Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ይህ ክፍል የገቢ ማግኛ መንገዶች እና የወጪ መዋቅር ትምህርቱን መረዳትና መተግበርን በተመለከተ ለሚጠየቁ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች አጭር መልሶችን ይሰጣል፡፡

  1. የገቢ ማግኛ መንገዶች ምንድን ናቸው፣ ለምንስ ያስፈልጋሉ?

መልስ:
የገቢ ማግኛ መንገዶች እንደ ቀጥተኛ ሽያጮች፣ ትብብሮች ወይም የአገልግሎት ክፍያዎች የመሳሰሉ የንግድ ስራዎ የገቢ ምንጮች ናቸው፡፡ የገቢ ማግኛ መንገዶች የንግድ ስራዎ እንዴት ገንዘብ እንደሚያገኝ ስለሚወስኑ እና የገንዘብ ዘላቂነትን ስለሚያረጋግጡ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ተጨባጭ የገቢ ማግኛ መንገዶችን መለየት ትርፋማነትዎን እንዲያቅዱ እና የንግድ ስራ ሞዴልዎን ከደንበኛ ፍላጎቶች ጋር እንዲያስማሙ ይረዳዎታል፡፡

 

  1. ለንጹህ የማብሰያ ምርቴ ሊሳኩ የሚችሉ የገቢ ማግኛ መንገዶችን የምለየው እንዴት ነው?

መልስ:
የትኩረት ደንበኞችዎን እና ፍላጎቶቻቸውን በመተንተን ይጀምሩ፡፡ ለምሳሌ፡

  • ቀጥተኛ ሽያጭ፡ እንደ ምድጃዎች ወይም ባዮፊዩል ያሉ ምርቶችን ለደንበኞች በቀጥታ መሸጥ፡፡
  • ትብብሮች: ወጪዎችን ለመደጎም ወይም ምርቶችን ለማከፋፈል ከኤንጂኦዎች፣ የማይክሮፋይናንስ ተቋማት ወይም የመንግስት ፕሮግራሞች ጋር በትብብር መስራት፡፡
  • የአገልግሎት ክፍያዎች: የጥገና፣ ስልጠና ወይም ትእዛዝን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶች ማቅረብ (ምሳ፡ የማገዶ አቅርቦት)፡፡
    እነዚህን እድሎች በብልሀት ለመዘርዘርና ቅድሚያ ለመስጠት የገቢ ማግኛ መንገዶችን መለያ ቴምፕሌቱን ይጠቀሙ፡፡
  1. የወጪ መዋቅር ምንድን ነው፣ በንግድ ስራዬ ላይ እንዴት ተጽእኖ ይፈጥራል?

መልስ:
የወጪ መዋቅር ቋሚ ወጪዎችን (ምሳ፡ ኪራይ፣ ደመወዝ)፣ ተለዋዋጭ ወጪዎችን (ምሳ፡ ጥሬ እቃዎች) እና የመጀመሪያ ኢንቨስትመንትን (ምሳ፡ የመጀመሪያ ሙከራ) ጨምሮ) የንግድ ስራዎን ለመጀመርና ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ይገልጻሉ፡፡ የወጪ መዋቅርዎን መረዳት ወጪዎችዎን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመቆጣጠር፣ ተጨባጭ ዋጋ ለመወሰን እና ትርፋማነትዎን ለማረጋገጥ ይረዳዎታል፡፡

  1. ለንግድ ሥራዬ የገቢ ማግኛ ነጥቤን የማሰላው እንዴት ነው?

መልስ:
የገቢ ማግኛ ነጥብ ሁሉንም ወጪዎችዎን ለመሸፈን መሸጥ ያለብዎ የምርቶች ብዛት ነው፡፡ ይህን ቀመር ይጠቀሙ፡
የገቢ ማግኛ ነጥብ (ምርቶች) = ቋሚ ወጪዎች ÷ (የመሸጫ ዋጋ – ተለዋዋጭ ወጪዎች) .
ለምሳሌ፡ ወጪዎችዎ ብር 500 ከሆኑ የመሸጫ ዋጋዎ ብር 25 እና በምርት ተለዋዋጭ ወጪዎችዎ ብር 10 ሲሆኑ የገቢ ማግኛ ነጥብዎ ብር 500 ÷ (25 – 10) = 33.33 ምርቶች ናቸው፡፡ ይህ ማለት ትርፍ ማግኘት ለመጀመር ቢያንስ 34 ምርቶችን መሸጥ ይኖርብዎታል፡፡

  1. ጠንካራ ልዩ የእሴት ዕቅድ (ዩቪፒ) ቢኖረኝም እንኳ ጪዎችን መተንተን የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

መልስ:
ጠንካራ ዩቪፒ ደንበኞችን ይስባል፣ ነገር ግን ወጪዎችን መተንተን የንግድ ስራዎ በገንዘብ አዋጭ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ወጪዎችዎን ካልተረዱ ለምርትዎ የተሳሳተ ዋጋ ሊሰጡ፣ ወጪዎችዎን ለመሸፈን ሊቸገሩ፣ ወይም ትርፍ ማግኘት ላይችሉ ይችላሉ፡፡ ዩቪፒም የወጪ ትንተናም ዘላቂ የንግድ ስራ ለመመስረት ወሳኝ ናቸው፡፡

  1. ትብብር ገቢዬን ለማሳደግ ወይም ወጪዎቼን ለመቀነስ ሊረዳኝ ይችላል?

