ዓላማ: የጉዳይ ጥናቱን ምሳሌ ይግለጹ እና ትምህርቱን በራስዎ ስራ ላይ ይተግብሩ፡፡
መመሪያዎች
- የሰላማዊት ከበደን የጉዳይ ጥናት ተመልሰው ይመልከቱ፡፡
- የሚከተሉትን የገለጻ ጥያቄዎች ይመልሱ:
- ሰላማዊት ስለ ደንበኛ ችግሮች በተመለከተ ያሏትን እሳቤዎች ያረጋገጠችው እንዴት ነበር?
- መፍትሄዋ ደንበኛን ያማከለ መሆኑን ለማረጋገጥ የተጠቀመቻቸው ስትራቴጂዎች ምን ነበሩ?
- ከስትራቴጂዎቿ መካከል አንዱን እንዴት በንግድ ስራ ሀሳብዎ ላይ ሊተገብሩ ይችላሉ?
- ገለጻዎን የሚያጠቃልል አጭር አንቀጽ ይጻፉ፡፡
የግምገማ መስፈርት
- የገለጻ ጥልቀት: መልሶቹ ጥልቅ አስተሳሰብን እና ከጉዳይ ጥናቱ ጋር ያሉ ግንኙነቶችን ይገልጻሉ (6 ነጥቦች)፡፡
- በራስ ስራ ላይ መተግበር: ከጉዳይ ጥናቱ የተወሰደ አንድ ስትራቴጂ በንግድ ስራ ሀሰብዎ ላይ በግልጽ መተግበር (4 ነጥቦች)፡፡
- ግልጽነትና አወቃቀር: የጽሁፉ ግልጽ፣ አጭር እና በአግባቡ የተደራጀ መሆን (2 ነጥቦች)፡፡
ጠቅላላ ውጤት: 12 ነጥቦች
የተመደበ ሰዓት: 20 ደቂቃዎች