Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ፍቺ/ ትርጓሜ

የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅ ስራ ፈጣሪዎችን እና ጀማሪዎችን የንግድ ሥራ ሀሳቦቻቸውን በፍጥነት እንዲያደራጁ፣ እንዲያረጋግጡ እንዲገልጹ ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀ አንድ ገጽ ስትራቴጂያዊ መሳሪያ ነው፡፡ ረቂቁ የንግድ ሥራ ንድፈ ሀሳብን በዘጠኝ ዋና ዋና የመነሻ ነጥቦች ማለትም፡ ችግር፣ መፍትሄ፣ ዋና ዋና መለኪያዎች፣ ልዩ የዋጋ ዕቅድ፣ የደንበኛ ምድቦች፣ የግንኙነት መስመሮች፣ የወጪ መዋቅር እና የገቢ ማግኛ መንገዶች ይከፋፍላል፡፡

 

ረጅም እና ጊዜ ወሳጅ ሊሆኑ ከሚችሉት ባህላዊ የንግድ ሥራ እቅዶች በተቃራኒው የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅ ስጋቶችን ከመቀነስ ጎን ለጎን እውነተኛ የደንበኛ ችግሮችን በመፍታት ላይ የሚያተኩር አጭርና የድርጊት ማዕቀፍ ይሰጣል፡፡

በኢትዮጵያ ንፁህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ ላሉ አዲስ ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅ የንግድ ስራ ሀሳቦችዎ እንደ በባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ መሆንን መቀነስ ወይም በንጹህ የኢነርጂ ውጤቶች አማካኝነት የቤተሰብ ኢኮኖሚና ጤናን ማሻሻል በመሳሰሉ ተጨባጭ የገበያ ፍላጎቶች ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደ የተግባር መመሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ጥቅሞች

  1. ግልጽነት እና ትኩረት: የንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ የሥራ ፈጣሪዎችን በአላስፈላጊ ዝርዝሮች ከመጠለፍ ይልቅ ትኩረታቸውን ተጨባጭ የገሀዱን ዓለም ችግሮች በመፍታት ላይ ማድረጋቸውን በማረጋገጥ ሀሳቦቻቸውን በግልጽና ሊተገበሩ በሚችሉ ክፍሎች እንዲያጠሩ ያስገድዳቸዋል፡፡
  2. ውጤታማ የሀብት ምደባ: ስራ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ውጤት የሚያስገኙ ስራዎችን በመለየት እና ለሀብቶች ቅድሚያ በመስጠት የወጪ ብክነትን ማስቀረት እና ውሱን በጀቶቻቸውን ማሳደግ ይችላሉ፡፡
  3. ዕሳቤዎችን ማረጋገጥ: ሥራ ፈጣሪዎች ቀደም ብለው እንደ የደንበኛ ችግሮች እና የገቢ ማግኛ ሞዴሎች ያሉ ዋና ዋና ክፍሎችን ለይተው በማወቅና ያለመሳካት ስጋቶችን በመቀነስ እሳቤዎቻቸውን መፈተሽ ይችላሉ፡፡
  4. በተደጋጋሚ ማሻሻል: የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅ ሥራ ፈጣሪዎች ግብረ መልስ ሲሰበስቡና ሀሳቦቻቸውን ሲያጣሩ እያደገ የሚሄድ፣ ቀጣይነት ያለው ትምህርትና ማሻሻያን የሚያጎለብት ሕያው ሰነድ ነው፡፡
  5. የመገናኛ መሳሪያ: ይህ ሀሳቦችዎን ለባለድርሻ አካላት፣ አማካሪዎች ወይም ዕጩ ባለሀብቶች የሚያጋሩበት ቀላል ሆኖም ሁሉን አቀፍ መንገድ የሚሰጥ ሲሆን ይህም ድጋፍ ማግኘትን ቀላል ያደርገዋል፡፡
  6. ለንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አስፈላጊነት: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ስራ ፈጣሪዎችን የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅ እንደ ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆነ የማብሰያ ምድጃዎች ወይም የተፈጥሮ ማገዶ አማራጮችን ከደንበኛ ፍላጎቶች፣ የአካባቢ ዘላቂነት እና የገንዘብ አዋጭነት ጋር ማስማማት ያሉ መፍትሄዎችን እንዲያረጋግጡ ያስችላቸዋል፡፡

 

ለትኩረት ቡድን አግባብነት ያለው ምሳሌ

ኩነት: ሰላማዊት የምትባል ወጣት ሴት ሥራ ፈጣሪ በሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችን በመሸጥ የንግድ ሥራ ለመጀመር ትፈልጋለች፡፡ ሰላማዊት ሀሳቧን ለማደራጀት የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅ ትጠቀማለች፡

  1. ችግር: ብዙ አባወራዎች በባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ መሆናቸው ከፍተኛ ወጪን፣ የቤት ውስጥ አየር ብክለትን እና የጤና ስጋቶችን ያስከትልባቸዋል፡፡
  2. መፍትሄ: ጭስን የሚቀንሱ እና የማብሰያ ቅልጥፍናን የሚያሻሽሉ በዋጋ ተመጣጣኝ፣ ለአካባቢ ተስማሚ የማብሰያ ምድጃዎች፡፡
  3. ዋና ዋና መለኪያዎች: ምርቱን የሚጠቀሙ ቤተሰቦች ብዛት፣ የቤት ውስጥ አየር ብክለት መቀነስ፣ የደንበኛ እርካታ ደረጃዎች፡፡
  4. ልዩ የዋጋ ዕቅድ: የማብሰያ ምድጃዎቹ ዋጋ ከተፎካካሪዎች ዋጋ በ30% የሚቀንስ ከመሆኑም በተጨማሪ ነጻ ተከላና ስልጠና ይቀርባል፡፡
  5. የደንበኛ ምድቦች: የገጠር አባወራዎች፣ የከተማ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች፣ በሴት እማወራ የሚመሩ ቤተሰቦች፡፡
  6. የግንኙነት መስመሮች: የአካባቢ ገበያዎች፣ የማህበረሰብ አውደ ጥናቶች፣ ከኤንጂኦዎች ጋር የሚደረጉ ትብብሮች፡፡
  7. የወጪ መዋቅር: የማምረቻ ወጪዎች፣ የገበያ ወጪዎች፣ የማከፋፈያ ሎጅስቲክስ፡፡
  8. የገቢ ማግኛ መንገዶች: የማብሰያ ምድጃዎች ቀጥተኛ ሽያጭ፣ የተተኪ መለዋወጫዎች ግዢ ሞዴል፣ የትብብር ማበረታቻዎች፡፡

 

የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅን በመጠቀም ሰላማዊት በንግድ ሥራ ሞዴሏ ላይ ግልጽነትን ታገኛለች እንዲሁም ትኩረት የምታደርግባቸውን እንደ ትኩረት የሚደረግባቸው የገጠር ቤተሰቦች እና ለማከፋፈል ከኤንጂኦዎች ጋር በትብብር መስራት የመሳሰሉ ዋና ዋና መስኮችን ለይታ ታውቃለች፡፡

Scroll to Top