Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ችግርን መለየት ትኩረት በሚደረግበት ገበያ ውስጥ ደንበኞችን የሚያጋጥሟቸውን ልዩ ተግዳሮቶች ወይም ችግሮች የመለየት፣ የመተንተን እና የመግለጽ ሂደት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንፁህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ ችግርን መለየት እንደ በባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ መሆን፣ የንጹህ የኢነርጂ ውጤቶች ከፍተኛ ወጪዎች እና በቤት ውስጥ አየር ብክለት ምክንያት የሚከተሉ የጤና ስጋቶች የመሳሰሉ ጉዳዮችን መረዳትን ያካትታል፡፡ ይህ ደረጃ ሥራ ፈጣሪዎችን የእውነተኛውን ዓለም ፍላጎቶችን የሚያሟሉ እና ለደንበኞችዎ ትርጉም ያለው እሴት የሚፈጥሩ የንግድ ሥራ ሀሳቦችን እንዲያዳብሩ ያስችላቸዋል፡፡

የትምህርቱ ዓላማዎች

በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡

  1. በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ ደንበኞችን የሚያጋጥሟቸውን ዋና ዋና ችግሮችን መለየት እና መግለጽ፡፡
  2. የንግድ ሥራ ሀሳብዎ የእውነተኛውን ዓለም ችግሮች በብቃት የሚፈቱ ስለመሆኑ ማረጋገጥ፡፡
  3. ደንበኛን ያማከሉ መፍትሄዎችን ለማዘጋጀት እንደ መሰረት ችግርን መለየትን መጠቀም፡፡

 

ዓላማ

የዚህ ትምህርት ዓላማ አዳዲስ የሥራ ፈጣሪዎችን ጊዜና ሀብቶቻቸውን ለንግድ ሥራ ሀሳቦቻቸው ከማዋላቸው በፊት የደንበኛ ችግሮችን የሚለዩበትና የሚያረጋግጡበትን ክህሎቶች ማሳወቅ ነው፡፡ በእውነተኛው ዓለም ችግሮች ላይ በማተኮር መፍትሄዎችዎ አግባብነት ያላቸው መሆኑን፣ ውጤት የሚያመጡ መሆኑን እና ከኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ፍላጎቶች ጋር የሚጣጣሙ መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች 

  1. የደንበኛ ችግሮችን መረዳት: በባህላዊ የማብሰያ ዘዴዎች ላይ ጥገኛ የሆኑ አባወራዎችን የሚያጋጥሟቸውን ልዩ ችግሮችን እንዴት ማወቅ እንደሚችሉ መማር (ምሳ፡ ከጭስ ጋር ተያያዥ የጤና ጉዳቶች፣ ውጤታማ አለመሆን፣ የአካባቢ ተጽእኖ)፡፡
  2. የማረጋገጫ ስልቶች: የንግድ ሥራ ሀሳቦችዎ እነዚህን ችግሮች የሚፈቱ መሆናቸውን የሚያረጋግጡባቸውን ዘዴዎች ያጥኑ፣ ለምሳሌ፡ የዳሰሳ ጥናቶች፣ ቃለ መጠይቆች ወይም በማህበረሰብ ባህሪያት ላይ ምልከታ ማድረግ፡፡
  3. ከገበያ ፍላጎቶች ጋር ማስማማት: መፍትሄዎ የተለዩትን ችግሮች በቀጥታ የሚፈታ መሆኑን እና ከነባሩ አማራጮች የተሻሉ ግልጽ ጥቅሞችን የሚያቀርብ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡
  4. የንፁህ ማብሰያ ትግበራ: ችግሮችን በሚለዩበት ወቅት እንደ የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ተደራሽነት እና ለባህል አግባብነት ባሉ ዘርፍ ተኮር ጉዳዮች ላይ ያተኩሩ፡፡
  5. በተደጋጋሚ ማጥራት: ችግርን መለየት ከእጩ ደንበኞች ተጨማሪ ዳታ እና ግብረ መልስ ሲሰበስቡ እያደገ የሚሄድ ቀጣይነት ያለው ሂደት እንደሆነ ይገንዘቡ፡፡

 

ምሳሌ

ኩነት: የአዲስ አበባ ነዋሪ ወጣት ሥራ ፈጣሪ የሆነው ዮሀንስ በሶላር ሀይል የሚሰሩ ማብሰያዎችን የሚሸጥበት የንግድ ሥራ ለመጀመር ይፈልጋል፡፡ ዮሀንስ ትኩረት ያደረገባቸው ደንበኞችን የሚያጋጥሟቸውን ዋና ዋና ችግሮች መለየት ይጀምራል፡

  1. ዋና ዋና ችግሮች:
    • ብዙ አባወራዎች በባህላዊ የእንጨት ወይም የከሰል ምድጃዎች ላይ ጥገኛ መሆናቸው የደን መጨፍጨፍን እና ከፍተኘ የማገዶ ወጪዎችን ያስከትላል፡፡
    • በጭስ ምክንያት የሚፈጠረው የቤት ውስጥ አየር ብክለት በተለይም በሴቶችና ህጻናት ላይ የመተንፈሻ አካል ህመሞችን ያስከትላል፡፡
    • ነባር ንጹህ የማብሰያ ውጤቶች በአብዛኛው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ውድ ከመሆናቸውም ባለፈ ተደራሽ አይደሉም፡፡
  2. ማረጋገጥ:
    • ዮሀንስ በማህበረሰብ ውስጥ ላሉ ለ20 ቤተሰቦች ቃለ መጠይቅ ያደርግ እና የዋጋ ተመጣጣኝነትና ለአጠቃቀም ቀላል መሆን ዋና ዋና ችግሮች እንደሆኑ ያውቃል፡፡
    • ዮሀንስ በተጨማሪም ብዙ አባወራዎች ስለ ስንጹህ የማብሰያ ቴክኖሎጂዎች የረጅም ጊዜ የጤናና የአካባቢ ጥቅሞች ግንዛቤ እንደሌላቸው ይገነዘባል፡፡
  3. መፍትሄን ማስማማት:
    • ዮሀንስ በግኝቶቹ ላይ ተመስርቶ ቀላል የማዘጋጀት ሂደት ያለው አነስተኛ ወጪ የሚያስወጣ የሶላር ማብሰያ ያዘጋጅ እና ስለ ማብሰያው ጥቅሞች በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር የትምህርት ቁሳቁሶችን ያካትታል፡፡
    • ሀሳቡን በአምስት አባወራዎች ላይ የመጀመሪያ ሙከራ በማድረግ ፈትኖ የሚያረጋግጥ ሲሆን አባወራዎቹ በአጠቃቀምና የወጪ አዋጭነት ላይ አዎንታዊ ግብረ መልስ ይሰጡታል፡፡

 

ችግርን በመለየት አማካኝነት ዮሀንስ የንግድ ስራ ሀሳቡ እውነተኛ የደንበኛ ፍላጎቶችን በመፍታት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የመሳካት እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ያረጋግጣል፡፡

Scroll to Top