Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ቴምፕሌቶቹ የተዘጋጁት ስራ ፈጣሪዎችን ትኩረት ሳቢ ልዩ የዕሴት ዕቅድ (ዩቪፒ) እንዲያዘጋጁ ለመርዳት ነው፡፡ እነዚህ ግብዓቶች ልዩነት መፍጠርን እንዲለዩ፣ ጥቅሞችን እንዲያብራሩ እና በደንበኛ ግብረ መልስ ላይ ተመስርተው ዩቪፒዎን እንዲያጠሩ በመመሪያነት ያገለግሉዎታል፡፡

  1. የዩቪፒ ዝግጅት ቴምፕሌት

ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎች ግልጽ እና ትኩረት ሳቢ ልዩ የዕሴት ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የዩቪፒ ዝግጅት ማዕቀፍ

የንግድ ድርጅት ስም: ____________________________
ምርት/አገልግሎት: ___________________________

 

ክፍል

ዝርዝሮች

ዋና ችግር

መፍትሄዎ ምን ልዩ ችግር ይፈታል?

መፍትሄ

ምርትዎ ወይም አገልግሎትዎ ምንድን ነው፤ ችግሩንስ እንዴት ይፈታል?

ልዩ ጥቅሞች

መፍትሄዎ የሚያቀርባቸው ከ2-3 ዋና ዋና ጥቅሞች ምንድን ናቸው (ምሳ፡ ወጪ ቁጠባ፣ ጤና)?

ልዩነት

መፍትሄዎን ከተፎካካሪዎችዎ ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

የትኩረት ደንበኛ

የመጀመሪያ ደንበኞችዎ እነ ማን ናቸው (ምሳ፡ የገጠር አባወራዎች፣ የከተማ ነዋሪዎች)?

የዩቪፒ መግለጫ

ከላይ የተገለጹትን በአጭር መግለጫ ያጣምሩ (ምሳ፡ “የእኛ ምርት X ሲሆን Z በማቅረብ የYን ችግር ይፈታል “)፡፡

 

መመሪያዎች:
ጠንካራ ዩቪፒ ለማዘጋጀት እያንዳንዱን ክፍል ደረጃ በደረጃ ይሙሉ፡፡ መግለጫዎን ለደንበኞችዎ የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ በደንበኞች ላይ ይሞክሩ፡፡

  1. የተፎካካሪ ትንተና ቴምፕሌት

ይህ ቴምፕሌት ሥራ ፈጣሪዎችን መፍትሄያቸው እንዴት ከነባር አማራጮች ጋር እንደሚነጻጸር እንዲለዩ በመርዳት ልዩነት መፍጠርን ያረጋግጣል፡፡

ቴምፕሌት: የተፎካካሪ ትንተና ግሪድ

ተፎካካሪ

ምን እንደሚያቀርቡ

ጥንካሬዎች

ደካማ ጎኖች

እርስዎ እንዴት እንደሚለዩ

የባህላዊ ከሰል ሻጮች

ርካሽ ሆኖም ለጤና ጎጂ ከሰል

በስፋት ይገኛል

የጤና ስጋቶች፣ የደን መጨፍጨፍ

ለአካባቢ ተስማሚ፣ ከጭስ ነጻ የሆነ

 

መመሪያዎች:

  1. በገበያዎ ላይ ያሉ ከ2-3 ዋና ዋና ተፎካካሪዎችን ወይም አማራጮችን ይዘርዝሩ፡፡
  2. ጥንካሬዎቻቸውን እና ደካማ ጎኖችጫቸውን ይተንትኑ፡፡ 
  3. እንዴት የእርስዎ መፍትሄ የተለየ እና የተሻለ እንደሆነ ያብራሩ፡፡
  1. የደንበኛ ጥቅም ማወቂያ ቴምፕሌት

ይህ ቴምፕሌት ስራ ፈጣሪዎችን መፍትሄያቸው ለደንበኞች የሚያቀርባቸውን ጥቅሞች እንዲለዩና በቅደም ተከተል እንዲያስቀምጡ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የደንበኛ ጥቅም ማወቂያ ቴምፕሌት

