Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ይህ መመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ዋና ዋና ንድፈ ሀሳቦች በተለይም በንጹህ የምግብ ማብሰያ ዘርፍ ላይ የሚተገብሩበት የተደራጀ፣ ደረጃ በደረጃ ሂደት ይሰጥዎታል፡፡ እያንዳንዱ ደረጃ የቀረበውን የትምህርት ይዘት ግልጽ መመሪያዎች እና ማጣቀሻዎች ይይዛል፡፡

ደረጃ 1: ችግሩን መረዳት

ዓላማ: በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ የእርስዎ መፍትሄ የሚፈታውን ዋና ችግር መለየት፡፡

  • ምን እንደሚያደርጉ:
    • የችግሩን መግለጫ መገምገም: ብዙ ቤተሰቦች በባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ በመሆናቸው ይህም ከፍተኛ ወጪዎችን፣ የቤት ውስጥ አየር መበከልን እና የጤና ስጋቶችን ያስከትልባቸዋል፡፡
    • ችግሩ እንዴት ትኩረት ባደረጉባቸው ደንበኞች (ምሳ፡ የገጠር ቤተሰቦች፣ በሴት እማወራ የሚመሩ ቤተሰቦች) ላይ ተጽእኖ እንደሚፈጥር ይግለጹ፡፡
  • መመሪያ: እንደ የነዳጅ/ማገዶ ወጪዎች፣ ከጭስ ጋር ተያያዥ ህመሞች ወይም በማገዶ እንጨት ፍጆታ የተነሳ የሚፈጠር የደን መጨፍጨፍ ስላሉ ልዩ ችግሮች ያስቡ፡፡
  • ቀጣይ እርምጃ: ወደ ደረጃ 2 ይለፉ፡፡

ደረጃ 2: መፍትሄውን መግለጽ

ዓላማ: ለተለየው ችግር መፍትሄዎን በግልጽ ማስቀመጥ፡፡

  • ምን እንደሚያደርጉ:
    • የችግሩን መግለጫ መገምገም: ጭስ የሚቀንሱ እና የምግብ ማብሰያ ቅልጥፍናን የሚያሻሽሉ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው፣ ለአካባቢ ተስማሚ ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎች፡፡
    • እንደ የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለአካባቢ ተስማሚነት እና የተሻሻለ ቅልጥፍና የመሳሰሉ የመፍትሄዎን ዋና ዋና ባህሪያት ያብራሩ፡፡
  • መመሪያ: መፍትሄዎ በቀጥታ ችግሩን እንደሚፈታ እና ከደንበኛ ፍላጎቶች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡
  • ቀጣይ እርምጃ: አንዴ መፍትሄዎን ከገለጹ በኋላ ወደ ደረጃ 3 ይለፉ፡፡

ደረጃ 3: ዋና ዋና መለኪያዎችን መለየት

ዓላማ: የንግድ ስራ ሀሳብዎን ስኬታማነት እንዴት እንደሚለኩ መወሰን፡፡

  • ምን እንደሚያደርጉ:
    • ዋና ዋና መለኪያዎችን መገምገም: ምርቱን የተቀበሉ ቤተሰቦች ብዛት፣ የቤት ውስጥ አየር መበከል መቀነስ፣ የደንበኛ እርካታ ደረጃዎች፡፡
    • ለመፍትሄዎና ግብዎ አግባብነት ያላቸው መለኪያዎችን ይዘርዝሩ፡፡
  • መመሪያ: ውጤትን በሚገልጹ መለካት የሚችሉ ውጤቶች ላይ ያተኩሩ (ምሳ፡ የጤና መሻሻሎች፣ የአካባቢ ጥቅሞች)፡፡
  • ቀጣይ እርምጃ: ዋና ዋና መለኪያዎችን ከለዩ በኋላ ወደ ደረጃ 4 ይለፉ፡፡

ድረጃ 4: ልዩ የዋጋ ዕቅድዎን (ዩቪፒ) መቅረጽ

ዓላማ: የእርስዎን መፍትሄ ምን ከተፎካካሪዎችዎ የተሻለ እንደሚያደርገው መግለጽ፡፡

  • ምን እንደሚያደርጉ:
    • ልዩ የዋጋ ዕቅድዎን መገምገም: የማብሰያ ምድጃዎቹ ዋጋ ከተፎካካሪዎች ዋጋ በ30% የሚቀንስ ከመሆኑም በተጨማሪ ነጻ ተከላና ስልጠና ይቀርባል፡፡
    • እንደ የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ተጨማሪ አገልግሎቶች ወይም ለባህል አግባብነት የመሳሰሉ የመፍትሄዎን ልዩ ጥቅሞች ያብራሩ፡፡
  • መመሪያ: ዩቪፒዎ ትኩረት የተደረገባቸውን ደንበኞች ቀልብ የሚስብ መሆኑን እና በገበያው ላይ ምርትዎን ልዩ የሚያደርግ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡
  • ቀጣይ እርምጃ: አንዴ ዩቪፒዎ ግልጽ ከሆነ በኋላ ወደ ደረጃ 5 ይለፉ፡፡

