Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ይህ የማረጋገጫ ዝርዝር ደንበኛን ካማከለ ትኩረት ትምህርቱ በተወሰዱ ዋና ዋና ንድፈ ሀሳቦች፣ መሳሪያዎችና ቴምፕሌቶች  ላይ ግንዛቤዎን እና የመተግበር ችሎታዎን እንዲገመግሙ ይረዳዎታል፡፡

ክፍል 1: ዋና ዋና ንድፈ ሀሳቦች

  • ደንበኛ ተኮር ትኩረትን መግለጽ እና በንጹህ የምግብ ማብሰያ ዘርፉ ውስጥ ያለውን አስፈላጊነት ማብራራት እችላለሁ፡፡
  • የተለያዩ የትኩረት ቡድኖችን በመለየት ረገድ የደንበኛ ምደባ ያለውን ሚና እረዳለሁ፡፡
  • መፍትሄዎችን ከተለያዩ የደንበኛ ምድቦች ልዩ ፍላጎቶች ጋር ማስማማት የሚሰጠውን ጠቀሜታ እገነዘባለሁ፡፡

ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 6 ነጥቦች

ክፍል 2: የመሳሪያዎችና ቴምፕሌቶች ትግበራ

  • የደንበኛ ምደባ ቴምፕሌቱን ሞልቻለሁ እንዲሁም ግልጽ የደንበኛ ቡድኖችን ለይቻለሁ፡፡
  • የማንነት መግለጫ ቴምፕሌቱን የትኩረት ደንበኞቼን ዝርዝር መግለጫዎች ለማዘጋጀት ተጠቅሜዋለሁ፡፡
  • የደንበኛ ፍላጎቶች ትንተና ቴምፕሌቱን ለችግሮችና ቅደም ተከተሎች ቅደም ተከተል ለመስጠት ተጠቅሜበታለሁ፡፡
  • እሳቤዎቼን ለማረጋገጥ የግብረ መልስ ስብሰባ ቴምፕሌቱን ተጠቅሜ ግብረ መልስ ሰብስቤያለሁ፡፡
  • የመፍትሄ ዝግጅት ማረጋገጫ ቅጹን መፍትሄዎቼ ከደንበኛ ፍላጎቶች ጋር የሚስማሙ መሆኑን ለማረጋገጥ ተመልክቼዋለሁ፡፡

ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 10 ነጥቦች

ክፍል 3: የጉዳይ ጥናት ገለጻ

  • የመስፍንን ጉዳይ ታሪክ አንብቤ የደንበኛ ተኮር መርሆዎችን እንዴት እንደተገበረ ተረድቻለሁ፡፡ 
  • የመስፍን ስትራቴጂዎች (ምሳ፡ ምደባ፣ ግብረ መልስ፣ መደጋገም) እንዴት ለእኔ የንግድ ስራ ሀሳብ መረጃ ሊሰጡ እንደሚችሉ አብራርቻለሁ፡፡
  • የደንበኛ ፍላጎቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመፍታት ተመሳሳይ ስትራቴጂዎችን ለመተግበር በራስ መተማመን ይሰማኛል፡፡

ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 6 ነጥቦች

ክፍል 4: አጠቃላይ በራስ መተማመን ደረጃ

  • የትኩረት ደንበኞቼን በስነ ህዝብ፣ ባህሪ እና ፍላጎቶች ላይ ተመስርቼ ለመግለጽና ለመመደብ በራስ መተማመን ይሰማኛል፡፡
  • የደንበኛ ችግሮችን እንዴት መተንተን እና በዚሁ መሰረት መፍትሄዎችን ማስማማት እንዳለብኝ እረዳለሁ፡፡
  • በዚህ ትምህርት ውስጥ የቀረቡትን መሳሪያዎችና ቴምፕሌቶች ያወቅኳቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ውጤታማ በሆነ መልኩ ልጠቀምባቸው እችላለሁ፡፡
  • የራሴን የንግድ ስራ ሀሳብ ወደማዘጋጅበት ቀጣዩ ደረጃ ለማለፍ ዝግጁ ነኝ (ምሳ፡ የንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ፣ የመፍትሄ ዲዛይን)፡፡