ጥቅም

ይህ ለደንበኞች እንዴት እንደሚጠቅም

የእርስዎ መፍትሄ ይህን እንዴት እንደሚያቀርብ

የወጪ ቁጠባዎች

የቤተሰብ ወጪዎችን ይቀንሳል

ዋጋው ተመጣጣኝ ነው፣ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል ማገዶ ነው

መመሪያዎች:

  1. መፍትሄዎ የሚያቀርባቸው ከ2-4 ዋና ዋና ጥቅሞችን ይዘርዝሩ፡፡
  2. እነዚህ ጥቅሞች ለምን የትኩረት ደንበኞችዎን እንደሚጠቅም ያብራሩ፡፡
  3. መፍትሄዎ እንዴት እያንዳንዱን ጥቅም እንደሚሰጥ ይግለጹ፡፡

 

  1. የዩቪፒ ሙከራ ግብረ መልስ ቅጽ

ይህ ቴምፕሌት ሥራ ፈጣሪዎችን ዩፒቪያቸውን ለማጥራት ከእጩ ደንበኞች የተዋቀረ ግብረ መልስ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የዩቪፒ ሙከራ ግብረ መልስ ቅጽ

የደንበኛ ስም: ____________________________
ምድብ: _________________________________
ቀን: ___________________________________

ምሳሌ

ጥያቄ

መልስ

ግንዛቤዎች/እርምጃዎች

ዩቪፒያችን ስለ ምርታችን ጥቅም በግልጽ ያብራራል? (አዎ/አይ)

   

ዩቪፒያችንን ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

   

ዩቪፒያችንን እንዴት ልናሻሽል እንችላለን?

   

ይህ ዩቪፒ እንዲገዙ ያደርግዎታል? (አዎ/አይ)

   

ማንኛውም ሌሎች ጥቆማዎች ወይም ስጋቶች?

   

መመሪያዎች:

  1. ዩቪፒዎን ከ5-10 እጩ ደንበኞች ያጋሩ፡፡
  2. መልሶችዎን ይመዝግቡ እና ተደጋጋሚ ጭብጦችን ያስተውሉ፡፡
  3. በዩቪፒዎ ላይ የግልጽነት እና ውጤት ማጣሪያ ለማድረግ ግንዛቤዎችን ይጠቀሙ፡፡
  1. የዩቪፒ ማጣሪያ ማረጋገጫ ዝርዝር

ይህ የማረጋገጫ ዝርዝር ስራ ፈጣሪዎችን ዩቪፒያቸውን በሚያዘጋጁበት ወቅት ሁሉንም ዋና ዋና ክፍሎች ከግምት ውስጥ ማስገባታቸውን እንዲያረጋግጡ ያስችላቸዋል፡፡ 

ቴምፕሌት: የዩቪፒ ማጣሪያ ማረጋገጫ ዝርዝር

ምርት/አገልግሎት: ____________________________

  • ግልጽነት መፍትሄዎ የሚፈታውን ዋና ችግር ለይቶ ያሳውቃል፡፡
  • የእርስዎ መፍትሄ እንዴት ችግሩን እንደሚፈታ ይግለጹ፡፡
  • ከደንበኞች ጋር የሚስማሙ ከ2-3 ልዩ ጥቅሞችን ያብራሩ፡፡
  • የእርስዎን መፍትሄ ምን ከተፎካካሪዎችዎ ልዩ እንደሚያደርገው በግልጽ ያብራሩ፡፡
  • መልዕክትዎን ከትኩረት ደንበኞችዎ ጋር ያስማሙ፡፡
  • ዩቪፒውን አጭርና ለመረዳት ቀላል አድርገው ያዘጋጁ፡፡
  • ዩቪፒው ከደንበኞች ጋር የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ በደንበኞች ላይ ይሞክሩ፡፡
  • ዩቪፒዎን ለማጣራትና ለማሻሻል ግብረ መልስ ያካቱ፡፡

 

መመሪያዎች:
እያንዳንዱን ዝርዝር ከተረጋገጠ በኋላ እንደተጠናቀቀ ምልክት ያድርጉበት፡፡ ዩቪፒዎ ትኩረት ሳቢና የተግባር መሆኑን ለማረጋገጥ ይህን የማረጋገጫ ዝርዝር ይጠቀሙ፡፡

Scroll to Top