ደረጃ 5: የደንበኛ ምድቦችን መግለጽ

ዓላማ: መፍትሄዎ የሚያገለግላቸውን የተወሰኑ የሰዎች ቡድኖች መለየት፡፡

  • ምን እንደሚያደርጉ:
    • የደንበኛ ምድቦችን መገምገም: የገጠር አባወራዎች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ቤተሰቦች፣ በሴት እማወራዎች የሚመሩ ቤተሰቦች፡፡
    • ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በቦታ አቀማመጥ፣ የገቢ ደረጃ ወይም ሥነ ሕዝብ ላይ ተመስርተው በተለያዩ ምድቦች ይመድቡ፡፡
  • መመሪያ: የእያንዳንዱን ምድብ ልዩ ፍላጎቶች ለማሟላት የገበያና የስርጭት ስትራቴጂዎችዎን ይጨምሩ፡፡
  • ቀጣይ እርምጃ: የደንበኛ ምድቦችን ከገለጹ በኋላ ወደ ደረጃ 6 ይለፉ፡፡

ደረጃ 6: የግንኙነት መስመሮችን መምረጥ

ዓላማ: ትኩረት ያደረጉባቸው ደንበኞች ጋር የሚደርሱባቸውን እጅግ ውጤታማ መንገዶችን መምረጥ፡፡

  • ምን እንደሚያደርጉ:
    • የግንኙነት መስመሮችን መገምገም: የአካባቢ ገበያዎች፣ የማህበረሰብ አውደ ጥናቶች፣ ከኤንጂኦዎች ጋር የሚደረጉ ትብብሮች፡፡
    • ከደንበኛ ምድብዎና መፍትሄዎ ጋር የሚጣጣሙ የግንኙነት መስመሮችን ይዘርዝሩ (ምሳ፡ በገጠር በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ማከፋፈል)፡፡
  • መመሪያ: የተደራሽነት እና ተቀባይነት ደረጃዎችን ከፍ በሚያደርጉ የግንኙነት መስመሮች ላይ ያተኩሩ፡፡
  • ቀጣይ እርምጃ: አንዴ የግንኙነት መስመሮች ከተመረጡ በኋላ ወደ ደረጃ 7 ይለፉ፡፡

ደረጃ 7: የወጪ መዋቅርን መተንተን

ዓላማ: የንግድ ስራዎን ለመጀመር እና ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ወጪዎችን መለየት፡፡

  • ምን እንደሚያደርጉ:
    • የወጪ መዋቅሩን መገምገም: የማምረቻ ወጪዎች፣ የገበያ ወጪዎች፣ የማከፋፈያ ሎጅስቲክስ፡፡፡
    • የመጀመሪያ ኢንቨስትመንት እና ተደጋጋሚ ወጪዎችን ጨምሮ ቋሚና ተለዋዋጭ ወጪዎችን ይመድቡ፡፡
  • መመሪያ: ሀብቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመመደብ እና አላስፈላጊ ወጪዎችን ለማስቀረት ይህን ትንተና ይጠቀሙ፡፡
  • ቀጣይ እርምጃ: ወጪዎን ከተነተኑ በኋላ ወደ ደረጃ 8 ይለፉ፡፡

ደረጃ 8: የገቢ ማግኛ መንገዶችን መለየት

ዓላማ: የንግድ ሥራዎ እንዴት ገቢ እንደሚያመጣ መወሰን፡፡

  • ምን እንደሚያደርጉ:
    • የገቢ ማግኛ መንገዶችን መገምገም: የማብሰያ ምድጃዎች ቀጥተኛ ሽያጭ፣ የተተኪ መለዋወጫዎች ትእዛዝ ሞዴል፣ የትብብር ማበረታቻዎች፡፡
    • ከንግድ ስራ ሞዴልዎ እና የደንበኛ ምርጫዎች ጋር የሚስማሙ ሊሳኩ የሚችሉ የገቢ ምንጮችዎን ይዘርዝሩ፡፡
  • መመሪያ: ተጨባጭና የረጅም ጊዜ ዘላቂነት ባላቸው የገቢ ማግኛ መንገዶች ላይ ያተኩሩ፡፡
  • ቀጣይ እርምጃ: አንዴ የገቢ ማግኛ መንገዶችዎን ከለዩ በኋላ ወደ ደረጃ 9 ይለፉ፡፡

 

ደረጃ 9: የተማሩትን ትምህርት መተግበር

ዓላማ: የንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅዎን ሁሉንም ክፍሎች በንግድ ሥራ እቅድዎ ውስጥ ያቀናጁ፡፡

  • ምን እንደሚያደርጉ:
    • ለንጹህ የማብሰያ ምርት የተሟላ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅ ለማዘጋጀት ከደረጃ 1-8 ያሉትን ግኝቶችዎን ያጣምሩ፡፡
    • ስትራቴጂዎን በመረጃ ለማስደገፍ ሀሳቦቹን ይጠቀሙ፣ ከፍተኛ ውጤት ለሚያስገኙ ስራዎች ቅድሚያ ይስጡ፣ እንዲሁም ከደንበኛ ፍላጎቶችና ሰፊ ግቦች ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን ያረጋግጡ፡፡
  • መመሪያ: የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን በግብረ መልስ እና የገበያ ሂደቶች እያደገ እንደሚሄድ ህያው ሰነድ አድርገው ይመልከቱ፡፡
  • ቀጣይ እርምጃ: በንጹህ የምግብ ማብሰያ ዘርፍ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ የንግድ ሥራዎን በማዘጋጀት ወደፊት ለመቀጠል ዝግጁ ነዎት፡፡
Scroll to Top