስፋት የተንሰራፉ እና ስር የሰደዱ እንደሆኑ ታረጋግጣለች፡፡
መፍትሄ ማዘጋጀት
ስለ ችግሮቹ በተመለከተ ግልጽ ግንዛቤ ያገኘችው ሰላማዊት የማህበረሰቧን ፍላጎቶች ያካተተ መፍትሄ ለማዘጋጀት ትዘጋጃለች፡፡ ዋጋቻው ተመጣጣኝ የሆኑ እና ለአጠቃቀም ቀላል የሆኑ ማገዶ ቆጣቢ የሆኑ የማብሰያ ምድጃዎች ለማምረት ከአካባቢ አምራች ጋር ሽርክና ትፈጥራለች፡፡ የዋጋ ተመጣጣኝነት ችግሮችን ለመፍታት ደንበኞችን በሶስት ወራት የተከፋፈሉ አነስተኛ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ የሚያስችላቸው ተለዋዋጭ የክፍያ ዕቅድ ታዘጋጃለች፡፡ በተጨማሪም ቤተሰቦችን ምድጃዎቹን እንዴት ውጤታማና አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንደሚጠቀሙ ለማስተማር ነጻ የስልጠና ክፍለ ጊዜዎች ታዘጋጃለች፡፡
ሰላማዊት በተጨማሪም ስለ ንጹህ የምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂዎች በተመለከተ ግንዛቤ የመፍጠር አስፈላጊነትን ትገነዘባለች፡፡ ከዚያም ደንበኞች ወደ ንጹህ የምግብ ማብሰያ አማራጮች መቀየር የሚያስገኛቸውን የጤናና አካባቢ ጥቅሞች የሚማሩባቸው አውደ ጥናቶች ለማዘጋጀት ከአካባቢ የሴት ቡድኖችና ትምህርት ቤቶች ጋር ትብብር ትመሰርታለች፡፡ እነዚህ ጥረቶች ማህበረሰቡን ማስተማር ብቻ ሳይሆን ለምርቷ እምነትና ተአማኒነትን ያጎለብታል፡፡
ሙከራና ድግግሞሽ
ምርቷን በስፋት ማከፋፈል ከመጀመሯ በፊት የማብሰያ ምድጃዎቿን በማህበረሰቧ ውስጥ ባሉ አምስት ቤተሰቦች ላይ ትሞክራለች፡፡ ለእነዚህ ቤተሰቦች የመጀመሪያ ሙከራ ታቀርብላቸው እና ከሁለት ሳምንታት መጠቀም በኋላ ግብረ መልሳቸውን ትሰበስባለች፡፡ ውጤቶቹ በሚገርም መልኩ አዎንታዊ ሲሆኑ ተጠቃሚዎቹ ምድጃዎቹ ጭስ እንደሚቀንሱ፣ የማብሰያ ጊዜን እንደሚያፈጥኑ እና የማገዶ ወጪዎችን እንደሚቀንሱ ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ ሆኖም አንዳንድ ደንበኞች የመጀመሪያው ምድጃዎቹን የመግጠም ሂደት በመጠኑ ግራ አጋቢ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ሰላማዊት ይህን ግብረ መልስ ከግምት ውስጥ በማስገባት መመሪያዎቹን በማቃለል በተለያዩ የአካባቢ ቋንቋዎች ደረጃ በደረጃ የእይታ መርጃዎችን ታካትታለች፡፡
ውጤቱን ማሳደግ
ሰላማዊት የንግድ ሥራዋን በጀመረች በስድስት ወራት ውስጥ ከ100 በላይ የማብሰያ ምድጃዎችን ከመሸጧም ባለፈ በትምህርት አውደ ጥናቶቿ አማካኝነት ከ500 በላይ ግለሰቦች ጋር ትደርሳለች፡፡ የሰላማዊት ስኬት ትኩረቱን የሳበው በዘላቂ ኢነርጂ ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ አንድ የክልል ኤንጂኦ የምድጃዎቹን ማከፋፈል በአቅራቢያ ወደሚገኙ የገጠር አካባቢዎች ለማስፋፋት በትብብር የመስራት ሀሳብ ያቀርብላታል፡፡ በዚህ ድርጅት ድጋፍ ሰላማዊት የዋጋ ተመጣጣኝነትና ተደራሽነት ቁርጠኝነቷን እንደጠበቀች ስራዎቿን ማሳደግ ችላለች፡፡
በአሁኑ ወቅት የሰላማዊት የንግድ ከሀዋሳ አልፎ የሌሎችንም አኗኗር እየቀየረ ነው፡፡ ቤተሰቦች ገንዘብ እየቆጠቡ፣ ንጹህ አየር እየተነፈሱ እና እንደ የማገዶ እንጨት ስብሰባ ላሉ የጉልበት ስራዎች የሚያጠፉትን ጊዜ እየቀነሱ ነው፡፡ ለሰላማዊት ጉዞዋ በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በግልም የሚያበረታታ ነው፡፡ “ይህን የንግድ ሥራ የጀመርኩት ማህበረሰቤን ለመርዳት ነው” የምትለው ሰላማዊት “ሰዎች አኗኗራቸው ምን ያክል ቀላል እንደሆነላቸው ሲነግሩኝ በፊታቸው ላይ የማየው ፈገግታ በስራዬ እንድቀጥልበት ያበረታታኛል፡፡” በማለት ትናገራለች፡፡
ከሰላማዊት ታሪክ የተወሰዱ ዋና ዋና ሀሳቦች
- ችግርን መለየት: የደንበኛ ችግሮችን በጥንቃቄ በማጥናትና በማረጋገጥ ሰላማዊት መፍትሄዋ የእውነተኛውን ዓለም ችግሮች የሚፈታ እንደሆነ አረጋግጣለች፡፡
- ደንበኛን ማዕከል ያደረገ አቀራረብ: ለተደራሽነት፣ ጥቅም ላይ መዋል መቻል እና ትምህርት የሰጠችው ትኩረት ምርቷን ትኩረት ለተደረገባቸው ደንበኞች ተደራሽ እና ማራኪ እንድታደርግ አስችሏታል፡፡
- ተደጋጋሚ ማሻሻያ: በደንበኛ ግብረ መልስ ላይ ተመስርታ ምርቷን መሞከሯና ማጣራቷ ሰላማዊትን የተሻለ፣ የበለጠ አስተማማኝ አቀርቦት እንድታዘጋጅ አስችሏታል፡፡
- በትብብሮች ማሳደግ: ከኤንጂኦ ጋር በትብብር መስራቷ ሰፊ የደንበኛ አድማስ ጋር እንድትደርስና ውጤቷን እንድታጎላ አስችሏታል፡፡
የሰላማዊት ታሪክ እንዴት በአግባቡ የተፈጸመ ችግርን የመለየት ሂደት በንጹህ የምግብ ማብሰያ ዘርፉ ውስጥ ለስኬታማና ውጤት አምጪ የስራ ፈጣሪ ስራ መሰረት መጣል እንደሚችል ይገልጽልናል፡፡