Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ ችግርን መለያ ደረጃ በደረጃ የአሰራር ሂደት

ይህ መመሪያ የተዘጋጀው አዳዲስ የስራ ፈጣሪዎችን ችግርን የመለየት ሂደትን ደረጃ በደረጃ ለመጠቀም እንዲረዳቸው ታስቦ ነው፡፡ መመሪያው የተደራጀና የትምህርት ተሞክሮን በማረጋገጥ መሳሪያዎችን እና ቴምፕሌቶችን እንዴት በብቃት መጠቀም እንደሚቻል በተመለከተ ግልጽ መመሪያዎችን ይሰጣል፡፡

ደረጃ 1: ዐውዱን በመረዳት መጀመር

ዓላማ: እራስዎን ከንጹህ የማብሰያ ዘርፉ እና ተግዳሮቶቹ ጋር ማስተዋወቅ፡፡

  • በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ውስጥ ችግርን መለየት ለምን ወሳኝ እንደሆነ ለመረዳት የትምህርቱን ዋና ዋና ሀሳቦች (በዚህ ሞጁል ውስጥ ቀደም ሲል የቀረቡትን) በማንበብ ይጀምሩ፡፡
  • እንደ በባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ መሆን፣ በቤት ውስጥ አየር መበከል ምክንያት የሚመጡ የጤና ስጋቶች እንደ የዋጋ ተመጣጣኝነት ችግሮች ያሉ የጋራ ችግሮችን ይግለጹ፡፡
  • ከንግድ ስራ ሀሳብዎ ወይም ማህበረሰብዎ ጋር የሚዛመዱ የትኛውንም ልዩ ችግሮች በማስታወሻ ይያዙ፡፡

ቀጣይ እርምጃ: አንዴ ስለ አውዱ መሰረታዊ ግንዛቤ ካገኙ በኋላ ወደ ደረጃ 2 ይለፉ፡፡

ደረጃ 2: የችግር መለያ ወርክሺቱን መሙላት

ዓላማ: ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞችን የሚያጋጥሟቸውን ዋና ዋና ችግሮች መለየት እና መግለጽጽ፡

  • ቀደም ሲል የቀረበውን የችግር መለያ ወርክሺት ቴምፕሌት ያውርዱ፡፡
  • ወርክሺቱን ለመሙላት እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ:
    1. ዋና ዋና ችግሮችን መለየት: በባህላዊ የምግብ ማብሰያ ዘዴዎች ላይ ጥገኛ የሆኑ ቤተሰቦችን የሚያጋጥሟቸውን ከ3–5 ዋና ዋና ችግሮች ይዘርዝሩ፡፡ እንደ ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች፣ የጤና ስጋቶች ወይም ግንዛቤ ማጣት ያሉ ምሳሌዎችን ይጠቀሙ፡፡
    2. ችግሮቹን ማረጋገጥ: እነዚህን እንዴት እውነተኛና አግባብነት ያላቸው እንደሆኑ እንዳረጋገጡ ይግለጹ፡፡ ቃለ መጠይቆች፣ የዳሰሳ ጥናቶች ወይም ምልከታዎች አካሂደዋል? የተጠቀሙባቸውን ዘዴዎች እና ግኝቶችዎን ይመዝግቡ፡፡
    3. መፍትሄዎን ማስማማት: የንግድ ስራ ሀሳብዎ እንዴት እያንዳንዱን የተለዩትን ችግሮች እንደሚፈታ ያብራሩ፡፡ ስለሚያቀርቡት መፍትሄ ጥቅሞች ግልጽ ይሁኑ፡፡

