Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ዓላማ: የደንበኛ ጥቅም ማወቂያ ቴምፕሌቱን በመጠቀም የደንበኛ ጥቅሞችን ይለዩና ቅደም ተከተል ይስጡ፡፡

መመሪያዎች

  1. መፍትሄዎ የሚያቀርባቸውን ከ2-4 ዋና ዋና ጥቅሞች ለመዘርዘር የደንበኛ ጥቅም ማወቂያ ቴምፕሌቱን ይጠቀሙ፡፡
  2. እነዚህ ጥቅሞች ለምን ለትኩረት ደንበኞችዎ እንደሚጠቅሙ ያብራሩ፡፡
  3. መፍትሄዎ እንዴት እያንዳንዱን ጥቅም እንደሚያቀርብ ይግለጹ፡፡
  4. የተጠናቀቀውን የደንበኛ ማወቂያ ግብረ መልስ ለማግኘት ለእኩያ ወይም አማካሪ ያጋሩ፡፡

የግምገማ መስፈርት

  • ጥቅሞች ተዘርዝረዋል: ተገቢና ውጤት አምጪ ጥቅሞች ተለይተዋል (3 ነጥቦች)፡፡
  • ይህ ለምን እንደሚጠቀም: ጥቅሞቹ ለምን ለደንበኞች ተስማሚ እንደሆኑ የተመለከተ ግልጽ ማብራሪያ (3 ነጥቦች)፡፡
  • እንዴት እንደሚቀርብ: መፍትሄዎ ጥቅሞቹን እንዴት እንደሚያቀርብ የተመለከተ ማብራሪያ (3 ነጥቦች)፡፡
  • ግልጽት እና አደረጃጀት: የደንበኛ ጥቅሞች ማወቂያው ለማንበብ ቀላልና በቅደም ተከተል የተዋቀረ ነው (1 ነጥብ)

ጠቅላላ ውጤት: 10 ነጥቦች

የተመደ ሰዓት: 15 ደቂቃዎች

Scroll to Top