Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትምህርትን መረዳትን እና መተግበርን በተመለከተ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች፡፡ እነዚህ FAQs በንድፈ ሀሳቦቹ፣ መሳሪያዎቹ እና ቴምፕሌቶቹ ላይ በሚሰሩበት ወቅት ሊያጋጥሙዎ ለሚችሉ የተለመዱ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣሉ፡፡

  1. ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ማለት ምን ማለት ነው፣ ለምንስ ያስፈልጋል?

መልስ:
ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ማለት የትኩረት ደንበኞችዎን ልዩ ፍላጎቶች መረዳትና መፍታት ነው፡፡ ይህ መፍትሄዎችዎ አግባብነት ያላቸው፣ ተደራሽ እና ውጤት አምጪ መሆናቸውን በማረጋገጥ ከፍተኛ የተቀባይነት ደረጃዎች እና የደንበኛ እርካታ ስለሚያስገኝ አስፈላጊ ነው፡፡

  1. የትኩረት ደንበኞቼን የምለየው እንዴት ነው?

መልስ:
ደንበኞችዎን በሥነ ሕዝብ (ምሳ፡ እድሜ፣ ገቢ)፣ በባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች) እና ፍላጎቶች (ምሳ፡ የዋጋ ተመጣጣኝነት) በመመደብ ይጀምሩ፡፡ ይህን መረጃ በብልሀት ለማደራጀት የደንበኛ ምደባ ቴምፕሌቱን ይጠቀሙ፡፡

  1. የትኩረት ደንበኞቼን በተመለከተ በቂ መረጃ ባላገኝስ??

መልስ:
ዳታ ውሱን ከሆነ የጥናት ዘዴዎችዎን ያስፋፉ፡፡ ከእጩ ደንበኞች በቀጥታ ግንዛቤዎችን ለማግኘት ቃለ መጠይቆች፣ የዳሰሳ ጥናቶች ወይም ምልከታዎች ያድርጉ፡፡ ከአካባቢ ድርጅቶች ጋር ትብብር መፍጠርም ተጨማሪ ምንጮችን እና ሀሳቦችን ሊያስገኝ ይችላል፡፡ 

  1. የደንበኛ የማንነት መግለጫ የማዘጋጀው እንዴት ነው?

መልስ:
የትኩረት ደንበኞችዎን ዝርዝር መግለጫዎች ለማዘጋጀት የማንነት መግለጫ ዝግጅት ቅጹን ይጠቀሙ፡፡ እንደ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ስራ፣ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ እንቅፋቶች እና ተነሳሽቶች የመሳሰሉ ባህሪያትን ያካቱ፡፡ ለእያንዳንዱ የማንነት መግለጫ ተያያዥ ስም ይስጡ (ምሳ፡ ለገጠር የቤት እመቤት “ሰላም”)፡፡

  1. መፍትሄዎችን ከተለያዩ የደንበኛ ቡድኖች ጋር ማስማማት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

መልስ:
የተለያዩ ቡድኖች የተለያዩ ችግሮች እና ምርጫዎች አሏቸው፡፡ መፍትሄዎችን ማስማማት ምርትዎ ልዩ ፍላጎቶችን እንደሚያሟላ በማረጋገጥ አግባብነትና ውጤታማነትን ያሳድጋል፡፡ ለምሳሌ፡ የከተማ ነዋሪዎች ለምቹነት ቅድሚያ የሚሰጡ ሲሆን የገጠር ቤተሰቦች ደግሞ በዋጋ ተመጣጣኝነት ላይ ሊያተኩሩ ይችላሉ፡፡

  1. ከደንበኞች ግብረ መልስ የምሰበስበው እንዴት ነው?

መልስ:
የዳሰሳ ጥናት ወይም ቃለ መጠይቅ ለማዘጋጀት የግብረ መልስ ስብሰባ ቴምፕሌቱን ይጠቀሙ፡፡ ስለ ደንበኞችዎ ችግሮች፣ የእርካታ ደረጃዎች እና ተፈላጊ ባህሪያት የተመለከቱ ጥያቄዎችን ይጠይቁ፡፡ ከተቻለ ሰፊ ግንዛቤዎችን ለማግኘት የመጀመሪያ ሙከራ ወይም የማስመሰያ ሙከራ ይሞክሩ፡፡

  1. የደንበኛ ግብረ መልስ ከእሳቤዎቼ ጋር የሚቃረን ከሆነ ምን ማድረግ አለብኝ?

