ይህ ክፍል ልዩ የእሴት ዕቅድ (ዩቪፒ) ትምህርትን ስለመገንዘብና መተግበር በተመለከተ በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች አጭር መልሶችን ይሰጣል፡፡
-
ልዩ የእሴት ዕቅድ (ዩቪፒ) ምንድን ነው?
መልስ:
ልዩ የዕሴት ዕቅድ (ዩቪፒ) ምን ምርትዎን ወይም አገልግሎትዎን የላቀ እንደሚያደርገው እና ለምን ደንበኞች ምርቱን ከተፎካካሪዎች ምርት ይልቅ መምረጥ እንዳለባቸው የሚያብራራ ግልጽ መግለጫ ነው፡፡ ልዩ የእሴት ዕቅድ የመፍትሄዎን ልዩ ጥቅሞችና ልዩነቶች ያብራራል፡፡
-
መፍትሄዬ የሚፈታውን ዋና ችግር የምለየው እንዴት ነው?
መልስ:
እንደ ቃለ መጠይቆች፣ የዳሰሳ ጥናቶች ወይም ምልከታዎች የመሳሰሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም የደንበኛ ችግሮችን በማጥናትና በማረጋገጥ ይጀምሩ፡፡ የትኩረት ደንበኞችዎን ስለሚያጋጥሟቸው እንደ ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች፣ የጤና ስጋቶች ወይም የአካባቢ ጉዳት የመሳሰሉ ችግሮች ያስቡ እና መፍትሄዎ እጅግ ውጤታማ በሆነ መልኩ ሊፈታው በሚችለው ችግር ላይ ያተኩሩ፡፡
-
በዩቪፒ ውስጥ ልዩነት መፍጠር የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
መልስ:
ልዩነት መፍጠር መፍትሄዎ በተወዳዳሪ ገበያ ውስጥ ልቆ እንዲወጣ ለማድረግ ያስችላል፡፡ ምን ምርትዎን ልዩ እንደሚያደርገው (ምሳ፡ የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለአካባቢ ተስማሚነት፣ ምቹነት) በማብራራት ለእነዚህ ልዩ ባህሪያት ዋጋ የሚሰጡ ደንበኞችን ትኩረት ይስባሉ፡፡
-
ዩቪፒ በማዘጋጀት ረገድ መቅረት ያለባቸው አንዳንድ የተለመዱ ስህተቶች ምንድን ናቸው?
መልስ:
- በጣም ግልጽ አለመሆን ወይም ማጠቃለል (ምሳ፡ “ምርታችን ምርጥ ነው”)፡፡
- ከጥቅሞች ይልቅ ባህሪያት ላይ ማተኮር፡፡
- የትኩረት ደንበኞችዎን ፍላጎቶች ችላ ማለት፡፡
- ዩቪፒውን በጣም ረጅም ወይም ውስብስብ ማድረግ፡፡
-
በዩቪፒዬ ውስጥ የደንበኛ ጥቅሞችን የማብራራው እንዴት ነው?
መልስ:
የትኩረት ደንበኞችዎ ዋጋ በሚሰጧቸው እንደ የወጪ ቁጠባዎች፣ የጤና ማሻሻያዎች ወይም አመቺነት ባሉ ተጨባጭ ውጤቶች ላይ ያተኩሩ፡፡ ተጠቃሚዎችን ለመዘርዘር፣ ለምን እነዚህ እንደሚጠቅሙ ለማብራራት እና እንዴት መፍትሄዎ ለእነዚህ መፍትሄ እንደሚሰጥ ለመግለጽ የደንበኛ ጥቅም ማወቂያ ቴምፕሌትን ይጠቀሙ፡፡
-
ለተለያዩ የደንበኛ ምድቦች የተለያዩ ዩቪፒዎችን መስጠት እችላለሁ?
መልስ:
አዎ፡፡ መፍትሄዎ ለብዙ የተለያዩ ምድቦች (ምሳ፡ የገጠር አባወራዎች እና የከተማ ነዋሪዎች) የሚያገለግል ከሆነ ዩቪፒዎን የእያንዳንዱን ቡድን ልዩ ፍላጎቶች እና ምርጫዎች መፍትሄ እንዲሰጥ አድርገው ሊያዘጋጁ ይችላሉ፡፡ ሆኖም እያንዳንዱ ዩቪፒ ግልጽና ትኩረት ሰጪ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡
-
ዩቪፒዬን በደንበኞች ላይ የምሞክረው እንዴት ነው?
መልስ:
ዩቪፒዎን ከ5-10 እጩ ደንበኞች ለማጋራት የዩቪፒ ሙከራ ግብረ መልስ ቅጽን ይጠቀሙ፡፡ የሚከተሉትን አይነት ጥያቄዎች ይጠይቁ፡
- ይህ ዩቪፒ የምርታችንን ጥቅም በግልጽ ያብራራል?
- ከዩቪፒያችን ውስጥ እጅግ የሚልቀው ምንድን ነው?
- እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ዩቪፒዎን ለማጥራት ግብረ መልስ ያካቱ፡፡
-
ጠንካራ ዩቪፒ ለማዘጋጀት ምን መሳሪያዎች ሊረዱኝ ይችላሉ?
መልስ:
የሚከተሉትን በትምህርቱ ውስጥ የቀረቡ ቴምፕሌቶች ይጠቀሙ፡
- የዩቪፒ ማዘጋጃ ቴምፕሌት፡ ግልጽና ሳቢ መግለጫ ለማዘጋጀት፡፡
- የተፎካካሪ ትንተና ቴምፕሌት: ልዩነትን ለይቶ ለማሳወቅ፡፡
- የደንበኛ ጥቅም ማወቂያ ቴምፕሌት: ለጥቅሞች ቅደም ተከተል ለመስጠት፡፡
- የዩቪፒ ግብረ መልስ ቅጽ፡ ዩቪፒዎን ለማረጋገጥና ለማጥራት፡፡
- የዩቪፒ ማጣሪያ ማረጋገጫ ዝርዝር: ሁሉም ክፍሎች መካተታቸውን ለማረጋገጥ፡፡
-
ዩቪፒዬ ምን ያክል ረጅም መሆን አለበት?
መልስ:
ዩቪፒዎ አጭር ማለትም አንድ ወይም ሁለት አረፍተ ነገሮችን ቢይዝ ይመረጣል፡፡ ዩቪፒዎ ደንበኞችን ግራ ሳያጋባ ዋና ችግሩን፣ መፍትሄውን እና ልዩ ጥቅሞችን በፍጥነት የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡
-
ዩቪፒዬ ውጤታማ እንደሆነ የማውቀው እንዴት ነው?
መልስ:
ውጤታማ ዩቪፒ ከትኩረት ደንበኞች ጋር የሚስማማና ወደ ተግባር የሚመራ ነው፡፡ ዩቪፒው ግልጽ፣ ሳቢ እና ደንበኞችን ከተፎካካሪዎች ይልቅ የእርስዎን መፍትሄ እንዲመርጡ እንደሚያነሳሳ ለማረጋገጥ በደንበኞች ላይ ይሞክሩት፡፡