Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ዓላማ: የወጪ መዋቅር ትንተና ቴምፕሌቱን በመጠቀም የንግድ ስራዎን ለመጀመርና ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን መተንተን፡፡

መመሪያዎች

  1. ቋሚና ተለዋዋጭ ወጪዎችዎን ለመመደብ የወጪ መዋቅር ትንተና ቴምፕሌቱን ይጠቀሙ፡፡
  2. የንግድ ስራዎን ለመጀመር የሚያስፈልጉ የመጀመሪያ ኢንቨስትመንት ወጪዎችን ያካቱ፡፡
  3. የእያንዳንዱን ምድብ ወርሀዊ ወጪዎችን ይገምቱ፡፡ 
  4. ግብረ መልስ ለማግኘት የተጠናቀቀውን ትንተናዎን ለእኩያ ወይም አማካሪ ያጋሩ፡፡

የግምገማ መስፈርት

  • የወጪ ምድቦች: ቋሚና ተለዋዋጭ ወጪዎች በግልጽ ተመድበዋል (4 ነጥቦች)፡፡
  • የመጀመሪያ ኢንቨስትመንት: እንደ የመጀመሪያ ሙከራ ወይም ማረጋገጫዎች ያሉ ቀጣይ ወጪዎች ተካተዋል (3 ነጥቦች)፡፡
  • ወርሀዊ ግምቶች: ለወርሀዊ ወጪዎች አሳማኝ ግምቶች ተሰጥተዋል (3 ነጥቦች)፡፡

ጠቅላላ ውጤት: 10 ነጥቦች

የተመደበ ሰዓት: 15 ደቂቃዎች

Scroll to Top