Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ፍቺ/ትርጉም

ልዩ የእሴት ዕቅድ (ዩቪፒ)ምርትዎ ወይም አገልግሎትዎ አንድን ችግር እንዴት እንደሚፈታ፣ ልዩ ጥቅሞችን እንደሚያቀርብ እና ለምን ከነባር አማራጮች እንደሚበልጥ የሚያብራራ ግልጽ መግለጫ ነው፡፡ በንፁህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ውስጥ ጠንካራ ዩቪፒ የእርስዎን መፍትሄ ጎልቶ እንዲወጣ የሚያደርገውን ነገር አጉልቶ ያሳያል— ለምሳሌ፡ የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ የጤና ጥቅማጥቅሞች፣ የአካባቢ ዘላቂነት፣ ወይም የአጠቃቀም ቀላልነት—እንዲሁም ደንበኞች አቅርቦትዎን ከተወዳዳሪዎችዎ ይልቅ እንዲመርጡ ያሳምናቸዋል፡፡

 

የትምህርቱ ዓላማዎች

ይህ ትምህርት ሲያበቃ እርስዎ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ:

  1. የእርስዎን ንጹህ የምግብ ማብሰያ ምርት ከነባር አማራጮች ጎልቶ እንዲታይ ያደረገው ምን እንደሆነ መግለጽ፡፡
  2. ምርትዎ ወይም አገልግሎትዎ ከተፎካካሪዎችዎ ይልቅ እንዴት የላቁ ጥቅሞችን የበለጠ ውጤታማ በሆነ መልኩ እንደሚያስገኝ ማብራራት፡፡
  3. ከትኩረት ደንበኞችዎ ጋር የሚስማማ እና በደንበኛ ዘንድ ተቀባይነትን የሚያስገኝ ትኩረት ሳቢ ዩቪፒ ማዘጋጀት፡፡

ዓላማ

የዚህ ትምህርት ዓላማ ስራ ፈጣሪዎችን ንጹህ የማብሰያ ምርትዎን ልዩ ጥቅሞች የሚገልጽ ግልጽና ትኩረት ሳቢ ዩፒቪ እንዲያዘጋጁ መርዳት ነው፡፡ ጠንካራ ዩቪፒ በተወዳዳሪ ገበያ ላይ ምርትዎን ተለይቶ እንዲታይ ማድረግ ብቻም ሳይሆን በትክኩረት ደንበኞችዎ ዘንድ እምነትና ተአማኒነትን እንዲያጎለብቱ በማስቻል በዋናነትም ከፍተኛ የተቀባይነት ደረጃዎችን እንዲያገኙ ያስችልዎታል፡፡

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች

  1. ችግርን ከመፍትሄ ጋር ማስማማት: ዩቪፒዎ በቀጥታ የተረጋገጠ የደንበኛ ችግርን እንደሚፈታ ያረጋግጡ (ምሳ፡ ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች፣ የቤት ውስጥ አየር መበከል)፡፡
  2. ልዩነት መፍጠር: መፍትሄዎን ከተፎካካሪዎችዎ የሚለዩት ምን እንደሆኑ ለይተው ያሳውቁ—ምሳ፡ ወጪው፣ ዲዛይኑ፣ አገልግሎቱ ወይም ተደራሽነቱ፡፡
  3. የደንበኛ ጥቅሞች: ምርትዎ በሚሰጣቸው ተጨባጭ ጥቅሞች ላይ ያተኩሩ፣ ለምሳሌ፡ የተሻለ የጤና ጥቅም፣ ወጪ ቆጣቢነት፣ አመቺነት ወይም የአካባቢ ውጤት፡፡
  4. ግልጽነት እና ቀላልነት: ደንበኞችዎ የዩፒቪዎን ጥቅም ወዲያውኑ እንዲረዱት ለማስቻል ዩፒቪዎን አጭር እና ለመረዳት ቀላል አድርገው ያዘጋጁ፡፡
  5. ሙከራና ማጥራት: ዩፒቪዎ ከእጩ ደንበኞች ጋር የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ በእጩ ደንበኞች ላይ ይሞክሩት እና በሚሰጡዎት ግብረ መልስ ላይ ተመስርተው ያስተካክሉ፡፡
  6. በንጹህ ማብሰያ ላይ መተግበር: በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ ስኬታማ የሆኑ ዩፒቪዎች ምሳሌዎችን ያጥኑ፣ ለምሳሌ፡ “ለገጠር አባወራዎች ጭስን የሚቀንሱና ጊዜ የሚቆጥቡ የሶላር የምግብ ማብሰያዎች”፡፡

ምሳሌ

ኩነት: የሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ ነዋሪ ወጣት ስራ ፈጣሪ የሆነችው ሰላማዊት ከግብርና ተረፈ ምርት የሚሰሩ የተፈጥሮ ፍግ የከሰል ምርት የሚሸጥ የንግድ ስራ ለመጀመር ትፈልጋለች፡፡ የምርቷን ጥቅም በግልጽ ለመግለጽ ዩቪፒ ታዘጋጃለች፡

  1. ዋና ችግር: ብዙ ቤተሰቦች ምግብ ለማብሰል ውድና ዘላቂ ባልሆነ የማገዶ እንጨት ወይም ከሰል ላይ ጥገኛ ናቸው፡፡
  2. መፍትሄ: መልሶ ጥቅም ላይ ከሚውል የግብርና ተረፈ ምርት በአካባቢ የተሰሩ በዋጋ ተመጣጣኝ፣ ለአካባቢ ተስማሚ የተፈጥሮ ፍግ ከሰሎች፡፡
  3. ልዩ ጥቅሞች:
    • የወጪ ቁጠባዎች: ከባህላዊ ከሰል ይልቅ ዋጋው በ30% ርካሽ ነው፡፡
    • የጤና መሻሻሎች: አነስተኛ ጭስ ይፈጥራል፣ የመተንፈሻ አካል ህመሞችን ይቀንሳል፡፡
    • የአካባቢ ውጤት: የሚሰራው መልሰው ጥቅም ላይ ከሚውሉ ቁሳቁሶች ነው፣ የደን መጨፍጨፍን ይቀንሳል፡፡
    • የአካባቢ ምርት: ከአካባቢው ጥሬ እቃዎችን በመውሰድ የአካባቢው አርሷደሮችን ይደግፋል፡፡
  4. የዩቪፒ መግለጫ:
    የእኛ የተፈጥሮ ፍግ ከሰሎች በዋጋ ተመጣጣኝ፣ ለአካባቢ ተስማሚ እና ጤናማ ስለሆኑገንዘብዎን ይቆጥብልዎታል፣ ቤተሰብዎን ይከላከላል እንዲሁም ለኢትዮጵያ ዘላቂ ግብርና ድጋፍ ያደርጋል፡፡

ውጤት: የሰላማዊት ዩቪፒ ከትኩረት ደንበኞቿ ጋር የሚስማማ በመሆኑ ምርቷ ከፍተኛ ፍላጎትና ተቀባይነት እንዲያገኝ አስችሏታል፡፡ ደንበኞች የመልዕክቷን ግልጽነት እና አግባብነት ያለው መሆን አድንቀውላታል፡፡

Scroll to Top