Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ኢትዮጵያ ውስጥ በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ላይ ለሚሰማሩ አዳዲስ ጥራ ፈጣሪዎች ድጋፍ ለማድረግ የሚከተሉት መሳሪያዎች እና ቴምፕሌቶች ውጤታማ ችግርን መለየትን እንዲያመቻቹ ታስበው ተዘጋጅተዋል፡፡ እነዚህ የመረጃ ምንጮች ተግባር ላይ የሚውሉ፣ ለአጠቃቀም ቀላል እና ትኩረት ከሚደረግባቸው ደንበኞች ልዩ ተግዳሮቶች ጋር ተያይዘው የተዘጋጁ ናቸው፡፡

  1. ችግርን መለያ ዎርክሺት

ይህ ወርክሺት ሥራ ፈጣሪዎችን በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ ያሉ የደንበኛ ችግሮችን በብልሀት እንዲለዩ እና እንዲያረጋግጡ ያግዛቸዋል፡፡

ቴምሌት: ችግርን መለያ ዎርክሺት

የሥራ ፈጣሪ  ስም: ____________________________

የንግድ ሥራ ሀሳብ: _______________________________

ደረጃ 1: ዋና ዋና ችግሮችን መለየት

በባህላዊ የማብሰያ ዘዴዎች ላይ ጥገኛ የሆኑ ቤተሰቦችን የሚያጋጥሟቸውን ዋና ዋና ችግሮች ይዘርዝሩ፡፡ እንደ ወጪ፣ ጤና፣ አካባቢ እና ተደራሽነት የመሳሰሉ ሁኔታዎችን ያስተውሉ፡፡

ምሳሌ:

ዋና ችግር

ዝርዝር

በደንበኞች ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ

በባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ መሆን

የቤተሰቦች በውድና ዘላቂነት የሌለው የማገዶ እንጨት ወይም ከሰል ላይ ጥገኛ መሆን፡፡

ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች፣ የደን መጨፍጨፍ

 

ደረጃ 2: ችግሮቹን ማረጋገጥ

ይህን ክፍል የተለዩት ችግሮች እውነተኛ እና ትኩረት ለተደረገባቸው ደንበኞች አግባብነት ያላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ይጠቀሙ፡፡

ምሳሌ:

የማረጋገጫ ዘዴ

እርስዎ ምን አደረጉ

የደንበኛ ግብረ መልስ/ሀሳቦች

ለቤተሰቦች ቃለ መጠይቆችን ማድረግ

ስለ የምግብ ማብሰል ልማዶችዎ በተመለከተ 10 የአዲስ አበባ ነዋሪ ቤተሰቦችን አነጋግረዋል፡፡

ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎችን እና የጭስ ጭግሮችን ገልጸውልዎታል፡፡

 

የችግሩ ማረጋገጫ ዳሰሳ ጥናት/የቃለ መጠይቅ ጥያቄ

ይህ መጠይቅ የተዘጋጀው ሥራ ፈጣሪዎችን ከእጩ ደንበኞች ሀሳቦችን እንዲሰበስቡ እና የተለዩት ችግሮች በንጹህ የማብሰያ ዘርፉ ውስጥ እንደሚያጋጥሙ ለማረጋገጥ እንዲረዳቸው ነው፡፡ ጥያቄዎቹ የተዘጋጁት ችግሮችን፣ ምርጫዎችን እና ከባህላዊ የምግብ ማብሰያ አሰራሮች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ባህሪያትን ለማወቅ እንዲያስችሉ ተደርገው ነው፡፡