ለራስዎ ውጤት ይስጡ: ለእያንዳንዱ የተረጋገጠ ጥያቄ 2 ነጥቦች ይስጡ፡፡
ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 8 ነጥቦች

የመጨረሻ ውጤት አሰጣጥና ግብረ መልስ

  • የሁሉንም ክፍሎች ውጤቶችዎን ይደምሩ፡፡
  • ጠቅላላ ሊሰጥ የሚችል ውጤት: 30 ነጥቦች

የውጤቶች ትንተና:

  • ከ25–30 ነጥቦች: በጣም ጥሩ! ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ጠንካራ ግንዛቤ ስላገኙ እነዚህን ክህሎቶች በራስ መተማመን ለመተግበር ዝግጁ ነዎት፡፡
  • ከ15–24 ነጥቦች: ጥሩ! አብዛኞቹን ንድፈ ሀሳቦች የተገነዘቡ ቢሆንም ልዩ የመሻሻያ መስኮችን መለስ ብለው ማየት ያስፈልግዎታል፡፡
  • ከ15 ነጥቦች በታች: መሻሻል ያለበት፡፡ የትምህርቱን ቁሳቁሶች፣ ተያያዥ ጥያቄዎች በድጋሚ ማንበብ እና መሳሪያዎቹን እና ቴምፕሌቶቹን በመጠቀም እንደገና መለማመድ አለብዎት፡፡

ዋና ዋና የትምህርቱ ነጥቦች

  1. ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ፍቺ/ትርጉም:
    • ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ማለት ውጤት አምጪ መፍትሄዎችን ለማዘጋጀት የትኩረት ደንበኞችዎን ልዩ ፍላጎቶች መረዳት እና መፍታት ነው፡፡
  2. የምደባ ጥቅም:
    • ደንበኞችን በሥነ ህዝብ፣ በባህሪና ፍላጎቶች መመደብ መፍትሄዎች ለተለያዩ ቡድኖች አግባብነት ያላቸው እና ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
  3. መፍትሄዎችን ማስማማት:
    • ምርቶች ወይም አገልግሎቶችን የእያንዳንዱን ምድብ ልዩ ፍላጎቶች በሚፈታ መልኩ ማዘጋጀት የተቀባይነት ደረጃዎችን እና የደንበኛ እርካታን ያሳድጋል፡፡
  4. መሳሪያዎች እና ቴምፕሌቶች:
    • የደንበኛ ምደባ ቴምፕሌትን፣ የማንነት መግለጫ ዝግጅት ቴምፕሌትን፣ የደንበኞች ፍላጎቶች ትንተና ቴምፕሌትን፣ የግብረ መልስ ስብሰባ ቴምፕሌትን፣ እና የመፍትሄ ዝግጅት ማረጋገጫ ዝርዝርን የደንበኛ ፍላጎቶችን በብልሀት ለመለየትና ለመፍታት ይጠቀሙባቸው፡፡
  5. ተደጋጋሚ ግብረ መልስ ማግኛ:
    • መፍትሄዎን ለማጥራት እና እያደጉ ከሚሄዱ ፍላጎቶች ጋር ተስማምተው ለመቀጠል ቀጣይነት ባለው መልኩ ግብረ መልስ ይሰብስቡ እና ያካቱ፡፡
  6. የጉዳይ ጥናት ግንዛቤዎች:
    • እምነትን ለማጎልበትና ስኬትን ለማስቀጠል ከመስፍን ደንበኞችን የመመደብ፣ እሳቤዎችን የማረጋገጥ እና በግብረ መልስ ላይ ተመስርቶ የመደጋገም ምሳሌ ይማሩ፡፡
  7. በንጹህ ማብሰያ ላይ መተግበር:
    • በዋጋ ተመጣጣኝ፣ ተደራሽ እና ውጤት አምጪ መፍትሄዎችን ለገጠር አባወራዎች፣ የከተማ ነዋሪዎች፣ በሴት እማወራ የሚመሩ ቤተሰቦች እና ሌሎች ዋና ዋና ምድቦች ለማዘጋጀት ደንበኛን ያማከለ መርሆዎችን ይተግብሩ፡፡
Scroll to Top