Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ቴምፕሌቱ የተዘጋጀው ስራ ፈጣሪዎችን ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ንድፈ ሀሳቦችን ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲተገብሩ ለመርዳት ነው፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች ትኩረት የሚደረግባቸውን ደንበኞች ለመመደብ፣ ልዩ ፍላጎቶቻቸውን ለመረዳት እና መፍትሄዎችን በዚሁ መሰረት ለማዘጋጀት ያግዛሉ፡፡

  1. የደንበኛ ምደባ ቴምፕሌት

ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎችን ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በሥነ ህዝብ፣ ባህሪና ፍላጎቶች ላይ ተመስርተው እንዲመድቡ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የደንበኛ ምደባ ማዕቀፍ

የንግድ ድርጅት ስም: ____________________________
ምርት/አገልግሎት: ___________________________

 

ምሳሌ

ምድብ

ሥነ ህዝብ

ባህሪ

ልዩ ፍላጎቶች/ችግሮች

የተዘጋጀ መፍትሄ

የገጠር አባወራዎች

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች፣ አርሷደሮች

በማገዶ እንጨት ላይ ጥገኛ መሆን፣ የግንዛቤ ውሱንነት

ከፍተኛ ወጪዎች፣ የንጹህ ማብሰያ አማራጮች አለመኖር

በዋጋ ተመጣጣኝ የተፈጥሮ ፍግ ምድጃዎች፣ ነጻ ስልጠና

 

መመሪያዎች:

  • የደንበኛ ምድቦችዎን ለመግለጽ እያንዳንዱን ረድፍ ይሙሉ፡፡
  • ይህን ማእቀፍ መፍትሄዎ እንዴት ለእያንዳንዱ ቡድን ልዩ ፍላጎቶች መፍትሄ እንደሚሰጥ ለማሰብ ይጠቀሙበት፡፡
  1. የደንበኛ ፍላጎቶች ትንተና ቴምፕሌት

ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎችን የደንበኛ ቡድኖች የተለያዩ ልዩ ፍላጎቶችን ለመለየትና ቅደም ተከተል ለመስጠት ይረዳቸዋል፡፡ 

ቴምፕሌት: የደንበኛ ፍላጎቶች ትንተና

የደንበኛ ምድብ: ____________________________
ቦታ: ___________________________________

 

ምሳሌ

ፍላጎት/ችግር

ለምን ችግር እንደሚፈጥር

ወቅታዊ መፍትሄዎች (ካሉ)

የማሻሻያ ዕድል

የዋጋ ተመጣጣኝነት

ቤተሰቦች ለአካባቢ ተስማሚ አማራጮችን የመግዛት አቅም የላቸውም

ያሉት የገንዘብ ማግኛ አማራጮች ውሱን ናቸው

በጊዜ የተከፋፈሉ የክፍያ ዕቅዶችን ማቅረብ

 

መመሪያዎች:

  • በአንድ ጊዜ አንድ የደንበኛ ምድብ ይምረጡ፡፡
  • ዋና ዋና ፍላጎቶች ወይም ችግሮችን ይዘርዝሩና ለምን እነዚህ ችግር እንደሚፈጥሩ ያብራሩ፡፡
  • ወቅታዊ መፍትሄዎችን ይተንትኑ እና እነዚህን የማሻሻያ መንገዶችን ይጠቀሙ፡፡

 

  1. ግብረ መልስ መሰብሰቢያ ቴምፕሌት

ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎችን አቅርቦቶቻቸውን ለማጥራት ከደንበኞች ግብረ መልስ እንዲሰበስቡና እንዲያደራጁ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የደንበኛ ግብረ መልስ ቅጽ

የደንበኛ ስም: ____________________________
ምድብ: _________________________________
ቀን: ___________________________________

 

ምሳሌ

ጥያቄ

መልስ

ግንዛቤዎች/ድርጊቶች

በምግብ ማብሰያዎች ላይ የሚጋጥሙዎ ችግሮች ምንድን ናቸው?

