ይህ ትምህርት ሲያበቃ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ:
- ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በስነ ሕዝብ፣ ባህሪ እና የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ልዩ ፍላጎቶች ላይ ተመስርተው መግለጽ እና መመደብ፡፡
- መፍትሄዎችን እንደ የገጠር አባወራዎች ወይም የከተማ ነዋሪዎች ያሉ የተለያዩ የደንበኛ ቡድኖችን የሚያጋጥሟቸውን ልዩ ችግሮች በሚፈታ መልኩ የማዘጋጀት አስፈላጊነትን መገንዘብ፡፡
- ከእያንዳንዱ ቡድን ልዩ መስፈርቶች ጋር የሚጣጣሙ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ለማዘጋጀት የደንበኛ ምደባ ሀሳቦችን መተግበር፡፡
ዓላማ
የዚህ ትምህርት ዓላማ ስራ ፈጣሪዎችን ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የሚለዩበትና የሚረዱበትን ክህሎቶች ማሳወቅ ነው፡፡ በደንበኛ ምደባና ማስማሚያ ላይ በማተኮር በኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ውስጥ ላሉ የተለያዩ ቡድኖች የሚስማሙ መፍትሄዎችን በማዘጋጀት ከፍተኛ የተቀባይነት ደረጃዎችን እና ከፍተኛ ማህበራዊ ውጤትን ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች
- በሥነ ህዝብ መመደብ: ደንበኞችን እንደ እድሜ፣ ጾታ፣ የገቢ ደረጃ እና የመገኛ ቦታ (ምሳ፡ ገጠር እና ከተማ) በመሳሰሉ ሁኔታዎች ላይ ተመስርተው እንዴት እንደሚመድቡ ይወቁ፡፡
- የባህሪ ግንዛቤዎች: የእንደ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ አጠቃቀም ፓተርኖች እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የመቀበል ፍላጎት ያሉ የደንበኛ ባህሪያትን ይተንትኑ፡፡
- በፍላጎቶች ላይ መሰረት ያደረገ ማስተካከያ: መፍትሄዎችዎን እንደ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች የዋጋ ተመጣጣኝነት ወይም ለአረጋውያን ተጠቃሚዎች ለአጠቃቀም ቀላልነት የመሳሰሉ የተለያዩ ቡድኖችን የሚያጋጥማቸውን ልዩ ችግሮች በሚፈታ መልኩ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚችሉ ይረዱ፡፡
- በንጹህ ማብሰያ ላይ መተግበር: ደንበኛን ያማከሉ አቀራረቦች በንጹህ የማብሰያ ዘርፉ ውስጥ እንዴት በስኬት ሊተገበሩ እንደሚችሉ የተመለከቱ ምሳሌዎችን ያጥኑ፤ ለምሳሌ፡ ለገጠር አባወራዎች ወይም ተጠጋግተው ለሚኖሩ የከተማ የአፓርታማ ነዋሪ ዘመናዊ አብሳዮች ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ ምድጃዎችን ማዘጋጀት፡፡
- ተደጋጋሚ ግብረ መልስ ማግኛዎች: አቅርቦቶችዎን ለማጥራትና ለማሻሻል ከደንበኞች ቀጣይነት ባለው መልኩ ግብረ መልስ የመሰብሰብ አስፈላጊነትን መገንዘብ፡፡
ምሳሌ
ኩነት: የአዲስ አበባ ነዋሪ ስራ ፈጣሪ የሆነው ዮሀንስ በሶላር የሚሰሩ ማብሰያዎች የሚሸጥበት የንግድ ስራ ለመጀመር ይፈልጋል፡፡ ዮሀንስ ትኩረት የሚያደርግባቸውን ደንበኞች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት እና በዚሁ መሰረት መፍትሄውን ለማዘጋጀት ደንበኛን ያማከለ ትኩረትን ተግባራዊ ያደርጋል:
- ትኩረት የሚደረግባቸውን ደንበኞች መግለጽና መመደብ:
- የገጠር አባወራዎች፡ በማገዶ እንጨት ላይ ጥገኛ የሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች፤ ለዋጋ ተመጣጣኝነትና የረጅም ጊዜ አገልግሎት ቅድሚያ ይስጡ፡፡
- የከተማ ነዋሪዎች: ኤሌክትሪክ የሚያገኙ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች፤ ለአመቺነትና ዘመናዊ ዲዛይን አጽንኦት ይስጡ፡፡
- በሴት እማወራዎች የሚመሩ ቤተሰቦች: ከፍተኛ ጊዜያቸውን ምግብ ለማብሰል የሚያውሉ ሴቶች፤ ጊዜ ቆጣቢ ባህሪያትን እና የጤና ጥቅሞችን ያብራሩ፡፡
- ልዩ ችግሮችን መረዳት:
- የገጠር አባወራዎች በከፍተኛ ወጪዎችና በንጹህ የማብሰያ አማራጮች ላይ ያላቸው ግንዛቤ ውሱን በመሆኑ የተነሳ ይቸገራሉ፡፡
- የከተማ ነዋሪዎች የቦታ ችግሮች ስለሚያጋጥሟቸው ቀልጣፋና ለመጠቀም ቀላል የሆኑ የምግብ ማብሰያዎችን ይመርጣሉ፡፡
- በሴት እማወራዎች የሚመሩ ቤተሰቦች ጭስን ለሚቀንሱና ጊዜ ቆጣቢ ለሆኑ መፍትሄዎች ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡
- መፍትሄዎችን ማዘጋጀት:
- ለገጠር አባወራዎች: አነስተኛ ወጪ የሚያስወጡ የሶላር ማብሰያዎችን ከነጻ ተከላና ስልጠና ጋር ያቅርቡ፡፡
- ለከተማ ነዋሪዎች: እንደ የሙቀት መቆጣጠሪያ ያሉ የተሻሻሉ ባህሪያት ያላቸው ቦታ የማይፈጁ፣ ውበት ያላቸው ሞዴሎችን ያዘጋጁ፡፡
- በሴት እማወራዎች ለሚመሩ ቤተሰቦች፡ ስለ ጤና ጥቅሞች የተመለከቱ የትምህርት ቁሳቁሶችን ያካቱ እንዲሁም እምነትን ለማጎልበት አውደ ጥናቶች ያዘጋጁ፡፡
- ውጤት:
ዮሀንስ የእያንዳንዱን ምድብ ልዩ ፍላጎቶች በመፍታት የደንበኛ እርካታን እና የተቀባይነት ደረጃዎችን ያሳድጋል፡፡ ተያያዥ፣ ከፍተኛ ውጤት የሚያስገኙ መፍትሄዎችን በማቅረብ መልካም ስም እያገኘ ሲሄድ የንግድ ስራው ያለማቋረጥ እያደገ ይሄዳል፡፡