Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ዓላማ: የቀረበውን ቴምፕሌት በመጠቀም የደንበኛ ችግሮችን ማወቅን መለማመድ፡፡

መመሪያዎች

  1. ልዩ የደንበኛ ምድብ ይምረጡ (ምሳ፡ በገጠር አካባቢዎች የሚኖሩ በሴት እማወራዎች የሚመሩ ቤተሰቦች)፡፡
  2. ችግሮችን ለመዘርዘር፣ ወቅታዊ መፍትሄዎችን ለመተንተን እና የማሻሻያ እድሎችን ለመለየት የደንበኛ ችግሮችን ማወቂያ ቴምፕሌቱን ይጠቀሙ፡፡
  3. ግብረ መልስ ለማግኘት የተጠናቀቀውን ቴምፕሌትዎን ለእኩያዎ ወይም አማካሪዎ ያጋሩ፡፡

የግምገማ መስፈርት

  • የተዘረዘሩት ችግሮች: የተለዩት አጠቃላይ እና ተገቢ ችግሮች (4 ነጥቦች)፡፡
  • የተተነተኑ ወቅታዊ መፍትሄዎች: የነባር መፍትሄዎች እና የእርስዎ ውሱንነቶች በግልጽ መብራራት (4 ነጥቦች)፡፡
  • የተለዩት እድሎች: ለማሻሻያ የተሰጡት ሀሳቦች የተግባርና የፈጠራ መሆን (4 ነጥቦች)፡፡
  • ግልጽትና አደረጃጀት: የችግር ማወቂያ ንድፉ ለማንበብ ቀላል መሆን እና በቅደም ተከተል መደራጀት (2 ነጥቦች)፡፡

ጠቅላላ ውጤት: 14 ነጥቦች

የተመደበ ሰዓት: 25 ደቂቃዎች

Scroll to Top