መልስ:
ምንም አይደለም! የደንበኛ ግብረ መልስ እሳቤዎችዎን ለማረጋገጥ ወይም ለማጥራት ይረዳዎታል፡፡ መፍትሄዎን ለማስተካከል እና ከእውነተኛው ዓለም ፍላጎቶች ጋር በተሻለ ሁኔታ እንዲጣጣሙ ለማድረግ ግንዛቤዎችን ይጠቀሙ፡ለ

  1. መፍትሄዎቼ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ደንበኞች በዋጋ ተመጣጣን መሆናቸውን የማረጋግጠው እንዴት ነው?

መልስ:
ወጪ ቆጣቢ ምርቶችን ያዘጋጁ እና እንደ በጊዜ የተከፋፈለ የክፍያ ዕቅድ ያሉ የገንዘብ ማግኛ አማራጮችን ያጥኑ፡፡ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ተደራሽነትዎን ለማሻሻል ከማይክሮፋይናንስ ተቋማት ወይም ኤንጂኦዎች ጋር ትብብር ይፍጠሩ፡፡

  1. በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ የደንበኛ ምድቦች ላይ ማተኮር እችላለሁ?

መልስ:
በጥረቶችዎ ላይ ለማተኮር እንዲረዳዎ በአንድ ወይም ሁለት ምድብ ላይ በማተኮር መጀመር የተሻለ ነው፡፡ አንዴ የደንበኞች ፍላጎቶችን ከፈቱ በኋላ ትኩረትዎን ወደ ሌሎች ምድቦች ሊያሰፉ ይችላሉ፡፡ ይህን ማድረግዎ ውጤትዎን በአግባቡ የተስማማና ውጤት አምጪ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡

  1. ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ከንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ ጋር የሚስማማው እንዴት ነው?

መልስ:
ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ለንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ የ“ችግር”፣ “መፍትሄ” እና “የደንበኛ ምድቦች” ክፍሎች መረጃ ይሰጣል፡፡ የትኩረት ደንበኞችዎን በጥልቀት በመረዳት የተረጋገጡ ችግሮችን የሚፈቱ እና የገበያ ፍላጎቶችን የሚያሟሉ መፍትሄዎችን ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡

 

  1. ደንበኛን ያማከሉ መርሆዎችን ለመተግበር ምን መሳሪያዎችን መጠቀም አለብኝ?

መልስ:
በትምህርቱ ውስጥ የቀረቡትን የደንበኛ ምደባ ቴምፕሌት፣ የማንነት መግለጫ ዝግጅት ቴምፕሌት፣ የደንበኛ ፍላጎቶች ትንተና ቴምፕሌት፣ የግብረ መልስ መሰብሰቢያ ቴምፕሌት እና የመፍትሄ ዝግጅት የማረጋገጫ ዝርዝር ይጠቀሙ፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች የደንበኛ ፍላጎቶችን በመለየትና በመፍታት ረገድ ደረጃ በደረጃ ይመሩዎታል፡፡

  1. ትብብሮች ደንበኛን ያማከለ ትኩረትን እንዴት ሊያሻሽሉ ይችላሉ?

መልስ:
ከአካባቢ ድርጅቶች፣ ኤንጂኦዎች ወይም የማህበረሰብ ቡድኖች ጋር የሚደረጉ ትብብሮች የተለያዩ የደንበኛ ግንዛቤዎችን፣ የስርጭት ኔትወርኮችን እና ምንጮችን ለመድረስ ያስችላል፡፡ ይህ የትኩረት ደንበኞችዎን ውጤታማ በሆነ መልኩ የመድረስና የማገልገል ችሎታዎን ያሳድጋል፡፡

  1. ደንበኛን ላማከለ ትንተና ምን ያክል ጊዜ መመደብ አለብኝ?

መልስ:
የሚያስፈልገው ጊዜ እንደ የንግድ ሥራ ሀሳብዎ ውስብስብነት ላይ ይመሰረታል፡፡ ሆኖም ጥንቃቄዎን በማረጋገጥ ፍጥነትዎን ይዘው ለመቀጠል ሂደቱን ከ1-2 ሳምንታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ያልሙ፡፡

  1. ከትንተና ወደ መፍትሄ ዝግጅት ለማለፍ ዝግጁ መሆኔን የማውቀው እንዴት ነው?

መልስ:
የደንበኛ ፍላጎቶችን ሲያረጋግጡ፣ ዝርዝር የማንነት መግለጫዎች ሲያዘጋጁ፣ የተግባር ግብረ መልስ ሲሰበስቡ እና መፍትሄዎን ከእያንዳንዱ ምድብ ልዩ ችግሮች ጋር ሲያስማሙ ዝግጁ ይሆናሉ፡፡

Scroll to Top