ይህ የማረጋገጫ ዝርዝር የተዘጋጀው በትምህርቱ ውስጥ የተካተቱ የዋና ዋና ንድፈ ሀሳቦች እና መሳሪያዎች ግንዛቤዎን ለመገምገም እንዲረዳዎ ነው፡፡ የማረጋገጫ ዝርዝሩ ከጥያቄዎችና ሙከራዎች ጋር የሚስማማ ከመሆኑም በተጨማሪ እድገትን ለመከታተል እና የማሻሻያ ሀሳቦችን ለመለየት የሚያስችል ቀላልና ግልጽ መንገድ ይሰጣል፡፡
ክፍል 1: ችግርን የመለየት ዋና ዋና ንድፈ ሀሳቦች
ዓላማ: ችግርን የመለየት መሰረታዊ እውቀትን መመዘን፡፡
- ችግርን የመለየት ዋነኛ ግብን ማብራራት እችላለሁ (ምሳ፡ የደንበኛ ችግሮችን መለየት እና ለእርስዎ አግባብነት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ)፡፡
- በንጹህ የማብሰያ ዘርፉ ውስጥ ያሉ የተለመዱ ችግሮችን እረዳለሁ (ምሳ፡ ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች፣ በቤት ውስጥ አየር መበከል ምክንያት የሚመጡ የጤና ስጋቶች፣ በባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ መሆን)፡፡
- ማረጋገጫ ለምን ችግርን ለመለየት አስፈላጊ እንደሆነ እረዳለሁ (ምሳ፡ መፍትሄዎች የእውነተኛውን ዓለም ችግሮች የሚፈቱ መሆናቸውን ያረጋግጣል)፡፡
- የደንበኛ ችግሮችን ለማረጋገጥ የሚያገለግሉ ቢያንስ ሁለት ዘዴዎችን መጥራት እችላለሁ (ምሳ፡ ቃለ መጠይቆች፣ የዳሰሳ ጥናቶች፣ ምልከታዎች)፡፡
- በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ ችግርን መለየት እንዴት ለስራ ፈጣሪዎች እንደሚጠቅም መግለጽ እችላለሁ (ምሳ፡ መፍትሄዎች ውጤት አምጪና አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 10 ነጥቦች
ክፍል 2: የመሳሪያዎችና ቴምፕሌቶች ትግበራ
ዓላማ: የተሰጡትን መሳሪያዎችና ቴምፕሌቶች በመጠቀም ብቁነትን ማረጋገጥ፡፡
- የችግር መለያ ወርክሺቱን ሞልቻለሁ እንዲሁም ዋና ዋና ችግሮቹን ለይቻለሁ፣ አረጋግጫለሁ እንዲሁም ከመፍትሄዬ ጋር አስማምቻለሁ፡፡
- ችግሮችን ለመለየት፣ ወቅታዊ መፍትሄዎችን ለመተንተን እና የማሻሻያ እድሎችን ለመለየት የደንበኛ ችግሮች ማወቂያ ቴምፕሌቱን ተጠቅሜያለሁ፡፡
- የችግር ማረጋገጫ ዝርዝሩን ዓላማ እና እንዴት የደንበኛ ችግሮችን በብልሀት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተረድቻለሁ፡፡
- ከአካባቢ ድርጅቶች ጋር የሚደረግ ትብብር እንዴት ችግርን የመለየት ሂደቱን እንደሚያሻሽል ማብራራት እችላለሁ (ምሳ፡ ዳታ፣ የተለያዩ እይታዎችን ማግኘት)፡፡
- እነዚህን መሳሪያዎች በራሴ የንግድ ስራ ሀሳብ ወይም የግምት ኩነት ላይ በራስ መተማመን እተገብራለሁ፡፡
ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 10 ነጥቦች
ክፍል 3: የጉዳይ ጥናት ገለጻ