ክፍል 1: ወቅታዊ የምግብ ማብሰያ አሰራሮች

  1. በአሁኑ ወቅት ምግብ ለማብሰል ምን አይነት ምድጃ ወይም ማገዶ ይጠቀማሉ?
    • አማራጮች: እንጨት፣ ከሰል፣ ናፍጣ፣ ጋዝ፣ ኤሌክትሪክ፣ ሶላር፣ ሌላ (እባክዎ ይግለጹ)፡፡ 
    • ዓላማ: ቤተሰቦች የሚጠቀሙትን የመጀመሪያ የኢነርጂ ምንጭ መረዳት፡፡
  2. በየወሩ ለምግብ ማብሰያ ነዳጅ ወይም የማገዶ እንጨት ምን ያክል ወጪ ያወጣሉ?
    • ዓላማ: ከባህላዊ ማገዶዎች ጋር ተያያዥ የሆኑ የዋጋ ተመጣጣኝነት ችግሮችን እና የገንዘብ ጫናዎችን ማጥናት፡፡
  3. የአሁኑ የማብሰያ ማገዶዎን ማግኘት ለእርስዎ ምን ያክል ቀላል ወይስ ከባድ ነው?
    • አማራጮች: በጣም ቀላል፣ ቀላል፣ ቀላልም ከባድም ያልሆነ፣ ከባድ፣ በጣም ከባድ፡፡
    • ዓላማ: የተደራሽነት ችግሮችን ለይቶ ማወቅ፤ ለምሳሌ፡ ርቀት ወይም የኢነርጂ ምንጮች መገኘት፡፡

 

ክፍል 2: የጤናና አካባቢ ስጋቶች

  1. እርስዎ ወይም የትኛውም የቤተሰብዎ አባል ከማብሰያ በሚወጣ ጭስ የተነሳ የጤና ችግሮች (ምሳ፡ የመተንፈሻ አካል ችግሮች) አጋጥመዋችኋል?
    • አማራጮች: አዎ፣ አይ፣ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡
    • ዓላማ: በቤት ውስጥ አየር መበከል ምክንያት የሚመጡ የጤና ስጋቶችን ማረጋገጥ፡፡
  2. የአሁን የምግብ ማብሰያ ዘዴዎ በአካባቢ ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል ብለው ያስባሉ (ምሳ፡ የደን መጨፍጨፍ፣ ብክለት)፡፡?
    • አማራጮች: አዎ፣ አይ፣ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡
    • ዓላማ: የአካባቢ መዘዞች ግንዛቤን እና ንጹህ አማራጮችን የመቀበል ፍላጎትን መለካት፡፡

ክፍል 3: ተግዳሮቶችና ችግሮች

  1. በአሁኑ የምግብ ማብሰያ ዘዴዎ ላይ የሚያጋጥምዎት ትልቁ ተግዳሮት ምንድን ነው?
    • ለሀሳብ ክፍት ምላሽ፡፡
    • ዓላማ: እንደ ወጪ፣ ጊዜ ወይም የጤና ስጋቶች ያሉ ልዩ ችግሮችን ማወቅ፡፡
  2. እርስዎ ወይም የቤተሰብዎ አባል በየሳምንቱ የማገዶ እንጨት ለመሰብሰብ ወይም ነዳጅ ለመግዛት ምን ያክል ጊዜ ታጠፋላችሁ?
    • ዓላማ: ከባህላዊ የምግብ ማብሰያ ዘዴዎች ጋር ተያያዥ የጊዜ ጫናን በአሀዝ ማስቀመጥ፡፡
  3. ንጹህ ወይም የበለጠ ውጤታማ የሆነ የምግብ ማብሰያ ምርት ዋጋው ተመጣጣኝ ቢሆን ወደዚህ የመቀየር ፍላጎት አለዎ?
    • አማራጮች: አዎ፣ አይ፣ ምናልባት፡፡
    • ዓላማ: ንጹህ የማብሰያ ቴክኖሎጂዎችን የመቀበል ዝግጁነትን ማጥናት፡፡

ክፍል 4: ግንዛቤ እና ምርጫዎች

  1. በማህበረሰብዎ ውስጥ ስለሚገኙ ስለ የትኛውም ንጹህ ወይም አማራጭ የምግብ ማብሰያ ምርቶች ያውቃሉ?
    • አማራጮች: አዎ፣ አይ፡፡ አዎ ካሉ እባክዎ ስለ እነዚህ ምን እንደሚያውቁ ይግለጹልኝ፡፡
    • ዓላማ: የግንዛቤ ደረጃዎችን እና ስለ ንጹህ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ያሉ የእውቀት ክፍተቶችን ለይቶ ማወቅ፡፡
  2. ተስማሚ በሆነ የምግብ ማብሰያ ምርት ውስጥ ምን አይነት ባህሪያትን ማየት ይፈልጋሉ (ምሳ፡ የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለአጠቃቀም ቀላልነት፣ ለረጅም ጊዜ ማገልገል)?
    • ለሀሳብ ክፍት ምላሽ፡፡
    • ዓላማ: የደንበኛ ምርጫዎችን መለየት እና ለምርት ዲዛይንዎ ዋና ዋና ባህሪያት ቅድሚያ መስጠት፡፡ 

