Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ፍቺ/ትርጉም

የገቢ ማግኛ መንገዶች እና የወጪ መዋቅር የንግድ ስራ ሞዴልን የገንዘብ መሰረት ይገልጻል፡፡

  • የገቢ ማግኛ መንገዶች: የንግድ ስራዎ ገቢ የሚያገኝባቸው እንደ ቀጥተኛ ሽያጭ፣ ግዢዎች፣ ሽርክናዎች ወይም የአገልግሎት ክፍያዎች የመሳሰሉ የገቢ ምንጮች ናቸው፡፡
  • የወጪ መዋቅር: ምርትን፣ ግብይትን እና የማከፋፈያ ወጪዎችን ጨምሮ የንግድ ሥራዎን ለመጀመር የሚከፈሉ ዋና ዋና ወጪዎች ናቸው፡፡
    እነዚህን ክፍሎች መረዳት የንግድ ስራዎ የገንዘብ ዘላቂነት እንዲኖረው እና ትርፋማ እንዲሆን ያስችላል፡፡

የትምህርቱ ዓላማዎች

ይህ ትምህርት ሲያበቃ እርስዎ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ:

  1. ከንግድ ስራ ሞዴልዎ ጋር የሚጣጣሙ ሊሳኩ የሚችሉ የገቢ ምንጮችን (ምሳ፡ ቀጥተኛ ሽያጭ፣ ሽርክናዎች) ለይተው ያውቃሉ፡፡
  2. የንግድ ስራዎን የገንዘብ ዘላቂነት ለማረጋገጥ የንግድ ስራውን ለመጀመርና ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን መተንተን፡፡

ዓላማ

የዚህ ትምህርት ዓላማ ስራ ፈጣሪዎችን ተጨባጭ የገቢ ማግኛ መንገዶችን በመለየት እና ተያያዥ ወጪዎችን በመረዳት የገንዘብ አዋጭነት ያለው የንግድ ስራ ሞዴል እንዲያዘጋጁ መርዳት ነው፡፡ ይህን ማድረግ ንጹህ የምግብ ማብሰያ ምርትዎ ወጪዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ በማስተዳደር ገቢ ማግኘት እንዲችል ያደርጋል፡፡

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች

  1. የገቢ ማግኛ መንገዶች:
    • ቀጥተኛ ሽያጮች፡ ምርቶችን በቀጥታ ለደንበኞች መሸጥ (ምሳ፡ የማብሰያ ምድጃዎች፣ ሰው ሰራሽ ከሰሎች)፡፡
    • ሽርክናዎች: ለምርቶቹ ድጎማ ለማግኘት ወይም ለማከፋፈል ከሌሎች የንግድ ድርጅቶች፣ ኤንጂኦዎች፣ የአካባቢ ድርጅቶች ወይም የመንግስት ፕሮግራሞች ጋር በትብብር መስራት፡፡
    • የአገልግሎት ክፍያዎች፡ ለምርትዎ የጥገና ወይም የስልጠና አገልግሎቶች መስጠት፡፡
  2. የወጪ መዋቅር:
    • ቋሚ ወጪዎች፡ እንደ ኪራይ፣ መሳሪያዎች ወይም ደመወዞች ያሉ በቋሚነት የሚከፈሉ ወጪዎች፡፡
    • ተለዋዋጭ ወጪዎች፡ እንደ ጥሬ እቃዎች ወይም ትራንስፖርት ያሉ በምርት ወይም የሽያጭ መጠን ላይ ተመስርተው የሚለያዩ ወጪዎች፡፡
    • የመጀመሪያ ኢንቨስትመንት፡ እንደ የመጀመሪያ ሙከራ ወይም ማረጋገጫዎች ያሉ የንግድ ስራዎን ለመጀመር የሚያስፈልጉ ወጪዎች ናቸው፡፡
  3. የትርፋማነት ትንተና:
    • የንግድ ስራዎ መቼ ትርፍ ማስገኘት እንደሚጀምር ለመወሰን የገቢ ማግኛ ጊዜውን ያስሉ፡፡
    • የገቢ ማግኛ መንገዶች በጊዜ ሂደት ከጠቅላላ ወጪዎች እየበለጡ መሄዳቸውን ያረጋግጡ፡፡
  4. በንጹህ የማብሰያ ዘርፉ ላይ መተግበር:
    • እንደ ከማይክሮፋይናንስ ተቋማት ጋር ሽርክና በመፍጠር በዋጋ ተመጣጣኝ የሆኑ የሶላር የምግብ ማብሰያዎችን መሸጥ ወይም ትእዛዝን መሰረት ያደረጉ የማገዶ አቅርቦት አገልግሎቶች የመሳሰሉ ምሳሌዎችን ያጥኑ፡፡