ዓላማ: የጉዳይ ጥናቱን ምሳሌ ይግለጹ እና ትምህርቶቹን በራስዎ ስራ ላይ ይተግብሩ፡፡
- የሰላማዊት ከበደን የጉዳይ ጥናት አንብቤ ስለ ደንበኛ ችግሮች በተመለከተ ያሏትን እሳቤዎች እንዴት እንዳረጋገጠች ተረድቻለሁ፡፡
- ሰላማዊት መፍትሄዋ ደንበኛን ያማከለ መሆኑን ለማረጋገጥ የተጠቀመችባቸውን ስትራቴጂዎች ለይቻለሁ (ምሳ፡ የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ትምህርት፣ ትብብሮች)፡፡
- ከሰላማዊት ስትራቴጂዎች መካከል አንዱ እንዴት በራሴ የንግድ ስራ ሀሳብ ላይ ሊተገበር እንደሚችል አብራርቻለሁ፡፡
- ገለጻዎቼን የሚያጠቃልል አጭር አንቀጽ ጽፌ ግብረ መልስ ለማግኘት ለእኩያዬ ወይም አማካሪ አጋርቻለሁ፡፡
- በጉዳይ ጥናቱ መነሳሳት እንደተፈጠረብኝ እና በራሴ የሥራ ፈጠራ ጉዞ ላይ ተመሳሳይ ስትራቴጂዎችን ለመተግበር እንደተነሳሳሁ ይሰማኛል፡፡
ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 10 ነጥቦች
ክፍል 4: አጠቃላይ በራስ መተማመን ደረጃ
ዓላማ: ችግርን የመለየት እውቀትን የማወቅ አጠቃላይ በራስ መተማመንን መለካት፡፡
- በንጹህ የማብሰያ ዘርፉ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና ችግሮችን የመለየትና የመግለጽ በራስ መተማመን አለኝ፡፡
- ቃለ መጠይቆችን፣ የዳሰሳ ጥናቶችን ወይም ምልከታዎችን በመጠቀም እንዴት የደንበኛ ችግሮችን ማረጋገጥ እንደሚቻል እረዳለሁ፡፡
- በተረጋገጡት ችግሮች ላይ ተመስርቼ ደንበናን ያማከሉ መፍትሄዎችን ማዘጋጀት እችላለሁ፡፡
- በዚህ ትምህርት ውስጥ የቀረቡትን መሳሪያዎችና ቴምፕሌቶች ያወቅኳቸው ከመሆኑም ባለፈ እነዚህን ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠቀም እችላለሁ፡፡
- የራሴን የንግድ ስራ ሀሳብ ወደማዘጋጅበት ቀጣዩ ደረጃ ለማለፍ ዝግጁ ነኝ (ምሳ፡ የንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ፣ የመፍትሄ ዲዛይን)፡፡
ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 10 ነጥቦች
የመጨረሻ ውጤት አሰጣጥና ግብረ መልስ
- የሁሉንም ክፍሎች ውጤቶችዎን ይደምሩ፡፡
- ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 40 ነጥቦች
የውጤቶች ትንተና:
- ከ35–40 ነጥቦች: በጣም ጥሩ! ችግርን የመለየት ጠንካራ ግንዛቤ ስላገኙ እነዚህን ክህሎቶች በራስ መተማመን ለመተግበር ዝግጁ ነዎት፡፡
- ከ25–34 ነጥቦች: ጥሩ! አብዛኞቹን ንድፈ ሀሳቦች የተገነዘቡ ቢሆንም ልዩ የመሻሻያ መስኮችን መለስ ብለው ማየት ያስፈልግዎታል፡፡
- ከ25 ነጥቦች በታች: መሻሻል ያለበት፡፡ የትምህርቱን ቁሳቁሶች፣ ተያያዥ ጥያቄዎች በድጋሚ ማንበብ እና መሳሪያዎቹን እና ቴምፕሌቶቹን በመጠቀም እንደገና መለማመድ አለብዎት፡፡