ይህን መጠይቅ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል

  • ለዳሰሳ ጥናቶች: ትኩረት ከተደረገባቸው ደንበኞች የይዘት መረጃ ለመሰብሰብ መጠይቁን በኢንተርኔት ወይም በህትመት ማሰራጨት፡፡
  • ለቃለ መጠይቆች: እነዚህን ጥያቄዎች በአንድ ለአንድ ውይይቶች ወቅት የይዘት ሀሳቦችን ለመሰብሰብ እንደ መመሪያ መጠቀም፡፡
  • የዳታ ትንተና: የደንበኛ ችግሮች ግንዛቤዎን ለማረጋገጥ ወይም ለማጥራት ምላሽ ሰጪ ቅርጸቶችን መፈለግ፡፡

 

ደረጃ 3: መፍትሄዎን ማስማማት

የንግድ ሥራ ሀሳብዎ እንዴት ለተለዩት ችግሮች መፍትሄ እንደሚሰጥ ይግለጹ፡፡

ምሳሌ:

የተለየ ችግር

የእርስዎ መፍትሄ

መፍትሄዎ እንዴት ችግሩን እንደሚፈታ

ከፍተኛ የነዳጅ/ማገዶ ወጪዎች

ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ የሶላር ማብሰያዎች

በውድ ማገዶዎች ላይ ጥገኛ መሆንን በመቀነስ፡፡

 

  1. የደንበኛ ችግሮችን ለይቶ ማወቂያ ቴምፕሌት

ይህ የእይታ መሳሪያ ስራ ፈጣሪዎችን በንጹህ የማብሰያ ዘርፉ ውስጥ የተለያዩ የደንበኛ ምድቦችን የሚያጋጥሟቸውን ልዩ ችግሮች ለይተው እንዲያውቁ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የደንበኛ ችግሮችን ማወቅ

የደንበኛ ምድብ: የገጠር አባወራዎች

ቦታ: ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ

ምሳሌ:

ችግር

ለምን ችግር እንደፈጠረ

ወቅታዊ መፍትሄዎች (ካሉ)

የመሻሻያ ዕድሎች

የንጹህ የማብሰያ ምድጃዎች ከፍተኛ ወጪ

ቤተሰቦች ለአካባቢ ተስማሚ አማራጮችን የመግዛት አቅም የሌላቸው በመሆኑ፡፡

ያሉት የገንዘብ ማግኛ አማራጮች ውሱን ናቸው፡፡

የተከፋፈለ ክፍያ ዕቅዶችን ማቅረብ፡፡

 

የደንበኛ ምድብ: ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ቤተሰቦች

ቦታ: አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ምሳሌ:

ችግር

ለምን ችግር እንደፈጠረ

ወቅታዊ መፍትሄዎች (ካሉ)

የመሻሻያ ዕድሎች

ምቹ ያልሆነ የነዳጅ መልሶ መሙያ ሂደት

የጋዝ ሲሊንደሮችን መልሶ መሙያ ወጪው ከፍተኛ ከመሆኑም በተጨማሪ አመቺ ባለመሆኑ፡፡

የነዳጅ ማደያዎች ከመኖሪያ ቦታዎች ሩቅ ናቸው፡፡ 

የነዳጅ የቤት ለቤት አቅርቦት አገልግሎቶችን ማዘጋጀት፡፡

 

  1. የችግር ማረጋገጫ ዝርዝር

ይህ የማረጋገጫ ዝርዝር ስራ ፈጣሪዎችን በንግድ ሥራ ሀሳቦቻቸው ወደፊት ከመግፋታቸው በፊት የተለዩ ችግሮቻቸውን በጥንቃቄ እንዲያረጋግጡ ያስችላቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የችግር ማረጋገጫ ዝርዝር

የሥራ ፈጣሪ ስም: ____________________________

የንግድ ሥራ ሀሳብ: _______________________________

ደረጃ 1: ዳታ መሰብሰብ

  • ቢያንስ ለ10 እጩ ደንበኞች ቃለ መጠይቆች ማካሄድ፡፡
  • በእውነተኛው አለም መቼቶች (ምሳ፡ የገበያ ቦታዎች፣ መኖሪያ ቤቶች) ውስጥ በደንበኛ ባህሪያት ላይ ምልከታ ማድረግ፡፡
  • በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ የይዘት ዳታ ለመሰብሰብ የዳሰሳ ጥናቶችን ማሰራጨት፡፡

