Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ዓላማ: የትኩረት ደንበኛዎን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ዝርዝር የደንበኛ ማንነት መግለጫዎች ያዘጋጁ፡፡

መመሪያዎች

  1. ከ2-3 የማንነት መግለጫዎች ለማዘጋጀት የማንነት መግለጫ ዝግጅት ቴምፕሌቱን ይጠቀሙ፡፡
  2. እንደ እድሜ፣ ጾታ፣ ስራ፣ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ እንቅፋቶችና ተነሳሽነቶች የመሳሰሉ ዝርዝሮችን ያካቱ፡፡
  3. ግብረ መልስ ለማግኘት የተጠናቀቀ የማንነት መግለጫዎን ለእኩያ ወይም አማካሪ ያጋሩ፡፡

 

የግምገማ መስፈርት

  • የማንነት መግለጫ ዝርዝሮች: አጠቃላይ እና እውነተኛ ባህሪያት ተካተዋል (4 ነጥቦች)፡፡
  • እንቅፋቶችና ተነሳሽነቶች: ተግዳሮቶችና ገፋፊዎች በግልጽ ተገልጸዋል (4 ነጥቦች)፡፡
  • አግባብነት: የማንነት መግለጫዎቹ ከተለዩት የደንበኛ ምድቦች ጋር ይጣጣማሉ (4 ነጥቦች)፡፡
  • ግልጽነት እና አደረጃጀት: የማንነት መግለጫዎቹ ለማንበብ ቀላልና በቅደም ተከተል የተዋቀሩ ናቸው (2 ነጥቦች፡፡

ጠቅላላ ውጤት: 14 ነጥቦች

የተመደበ ሰዓት: 20 ደቂቃዎች

Scroll to Top