ምሳሌ: የሶፊያ ጉዞ

የ22 ዓመቷ የአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ነዋሪ የኮሌጅ ተማሪ የሆነችው ሶፊያ የፈጠራ ዝንባሌ አላት፡፡ እንደ የኮሌጅ ፕሮጀክቷ አንድ ክፍል ለከተማ ነዋሪዎች ታስቦ የሚዘጋጅ የፈጠራ ለአያያዝ ቀላል የሆነ የሶላር የምግብ ማብሰያ ታዘጋጃለች፡፡ ሀሳቧን ወደ ንግድ ስራ ለመቀየር የገቢ ማግኛ መስመሮችን በመለየት እና ወጪዎችን መተንተን ላይ ትኩረት ታደርጋለች፡፡

  1. የገቢ ማግኛ መንገዶች:
    • ቀጥተኛ ሽያጭ፡ ሶፊያ የሶላር የምግብ ማብሰያዎቿን በኦንላይን ፕላትፎርሞችና የአካባቢ ገበያዎች በኩል በቀጥታ ለከተማ ቤተሰቦች ትሸጣለች፡፡
    • ሽርክናዎች: ሶፊያ ተደራሽነትን በማሳደግ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች የወጪ ድጎማ ለማድረግ ከአካባቢ ኤንጂኦ ጋር በትብብር ትሰራለች፡፡
    • የአገልግሎት ክፍያዎች: ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለሚፈልጉ ደንበኞች አማራጭ የጥገና መርሀግብሮችን ታቀርባለች፡፡
  2. የወጪ መዋቅር:
    • ቋሚ ወጪዎች፡ የአነስተኛ ቤተ ሙከራ ኪራይ፣ የኦንላይን ሽያጮች ወርሀዊ የኢንተርኔት ወጪዎች እና የመሰረታዊ መሳሪያዎች መገጣጠሚያ ወጪዎች፡፡
    • ተለዋዋጭ ወጪዎች፡ ጥሬ ዕቃዎች (ሶላር ፓኔሎች፣ ካስቲንግ)፣ የማሸጊያና አቅርቦት ወጪዎች፡፡
    • የመጀመሪያ ኢንቨስትመንት: የመጀመሪያ ሙከራ፣ የማረጋገጫ ክፍያዎች እና የመጀመሪያ ንብረት ማፍሪያ፡፡
  3. የትርፋማነት ትንተና:
    • ሶፊያ ወርሀዊ ቋሚ ወጪዎቿ (ብር 5000) እና በአንድ ዩኒት ተለዋዋጭ ወጪዎቿ (ብር 500) እንደሆኑ በመገመት የገተቢ ማግኛ ጊዜዋን ታሰላለች፡፡
    • በብር 500 የአንድ ምርት የመሸጫ ዋጋ ወጪዎቿን ሸፍና ትርፍ ማግኘት ለመጀመር በወር ቢያንስ 25 ምርቶችን መሸጥ እንዳለባት ትወስናለች፡፡
    • ቀመር – [የገቢ ማግኛ ጊዜ (ምርቶች) = ቋሚ ወጪዎች ÷ (የአንድ ምርት የመሸጫ ዋጋ – የአንድ ምርት ተለዋዋጭ ወጪዎች)
  4. ውጤት:
    ሶፊያ የገቢ ማግኛ መንገዶቿን ከትኩረት ደንበኞቿ ፍላጎቶች ጋር በማስማማት እና ወጪዎቿን በጥንቃቄ በማስተዳደር የንግድ ስራዋን በስኬት ትጀምራለች፡፡ በስድስት ወራት ውስጥ ገቢ ማግኘት ከመጀመሯም ባለፈ ትርፏን የምርት መስመሯን ለማስፋት ኢንቨስት ማድረግ ትጀምራለች፡፡
Scroll to Top