መልስ:
አዎ፡፡ ትብብሮች ለንግድ ስራዎ በእጅጉ ሊጠቅሙ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡

  • ከኤንጂኦዎች ጋር ትብብር ማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ለምርት ወጪዎች ድጎማ በማድረግ የምርቱን የተቀባይነት ደረጃዎች ሊያሳድግ ይችላል፡፡
  • ከማይክሮፋይናንስ ተቋማት ጋር መተባበር ለደንበኞች የገንዘብ ድጋፍ አማራጮችን በማቅረብ ምርትዎን የበለጠ ተደራሽ ሊያደርግ ይችላል፡፡
  • ከመንግስት ፕሮግራሞች ጋር በትብብር መስራት የማከፋፈያ ኔትወርኮችን ወይም ተአማኒነትን ሊያስገኝ ይችላል፡፡
    እጩ አጋሮችን ለመለየትና ለመገምገም የትብብር እድል ማወቂያ ቴምፕሌትን ይጠቀሙ፡፡
  1. የንግድ ስራዬ የገንዘብ አዋጭነት እንዳለው የማረጋግጠው እንዴት ነው?

መልስ:
የገንዘብ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ:

  • ከንግድ ስራዎ ሞዴል ጋር የሚስማሙ ተጨባጭ የገቢ ማግኛ መንገዶችን ይለዩ፡፡
  • ወጪዎችዎን በውጤታማነት ለማስተዳደር የወጪ መዋቅርዎን ይተንትኑ፡፡
  • ኢላማዎችን ለማዘጋጀትና ትርፋማነትን ለማረጋገጥ የገቢ ማግኛ ነጥብዎን ያስሉ፡፡
  • በገበያ ግብረ መልስና አፈጻጸምዎ ላይ ተመስርተው የገንዘብ እቅድዎን በቋሚበነት እየገመገሙ ያስተካክሉ፡፡
    ሁሉም ዋና ዋና ክፍሎች መዳሰሳቸውን ለማረጋገጥ የገንዘብ አዋጭነት ማረጋገጫ ዝርዝር ይጠቀሙ፡፡
  1. በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ የቋሚና ተለዋዋጭ ወጪዎች አንዳንድ ምሳሌዎች ምንድን ናቸው?

መልስ:

  • ቋሚ ወጪዎች: የቤተ ሙከራ ኪራይ፣ የሰራተኞች ደመወዝ፣ የማምረቻ መሳሪያዎች ወይም የኦንላይን ሽጮች ወርሀዊ የኢንተርኔት ወጪዎች፡፡
  • ተለዋዋጭ ወጪዎች፡ ጥሬ ዕቃዎች (ምሳ፡ የሶላር ፓኔሎች፣ ሰው ሰራሽ ከሰል)፣ የማሸጊያ፣ ትራንስፖርት ወይም አቅርቦት ክፍያዎች፡፡

እነዚህን ወጪዎች መረዳት በጀትዎን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማዘጋጀት እና ለምርትዎ ተገቢውን ዋጋ ለማስከፈል ይረዳዎታል፡፡

  1. የንግድ ስራ ሞዴሌን ለማሻሻል በዚህ ትምህርት ውስጥ የቀረቡትን መሳሪያዎች እንዴት ልጠቀምባቸው እችላለሁ?

መልስ:
እያንዳንዱ መሳሪያ ለልዩ ዓላማ ያገለግላል:

  • የገቢ ማግኛ መንገዶችን መለያ ቴምፕሌት፡ የገቢ ምንጮችዎን እንዲያጠኑና በቅደም ተከተል እንዲያስቀምጡ ይረዳዎታል፡፡
  • የጠጪ መዋቅር ትንተና ቴምፕሌት፡ ለተሻለ የወጪ አስተዳደር ቋሚና ተለዋዋጭ ወጪዎችን ያሰላል፡፡
  • የገቢ ማግኛ ነጥብ ቴምፕሌት፡ የንግድ ስራዎ መቼ ገቢ ማስገኘት እንደሚጀምር ያሰላል፡፡
  • የትብብር እድል ማወቂያ ቴምፕሌት፡ ተደራሽነትዎን ለማስፋት ወይም ወጪዎችዎን ለመቀነስ እጩ ተባባሪዎችዎን ይለያል፡፡
  • የገንዘብ አዋጭነት ማረጋገጫ ዝርዝር፡ የገንዘብ እቅድ ዝግጅት ሁሉም ክፍሎች ከግምት ውስጥ መግባታቸውን ያረጋግጣል፡፡
    እነዚህን መሳሪያዎች በብልሀት መጠቀም የንግድ ስራ ሞዴልዎ በአግባቡ እንደታቀደ እና የገንዘብ አዋጭነት እንዳለው ያረጋግጣል፡፡
Scroll to Top