መመሪያ: ከየት እንደሚጀምሩ እርግጠኛ ካልሆኑ መነሳሻ ለማግኘት የሰላማዊት ከበደን የጉዳይ ጥናት ምሳሌ ተመልሰው ይመልከቱ፡፡

ደረጃ 3: ቴምፕሌቱን በመጠቀም የደንበኛ ችግሮችን ማወቅ

ዓላማ: የተለያዩ የደንበኛ ምድቦችን የሚያጋጥሙ ልዩ ችግሮችን በአይነ ህሊናዎ መመልከት፡፡

  • የደንበኛ ችግሮችን ማወቂያ ቴምፕሌቱን ይክፈቱ፡፡
  • እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ:
    1. የደንበኛ ምድብዎን መግለጽ:  በአንድ ጊዜ አንድ የደንበኛ ምድብ ይምረጡ (ምሳ፡ የገጠር አባወራዎች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ቤተሰቦች)፡፡
    2. ችግሮችን መዘርዘር: ለእያንዳንዱ የደንበኛ ምድብ ውስጥ ከምግብ ማብሰያ አሰራሮች ጋር በተያያዘ ልዩ ተግዳሮቶችዎን ይለዩ፡፡ 
    3. ወቅታዊ መፍትሄዎችን መተንተን: የትኛውንም አሁን ያሉ መፍትሄዎችን እና ውሱንነቶችዎን ይገንዘቡ፡፡
    4. እድሎችን መለየት: የንግድ ስራዎ አሁን ያሉ መፍትሄዎችን ሊያሻሽል ወይም ክፍተቶችን ሊደፍን የሚችልባቸውን መንገዶች ይጠቁሙ፡፡

ጠቃሚ ምክር: በመጀመሪያ ሙከራውን መሰራት የሚችል ለማድረግ በአንድ የደንበኛ ምድብ ላይ ያተኩሩ፡፡ ሂደቱን ቆይተው ለተጨማሪ የደንበኛ ምድቦች ሊደግሙት ይችላሉ፡፡ 

ቀጣይ እርምጃ: አንድ ጊዜ የደንበኛ ምድቦችን ማወቅዎን ካረጋገጡ በኋላ ወደ ደረጃ 4 ይለፉ፡፡

ደረጃ 4: የማረጋገጫ ዝርዝሩን በመጠቀም ግኝቶችዎን ማረጋገጥ

ዓላማ: የተለዩት ችግሮችዎ እውነተኛና የተግባር መሆናቸውን ማረጋገጥ፡፡

  • ግኝቶችዎን በብልሀት ለማረጋገጥ የችግር ማረጋገጫ ዝርዝሩን ይጠቀሙ፡፡
  • የሚከተሉትን ደረጃዎች ይከተላሉ:
    1. ዳታ መሰብሰብ: ቃለ መጠይቆች ያድርጉ፣ የዳሰሳ ጥናቶችን ያሰራጩ ወይም በደንበኛ ባህሪያት ላይ ምልከታ ያድርጉ፡፡ ስራዎችዎን በማረጋገጫ ዝርዝሩ ላይ ይመዝግቡ፡፡
    2. ግብረ መልስ መተንተን: ከዳታ ስብሰባ ጥረቶችዎ ያገኟቸውን ፓተርኖች እና ሀሳቦች ያጠቃሉ፡፡
    3. እሳቤዎችን መሞከር: ለመፍትሄዎ የመጀመሪያ ሙከራ ወይም የማስመሰያ ሙከራ ያዘጋጁ እና ይህን በአነስተኛ የደንበኞች ቡድን ላይ ይሞክሩ፡፡ የሚያገኙትን ግብረ መልስ ይመዝግቡ፡፡
    4. አቀራረብዎን ማጥራት: በአዳዲስ ሀሳቦች ላይ ተመስርተው በችግር ዝርዝርዎ ላይ ማሻሻያ ያድርጉ እንዲሁም የንግድ ስራ ሀሳብዎን በዚሁ መሰረት ያስተካክሉ፡፡

መመሪያ: እስካሁን የመጀመሪያ ሙከራ ካላዘጋጁ በቃለ መጠይቆች እና ምልከታዎች አማካኝነት የይዘት ዳታ በመሰብሰብ ላይ ያተኩሩ፡፡

ቀጣይ እርምጃ: ግኝቶችዎን ካረጋገጡ በኋላ ወደ ደረጃ 5 ይለፉ፡፡

ደረጃ 5: የምሳሌ የጉዳይ ጥናቱን መመልከት

ዓላማ: ከእውነተኛው ዓለም ስኬታማ ችግርን የመለየት ምሳሌ መማር፡፡

  • የጉዳይ ጥናቱን ማንበብ: የሰላማዊት ማህበረሰቦችን በንጹህ የማብሰያ ምድጃዎች የማብቃት ጉዞ፡፡
  • ሰላማዊት እንዴት የሚከተሉትን እንዳደረገች ትኩረት ይስጡ:
    • እንዴት የማህበረሰቧን ዋና ዋና ችግሮች እንደለየች፡፡
    • እንዴት እሳቤዎቿን በቃለ መጠይቆችና ሙከራ እንዳረጋገጠች፡፡
    • እንዴት ለደንበኛ ፍላጎቶች ተስማሚ መፍትሄ እንዳዘጋጀች፡፡
    • እንዴት በግብረ መልስ ላይ ተመስርታ እንደደገመችና ውጤቷን እንዳሳደገች፡፡

