እነዚህ ቴምፕሌቶች የተዘጋጁት ስራ ፈጣሪዎችን የገቢ ማግኛ መንገዶችን እንዲለዩ፣ ወጪዎችን እንዲተነትኑ እና የገንዘብ ዘላቂነትን እንዲያረጋግጡ ለመርዳት ነው፡፡ እነዚህ ምንጮች አዋጭ የንግድ ስራ ሞዴል ለማዘጋጀት በሚያካሂዷቸው የዕቅድ ዝግጅትና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ላይ በመመሪያነት ያገለግሉዎታል፡፡
-
የገቢ ማግኛ መንገዶችን መለያ ቴምፕሌት
ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎችን ለንግድ ስራቸው ሊሳኩ የሚችሉ የገቢ ምንጮችን በብልሀት እንዲለዩ ይረዳቸዋል፡፡
ቴምፕሌት: የገቢ ማግኛ መንገዶች ማዕቀፍ
የንግድ ድርጅት ስም: ____________________________
ምርት/አገልግሎት: ___________________________
ምሳሌ
|
የገቢ ማግኛ መንገድ |
ዝርዝር |
የትኩረት ደንበኞች |
የሚገመት ወርሀዊ ገቢ |
|
ቀጥተኛ ሽያጮች |
ምርቶችን በቀጥታ ለደንበኞች መሸጥ |
የከተማ ቤተሰቦች |
ብር 500 |
|
ሽርክናዎች |
ከኤንጂኦዎች ወይም የመንግስት ፕሮግራሞች ጋር በትብብር መስራት |
አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች |
ብር 300 |
|
የአገልግሎት ክፍያዎች |
ጥገና ወይም ስልጠና ማቅረብ |
ድጋፍ የሚፈልጉ ደንበኞች |
ብር 100 |
መመሪያዎች:
- ሁሉንም ሊሳኩ የሚችሉ የገቢ ማግኛ መንገዶች ይዘርዝሩ (ምሳ፡ ቀጥተኛ ሽያጮች፣ ሽርክናዎች፣ ትእዛዞች)፡፡
- እያንዳንዱን መንገድ ይግለጹ እና የትኩረት ደንበኞችዎን ይለዩ፡፡
- ገገበያ ጥናት ወይም እሳቤዎች ላይ ተመስርተው የእያንዳንዱን የገቢ ማግኛ መንገድ ወርሀዊ ገቢ ይገምቱ፡፡
መመሪያ: ከንግድ ስራ ሞዴልዎ እና የደንበኞች ፍላጎት ጋር የሚስማሙ የገቢ ማግኛ መንገዶችን በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ ይህን ማዕቀፍ ይጠቀሙ፡፡
-
የወጪ መዋቅር ትንተና ቴምፕሌት
ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎችን የንግድ ስራቸውን ለመጀመር እና ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን እንዲመድቡና እንዲገምቱ ይረዳቸዋል፡፡
ቴምፕሌት: የወጪ መዋቅር ስሌት
የንግድ ድርጅት ስም: ____________________________
ምርት/አገልግሎት: ___________________________
ምሳሌ
|
የወጪ አይነት |
ስርዝር |
የሚገመት ወርሀዊ ወጪ |
|
ቀጥተኛ ወጪዎች |
ኪራይ፣ ደመወዝ፣ መሳሪያዎች |
ብር 400 |
|
ተለዋዋጭ ወጪዎች |
ጥሬ ዕቃዎች፣ ማሸጊያ፣ ትራንስፖርት |
ብር 200 |
|
የመጀመሪያ ኢንቨስትመንት |
የመጀመሪያ ሙከራ፣ ማረጋገጫዎች፣ የንብረት ቆጠራ |
ብር 1,000 (የአንድ ጊዜ) |
|
ገበያና ማከፋፈያ |
ማስታወቂያ፣ የኦንላይን ፕላትፎርሞች፣ ሎጅስቲክስ |
ብር 150 |
መመሪያዎች:
- ቋሚ ወጪዎችን (ምሳ፡ ኪራይ፣ ደመወዝ) እና ተለዋዋጪ ወጪዎችን (ምሳ፡ ጥሬ እቃዎች) መለየት፡፡
- የንግድ ስራዎን ለመጀመር የሚያስፈልጉ የመጀመሪያ ኢንቨስትመንት ወጪዎችን ያካቱ፡፡
- ጠቅላላ ወጪዎችን ለማስላት ወርሀዊ ወጪዎችን ይገምቱ፡፡
መመሪያ: የወጪ መዋቅርዎን ለመረዳት እና ምን ላይ ወጪዎን መቀነስ እንዳለብዎ ለመለየት ይህን ስሌት ይጠቀሙ፡፡
-
የገቢ ማግኛ ነጥብ ትንተና ቴምፕሌት
ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎችን የንግድ ስራቸው መቼ ትርፍ ማግኘት እንደሚጀምር ለመወሰን የገቢ ማግኛ ነጥባቸውን እንዲያሰሉ ይረዳቸዋል፡፡
ቴምፕሌት: የገቢ ማግኛ ነጥብ ትንተና
የንግድ ድርጅት ስም: ____________________________
ምርት/አገልግሎት: ___________________________
ምሳሌ
|
ተለዋዋጭ |
ዋጋ |
|
ቋሚ ወጪዎች (ወርሀዊ) |
ብር 600 |
|
ተለዋዋጭ ወጪዎች በምርት |
ብር 10 |
|
የመሸጫ ዋጋ በምርት |
ብር 25 |
|
የገቢ ማግኛ ነጥብ (በምርቶች) |
ቋሚ ወጪዎች ÷ (የመሸጫ ዋጋ – ተለዋዋጭ ወጪዎች) = ___ ምርቶች |
ምሳሌ ስሌት:
- ቋሚ ወጪዎች: ብረት 600
- ተለዋዋጭ ወጪዎች በምርት: ብር 10
- የመሸጫ ዋጋ በምርት: ብር 25
- የገቢ ማግኛ ነጥብ: ብር 600 ÷ (ብር 25 – ብር 10) = 40 ምርቶች
መመሪያዎች:
- የግብአት ቋሚ ወጪዎች፣ ተለዋዋጭ ወጪዎች በምርት እና የመሸጫ ዋጋ፡፡
- ወጪዎችዎን ለመሸፈን ምን ያክል ምርቶች መሸጥ እንዳለብዎ ለመወሰን የገቢ ማግኛ ነጥብዎን ያስሉ፡፡
መመሪያ: ተጨባጭ የሽያጭ ኢላማዎች ለማዘጋጀትና ትርፋማነትን ለማረጋገጥ ይህን ትንተና ይጠቀሙ፡፡
-
የሽርክና እድል ማወቂያ ቴምፕሌት
ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎችን ገቢን ለማሳደግና ወጪዎችን ለመቀነስ ለ.ሳኩ የሚችሉ ትብብሮችን እንዲለዩና እንዲገመግሙ ይረዳቸዋል፡፡
ቴምፕሌት: የትብብር እድል ማወቂያ
ምሳሌቴ
|
ሊሆን የሚችል ተባባሪ |
የትብብር አይነት |
ለንግድ ስራዎ የሚያስገኘው ጥቅም |
የድርጊት ደረጃዎች |
|
የአካባቢ ኤንጂኦ |
አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ለምርት ወጪዎች ድጎማ ማድረግ |
ተደራሽንነትን ማሳደግ፣ የደንበኞች መሰረትን ማስፋት |
የኤንጂኦ ተወካዮችን ማናገር፣ የትብብር ሀሳብ ማቅረብ |
|
የማይክሮፋይናንስ ተቋም |
ለደንበኞች የገንዘብ ድጋፍ አማራጮችን ማቅረብ |
ከፍተኛ የተቀባይነት ደረጃዎች፣ ተደጋጋሚ ገቢ |
የትብብር ፕሮፖዛል ረቂቅ ማዘጋጀት፣ የስብሰባዎች ቀጠሮ መያዝ |
|
የመንግስት ፕሮግራም |
ምርቶችን በገጠር አካባቢዎች ማከፋፈል |
ለአዲስ ገበያዎች ተደራሽ መሆን፣ ተአማኒነት |
ፕሮግራሞችን ማጥናት፣ አካታችነትን መተግበር |
መመሪያዎች:
- ሊሳኩ የሚችሉ ትብብሮችን ይዘርዝሩ (ምሳ፡ ኤንጂኦዎች፣ የመንግስት ፕሮግራሞች፣ የማይክሮፋይናንስ ተቋማት)፡፡
- የትብብሩን አይነት እና ጥቅሞቹን ይግለጹ፡፡
- ትብብሩን መጀመሪያ የድርጊት ደረጃዎችን ያብራሩ፡፡
መመሪያ: ከተልእኮዎ ጋር የሚስማሙና ተደራሽነትዎን የሚያሰፉ ትብብሮች ላይ ያተኩሩ፡፡
-
የገንዘብ ዘላቂነት ማረጋገጫ ዝርዝር
ይህ የማረጋገጫ ዝርዝር ስራ ፈጣሪዎችን ሁሉንም የገቢ ማግኛ መንገዶችና የወጪ መዋቅር ዋና ዋና ክፍሎች ከግምት ውስጥ እንዳስገቡ እንዲያረጋግጡ ይረዳቸዋል፡፡
ቴምፕሌት: የገንዘብ ዘላቂነት ማረጋገጫ ዝርዝር
የንግድ ድርጅት ስም: ____________________________
- ቢያንስ ከ2-3 ተጨባጭ የገቢ ማግኛ መንገዶች ተለይተዋል፡፡
- የእያንዳንዱ የገቢ ማግኛ መንገድ የተገመተ ወርሀዊ ገቢ፡፡
- ቋሚና ተለዋዋጭ ወጪዎች በትክክል ተመድበዋል፡፡
- ትርፋማነትን ለመወሰን የገቢ ማግኛ ነጥቡ ተሰልቷል፡፡
- ገቢን ለማሳደግ ወይም ወጪዎችን ለመቀነስ ሊሳኩ የሚችሉ ትብብሮች ተጠንተዋል፡፡
- ጠቅላላ ገቢ በጊዜ ሂደት ከጠቅላላ ወጪዎች እንደሚበልጥ ተረጋግጧል፡፡
- የገበያ ጥናትን መሰረት በማድረግ እሳቤዎች ተገምግመው ተስተካክለዋል፡፡