   

በአሁኑ ምድጃዎ ምን ያክል ረክተዋል? (ከ1–5 መለኪያ)

   

 

መመሪያዎች:

  • ይህን ቅጽ በቃለ መጠይቆች፣ የዳሰሳ ጥናቶች ወይም የሚከራ ክፍለ ጊዜዎች ወቅት ይጠቀሙት፡፡
  • ምላሾችን ይመዝግቡ እና ምርትዎን/አገልግሎትዎን ለማሻሻል የተግባር ግንዛቤዎችን ያስተውሉ፡፡

 

  1. የማንነት መገለጫ ዝግጅት ቴምፕሌት

ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎችን ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ዝርዝር የደንበኛ ገጽታዎችን ለማዘጋጀት ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የደንበኛ ማንነት መረጃ

የማንነት ስም: ____________________________
ምድብ: ________________________________
ቦታ: _______________________________

 

ምሳሌ

ባህሪ

ዝርዝሮች

ዕድሜ

 

ጾታ

 

የገቢ ደረጃ

 

ስራ

 

የምግብ ማብሰያ ልማዶች

 

ዋና ዋና ችግሮች

 

ተመራጭ የመገናኛ ዘዴዎች

 

ተነሳሽነቶች

 

የመቀበል እንቅፋቶች

 

 

የማንነት ምሳሌ:

  • ስም: ሰላም (የገጠር የቤት እመቤት)
  • ዕድሜ: 35
  • የገቢ ደረጃ: አነስተኛ
  • የምግብ ማብሰያ ልማዶች: በየዕለቱ የማገዶ እንጨት ትጠቀማለች፣ የማገዶ እንጨት ለመሰብሰብ 3 ሰዓቶችን ታጠፋለች፡፡
  • ዋና ዋና ችግሮች፡ ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች፣ ከጭስ ጋር ተያያዥ የጤና ችግሮች፡፡
  • ተነሳሽነቶች: ገንዘብ መቆጠብ፣ የቤተሰብን ጤና መከላከል፡፡
  • እንቅፋቶች: ስለ አማራጮች ግንዛቤ አለመኖር፣ የዋጋ ተመጣጣኝነት ችግሮች፡፡

መመሪያዎች:

  • የተለያዩ የደንበኛ ምድቦችን የሚወክሉ ከ2–3 የማንነት መገለጫዎች ያዘጋጁ፡፡
  • እነዚህን የማንነት መገለጫዎች ለምርት ዲዛይንዎ እና የገበያ ስትራቴጂዎችዎ በመመሪያነት ይጠቀሙት፡፡
  1. የመፍትሄ ማዘጋጃ ማረጋገጫ ዝርዝር

ይህ የማረጋገጫ ዝርዝር ስራ ፈጣሪዎችን መፍትሄዎቻቸውን የእያንዳንዱን የደንበኛ ምድብ ልዩ ፍላጎቶች በሚፈታ መልኩ እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የመፍትሄ ማዘጋጃ ማረጋገጫ ዝርዝር

የመፍትሄ ስም: ____________________________
የትኩረት ምድብ: ___________________________

  • ለትኩረት ምድብ የተደረጉ ቃለ መጠይቆች/የዳሰሳ ጥናቶች፡፡
  • የተለዩ 3 ዋና ዋና ተግዳሮቶች ወይም ችግሮች፡፡
  • እነዚህን ችግሮች በቀጥታ እንዲፈቱ የተዘጋጁ ባህሪያት፡፡
  • በአነስተኛ የደንበኛ ቡድኖች ላይ የተሞከረ መፍትሄ፡፡
  • የተሰበሰበ ግብረ መልስና የተደረጉ አስፈላጊ ማሻሻያዎች፡፡
  • አነስተኛ ገቢ ላላቸው ምድቦች የተረጋገጠ የዋጋ ተመጣጣኝነት (ተግባራዊ ከተደረገ)፡፡
  • ለውስብስብ መፍትሄዎች የተካተቱ የትምህርት ቁሳቁሶች ወይም ስልጠና፡፡
  • ተደራሽነትን ለማሻሻል ከአካባቢ ድርጅቶች ጋር የተደረገ ትብብር፡፡

መመሪያዎች:

  • ይህን የማረጋገጫ ዝርዝር መፍትሄዎ ለእያንዳንዱ ምድብ በተሟላ ሁኔታ መዘጋጀቱን ለማረጋገጥ ይጠቀሙት፡፡
  • እያንዳንዱ ዝርዝር ከተረጋገጠ በኋላ እንደተጠናቀቀ ምልክት ያድርጉበት፡፡
Scroll to Top