የገለጻ ጥያቄዎች:

  • የሰላማዊት አቀራረብ ከእርስዎ ጋር እንዴት ይነጻጸራል?
  • እሷ የተጠቀመቻቸው ለራስዎ የንግድ ስራ ሀሳብ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው ስትራቴጂዎች አሉ?

መመሪያ: ከጉዳይ ጥናቱ የተወሰዱ ዋና ዋና ሀሳቦችን ያብራሩ እና እነዚህ እንዴት ለእርስዎ ስራ መረጃ ሊሰጡ እንደሚችሉ ያስቡ፡፡

ቀጣይ እርምጃ: በተመራጭ አሰራሮች ላይ ግልጽ ግንዛቤ ካገኙ በኋላ ወደ ደረጃ 6 ይለፉ፡፡

 

ደረጃ 6: የችግር መለያ ሪፖርትዎን ማጠናቀቅ

ዓላማ: ግኝቶችዎን ወደ አጠቃላይ ሪፖርት ማጠናቀር፡፡

  • ሁሉንም የተጠናቀቁ ቴምፕሌቶችዎን (የችግር መለያ ወርክሺት፣ የደንበኛ ችግሮች ማወቂያ፣ የችግር ማረጋገጫ ዝርዝር) ወደ አንድ ሰነድ ይሰብስቡ፡፡
  • የሚከተሉትን የሚይዝ ማጠቃለያ ይጻፉ:
    1. የለዩዋቸውን ዋና ዋና ችግሮች፡፡
    2. እነዚህን ችግሮች እንዴት እንዳረጋገጡ፡፡
    3. የንግድ ስራ ሀሳብዎ እንዴት እነዚህን ችግሮች እንደሚፈታ፡፡
    4. በራስ ከመማር ሂደቱ የተገኙ ዋና ዋና ትምህርቶች፡፡

መመሪያ: ሪፖርትዎን ለወደፊት እቅድ ዝግጅት በማጣቀሻነት እንዲያገለግል ለማድረግ አጭር ነገር ግን በቂ ዝርዝሮችን እንዲይዝ ያድርጉ፡፡

ቀጣይ እርምጃ: ግብረ መልስ ለማግኘት ሪፖርትዎን ለአማካሪ ወይም እኩያዎ ያጋሩ፡፡ ይህን ማድረግዎ ግንዛቤዎን እንዲያጠሩ እና ችግር የመለየት ክህሎቶችዎን እንዲያጠናክሩ ይረዱዎታል፡፡

ደረጃ 7: የተማሩትን ትምህርት መተግበር

ዓላማ: ችግርን ከመለየት ወደ መፍትሄ ማዘጋጀት መሸጋገር፡፡

  • የተጠናቀቀ ሪፖርትዎን ምርትዎን ወይም አገልግሎትዎን ለማዘጋጀት መሰረት አድርገው ይጠቀሙበት፡፡
  • ከተለዩት ችግሮች ጋር ሊስማሙ የሚችሉ መፍትሄዎችን ማሰላሰል ይጀምሩ፡፡
  • የንግድ ስራ ሞዴልዎን ለማወቅ ወደ ኋላ ተመልሰው የንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ ማእቀፉን (በሞጁል 1 ውስጥ የተገለጸው) ይመልከቱ፡፡

ጠቃሚ ምክር: ችግርን መለየት የሚደጋገም ሂደት እንደሆነ ያስታውሱ፡፡ መፍትሄዎን በማዘጋጀት ላይ ሳሉ ግብረ መልስ መሰብሰብዎን እና አቀራረብዎን ማጥራትዎን ይቀጥሉ፡፡

Scroll to Top