ደረጃ 2: ግብረ መልስ መተንተን

  • ከደንበኛ ግብረ መልስ ላይ የጋራ ጭብጦችን ማጠቃለል፡፡
  • እጅግ አንገብጋቢ ችግሮችን በድግግሞሽና ከባድነት ላይ ተመስርቶ መለየት፡፡
  • ግኝቶችን ከነባር ጥናት ወይም የኢንዱስትሪ ሪፖርቶች ጋር ማነጻጸር፡፡

ደረጃ 3: እሳቤዎችን መሞከር

  • ለመፍትሄዎ የመጀመሪያ ሙከራ ወይም mock-up ያዘጋጁ፡፡
  • ሙከራውን በአነስተኛ የደንበኞች ቡድን (ምሳ፡ ከ5-10 ቤተሰቦች) ላይ መሞከር፡፡
  • ጥቅም ላይ መዋልን፣ የዋጋ ተመጣጣኝነትን እና ውጤትን የተመለከተ መረጃ መሰብሰብ፡፡

ደረጃ 4: አቀራረብዎን ማጥራት

  • በአዳዲስ ሀሳቦች ላይ ተመስርተው የችግር ዝርዝርዎን ማሻሻል፡፡
  • የተረጋገጡ ችግሮችን በተሻለ ሁኔታ ለመፍታት የንግድ ስራ ሀሳብዎን ማስተካከል፡፡
  • የተማሩትን ትምህርት ለወደፊት ድግግሞሾች መዝግቦ መያዝ፡፡
  1. የጉዳይ ጥናት ቴምፕሌት ምሳሌ

ይህ ቴምፕሌት የእውነተኛውን ዓለም የተግባር ችግርን የመለየት ምሳሌዎችን ለመመዝገብ የሚያገለግል ፎርማት ይሰጣል፡፡

ቴምፕሌት: የጉዳይ ጥናት

የሥራ ፈጣሪ ስም: ዮሀንስ ገብሬ

የንግድ ሥራ ሀሳብ: ለከተማ ቤተሰቦች የሚቀርቡ በሶላር ሀይል የሚሰሩ ምድጃዎች

ደረጃ 1: ዋና ዋና ችግሮችን መለየት

  • የባህላዊ ምድጃዎች ከፍተኛ የነዳጅ ወጪዎች፡፡
  • የጤና ስጋቶችን የሚያስከትል የቤት ውስጥ አየር መበከል፡፡
  • ስለ ንጹህ የማብሰያ አማራጮች ግንዛቤ ያለመኖር፡፡

 

ደረጃ 2: የማረጋገጫ ሂደት

  • የአዲስ አበባ ነዋሪ ለሆኑ 20 ቤተሰቦች ቃለ መጠይቆች ማካሄድ፡፡
  • በአካባቢ የገበያ ልማዶች ላይ ምልከታ ማካሄድ፡፡
  • የዋጋ ተመጣጣኝነት እግሮችን ለማጥናት የዳሰሳ ጥናት ማሰራጨት፡፡

ደረጃ 3: መፍትሄን ማስማማት

  • ቀላል የዝግጅት መመሪያዎች ያሉት አነስተኛ ወጪ የሚያስወጣ የሶላር ማብሰያ ማዘጋጀት፡፡
  • ግንዛቤ ለመፍጠር ነጻ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ማካተት፡፡
  • ማብሰያዎቹን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ለማከፋፈል ከኤንጂኦዎች ጋር በትብብር መስራት፡፡

ደረጃ 4: ውጤቶች

  • ከሙከራ ተጠቃሚዎች አዎንታዊ ግብረ መልስ ማግኘት: “የሶላር ማብሰያው ገንዘብ ይቆጥባል እንዲሁም የአየር ጥራትን ያሻሽላል፡፡”
  • የዳሰሳ ጥናት የተካሄደባቸው ቤተሰቦች ለንጹህ የማብሰያ ምርቶች ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየት፡፡

የንግድ ስራውን ወደ የገጠር አካባቢዎች ለማስፋፋት ማቀድ፡፡

Scroll to Top