Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ
  1. ችግርን መለየት ምንድን ነው፣ ለምንስ ያስፈልጋል?

መልስ:

ችግርን መለየት ትኩረት በተደረገበት ገበያ ውስጥ ያሉ ደንበኞችን የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች የመገንዘብ እና የመተንተን ሂደት ነው፡፡ ችግርን መለየት የንግድ ሥራ ሀሳብዎ የእውነተኛውን ዓለም ችግሮች የሚፈታ መሆኑን በማረጋገጥ ያለመሳካት እድልን ስለሚቀንስ እና ውጤቱን ስለሚያሳድግ አስፈላጊ ነው፡፡

  1. በንጹህ የማብሰያ ዘርፉ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና ችግሮችን የምለየው እንዴት ነው?

መልስ:

እንደ ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች፣ በቤት ውስጥ አየር መበከል ምክንያት የሚፈጠሩ የጤና ስጋቶችና በባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ መሆን የመሳሰሉ የተለመዱ ችግሮችን በማጥናት ይጀምሩ፡፡ ዳታ ለመሰብሰብ እና እነዚህን ችግሮች ለማረጋገጥ እንደ ቃለ መጠይቆች፣ የዳሰሳ ጥናቶች ወይም ምልከታ የመሳሰሉ መሳሪያዎችን ይጠቀሙ፡፡

  1. ችግርን በመለየት ላይ ምን መሳሪያዎች ሊረዱኝ ይችላሉ?

መልስ:

በትምህርቱ ውስጥ የቀረቡትን የችግር መለያ ወርክሺት፣ የደንበኛ ችግሮችን ማወቂያ ቴምፕሌት እና የችግር ማረጋገጫ ዝርዝር ይጠቀሙ፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች የደንበኛ ችግሮችን ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲዘረዝሩእንዲያረጋግጡና እንዲፈቱ ይመሩዎታል፡፡

  1. የለየኋቸውን ችግሮች የማረጋግጠው እንዴት ነው?

መልስ:

ችግሮችን በቃለ መጠይቆች፣ የዳሰሳ ጥናቶች ወይም የመጀመሪያ ሙከራ አማካኝነት ከእጩ ደንበኞች ግብረ መልስ በመሰብሰብ ያረጋግጡ፡፡ የችግሮቹን አግባብነት ለማረጋገጥ ግኝቶችዎን ከነባር ጥናት ወይም ሪፖርቶች ጋር ያነጻጽሩ፡፡

  1. ስለ ደንበኛ ችግሮች በተመለከተ በቂ መረጃ ባላገኝስ?

መልስ:

ዳታ ውሱን ከሆነ የጥናት ዘዴዎችዎን ያስፋፉ፡፡ ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማጥናት ተጨማሪ ቃለ መጠይቆችን ያድርጉ፣ በደንበኛ ባህሪያት ላይ ቀጥተኛ ምልከታ ያድርጉ ወይም ከአካባቢ ድርጅቶች ጋር በትብብር ይስሩ፡፡

  1. መፍትሄዬ ከደንበኛ ፍላጎቶች ጋር እንደሚስማማ የማረጋግጠው እንዴት ነው?

መልስ:

ችግሮችን ከለዩ እና ካረጋገጡ በኋላ መፍትሄዎን በቀጥታ ችግሮቹን ለመፍታት ያዘጋጁ፡፡ መፍትሄዎን በአነስተኘ የደንበኞች ቡድን ላይ ይሞክሩ እና በሚያገኙት ግብረ መልስ ላይ ተመስርተው ያጥሩ፡፡

  1. በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ የደንበኛ ምድቦች ላይ ማተኮር እችላለሁ?

መልስ:

በጥረቶችዎ ላይ ለማተኮር እንዲረዳዎ በአንድ ምድብ (ምሳ፡ የገጠር አባወራዎች) ላይ በማተኮር መጀመር የተሻለ ነው፡፡ ትኩረትዎን እንደ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ቤተሰቦች ወዳሉ ሌሎች ምድቦች ሊያሰፉ ይችላሉ፡፡

  1. የመጀመሪያ እሳቤዎቼ የተሳሳቱ ከሆኑ ምን ማድረግ አለብኝ?

መልስ:

ምንም አይደለም! ችግርን መለየት ተደጋጋሚ ሂደት ነው፡፡ እሳቤዎችዎን ለማስተካከል እና ከመቀጠልዎ በፊት የደንበኛ ፍላጎቶች ግንዛቤዎን ለማጥራት የሚያገኙትን ግብረ መልስ ይጠቀሙ፡፡

  1. ችግርን መለየት ከንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ ማዕቀፍ ጋር እንዴት ይጣጣማል?

መልስ:

ችግርን መለየት የንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ መሰረት ይሰጣል፡፡ የ“ችግር” እና “መፍትሄ” ክፍሎች የደንበኛ ችግሮችን በግልጽ በመግለጽና የማረጋገጥ ችሎታዎ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡

  1. ትብብሮች ችግርን ለመለየት እንዴት ሊረዱ ይችላሉ?

መልስ:

ከኤንጂኦዎች፣ የማህበረሰብ ቡድኖች ወይም የአካባቢ ድርጅቶች ጋር የሚደረጉ ትብብሮች ሰፊ የዳታ ስብስቦችን፣ የተለያዩ እይታዎችን እና የማረጋገጫ ግብዓቶችን በመስጠት የግኝቶችዎን ትክክለኛነት ሊያሻሽሉ ይችላሉ፡፡

  1. ችግርን በመለየት ወቅት ማስቀረት ያሉብኝ አንዳንድ የተለመዱ ስህተቶች ምንድን ናቸው?

መልስ:

  • ችግሮችን ያለ ማረጋገጫ ማሰብ፡፡
  • ከደንበኛ ፍላጎቶች ጋር በማይጣጣሙ አላስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ማተኮር፡፡
  • እንደ ችግሮችን ማወቅ ወይም የመጀመሪያ ሙከራ ማድረግ የመሳሰሉ ደረጃዎችን መዝለል፡፡
  1. ችግርን በመለየት ላይ ምን ያክል ጊዜ ማዋል አለብኝ?

መልስ:
የሚያስፈልገው ጊዜ እንደ የንግድ ሥራ ሀሳብዎ ውስብስብነት ላይ ይመሰረታል፡፡ ሆኖም ጥንቃቄዎን በማረጋገጥ ፍጥነትዎን ይዘው ለመቀጠል ሂደቱን ከ1-2 ሳምንታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ያልሙ፡፡

  1. ችግርን ከመለየት መፍትሄ ወደማዘጋጀት ለመሸጋገር ዝግጁ እንደሆንኩ የማውቀው እንዴት ነው?

መልስ:
ችግሮቹን ሲያረጋግጡ፣ መፍትሄዎን ከደንበኛ ፍላጎቶች ጋር ሲያስማሙ እና በልበ ሙሉነት ለመቀጠል በቂ ግብረ መልስ ሲሰበስቡ ዝግጁ ይሆናሉ፡፡

Scroll to Top