Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ይህ የማረጋገጫ ዝርዝር ከልዩ የዕሴት ዕቅድ (ዩቪፒ) ትምህርቱ በተወሰዱ ዋና ዋና ንድፈ ሀሳቦች፣ መሳሪያዎችና ቴምፕሌቶች ላይ ግንዛቤዎን እና የመተግበር ችሎታዎን እንዲገመግሙ ይረዳዎታል፡፡

ክፍል 1: ዋና ዋና ንድፈ ሀሳቦች

  • ልዩ የዕሴት ዕቅድ (ዩቪፒ)ን መግለጽ እና በንጹህ የምግብ ማብሰያ ዘርፉ ውስጥ ያለውን አስፈላጊነት ማብራራት እችላለሁ፡፡
  • መፍትሄዬን ከተፎካካሪዎቼ የላቀ ለማድረግ ልዩነት መፍጠር ያለውን ሚና እረዳለሁ፡፡
  • በዩቪፒ የደንበኛ ጥቅሞችን ማብራራት ያለውን ጥቅም እገነዘባለሁ፡፡

ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 6 ነጥቦች

ክፍል 2: የመሳሪያዎችና ቴምፕሌቶች ትግበራ

  • ግልጽና ሳቢ ዩቪፒ ለማዘጋጀት የዩቪፒ ማዘጋጃ ቴምፕሌቱን ሞልቻለሁ፡፡
  • መፍትሄዬ እንዴት ከነባር አማራጮች ጋር እንደሚነጻጸር ለመለየት የደንበኛ ትንተና ቴምፕሌትን ተጠቅሜያለሁ፡፡
  • ከትኩረት ደንበኞቼ ጋር ለሚስማሙ ጥቅሞች ቅደም ተከተል ለመስጠት የደንበኛ ጥቅም ማወቂያ ቴምፕሌትን ተጠቅሜያለሁ፡፡
  • ዩቪፒዬን የዩቪፒ ሙከራ ግብረ መልስ ቅጽን በመጠቀም ሞክሬያለሁ እንዲሁም የተግባር ግንዛቤዎች ግብረ መልስ ሰብስቤያለሁ፡፡
  • ዩቪፒዬ ግልጽ፣ አጭርና ውጤት አምጪ መሆኑን ለማረጋገጥ የዩቪፒ ማጣሪያ ማረጋገጫ ዝርዝርን ተመልክቻለሁ፡፡

ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 10 ነጥቦች

ክፍል 3: የጉዳይ ጥናት ገለጻ

  • የአለምን የጉዳይ ጥናት አንብቤ እንዴት አሸናፊ ዩቪፒ እንዳዘጋጀ ተረድቻለሁ፡፡
  • የአለም ስትራቴጂዎች (ምሳ፡ የተፎካካሪ ትንተና፣ የጥቅም ማወቂያ፣ ሙከራ) እንዴት ለንግድ ስራ ሀሳቤ መረጃ እንደሚሰጥ አብራርቻለሁ፡፡
  • ለመፍትሄዬ ሳቢ ዩቪፒ ለማዘጋጀት ተመሳሳይ ስትራቴጂዎችን ለመተግበር በራስ መተማመን ይሰማኛል፡፡

ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 6 ነጥቦች

ክፍል 4: አጠቃላይ በራስ መተማመን ደረጃ

  • መፍትሄዬ የሚፈታውን ዋና ችግር ለመለየት በራስ መተማመን አለኝ፡፡
  • እንዴት የተፎካካሪዎች ትንተና ማካሄድ እና ልዩነት መፍጠርን ማብራራት እንዳለብኝ እረዳለሁ፡፡
  • በዚህ ትምህርት ውስጥ የቀረቡትን መሳሪያዎችና ቴምፕሌቶች ያወቅኳቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ውጤታማ በሆነ መልኩ ልጠቀምባቸው እችላለሁ፡፡
  • ዩቪፒዬን ከገበያና የግንኙነት ጥረቶቼ ጋር ወደማቀናጅበት ቀጣዩ ደረጃ ለማለፍ ዝግጁ ነኝ፡፡

ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 8 ነጥቦች

የመጨረሻ ውጤት አሰጣጥና ግብረ መልስ

  • የሁሉንም ክፍሎች ውጤቶችዎን ይደምሩ፡፡
  • ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 30 ነጥቦች

የውጤቶች ትንተና:

  • ከ25–30 ነጥቦች: በጣም ጥሩ! ስለ ዩቪፒ ዝግጅት ጠንካራ ግንዛቤ ስላገኙ እነዚህን ክህሎቶች በራስ መተማመን ለመተግበር ዝግጁ ነዎት፡፡
  • ከ15–24 ነጥቦች: ጥሩ! አብዛኞቹን ንድፈ ሀሳቦች የተገነዘቡ ቢሆንም ልዩ የመሻሻያ መስኮችን መለስ ብለው ማየት ያስፈልግዎታል፡፡

ከ15 ነጥቦች በታች: መሻሻል ያለበት፡፡ የትምህርቱን ቁሳቁሶች፣ ተያያዥ ጥያቄዎች በድጋሚ ማንበብ እና መሳሪያዎቹን እና ቴምፕሌቶቹን በመጠቀም እንደገና መለማመድ አለብዎት፡፡

Scroll to Top