Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ዓላማ: የቀረበውን ቴምፕሌት በመጠቀም የትኩረት ደንበኞችዎን መመደብን እንዲለማመዱ፡፡

መመሪያዎች

  1. የደንበኛ ምደባ ቴምፕሌቱን ያውርዱ፡፡
  2. ከ2–3 የተለያዩ የደንበኛ ምድቦችን ይለዩ (ምሳ፡ የገጠር አባወራዎች፣ የከተማ ነዋሪዎች)፡፡
  3. ለእያንዳንዱ ምድብ በሥነ ህዝብ፣ ባህሪያት፣ ልዩ ችግሮች እና ተስማሚ መፍትሄዎች ይሙሉ፡፡
  4. የተጠናቀቀውን ቴምፕሌትዎን ለግምገማ ያስገቡ፡፡

የግምገማ መስፈርት

  • የተለዩ ምድቦች: ግልጽና ነአግባብነት ያላቸው የደንበኛ ቡድኖች ተዘርዝረዋል (4 ነጥቦች)፡፡
  • የቀረቡ ዝርዝሮች: ሥነ ህዝብ፣ ባህሪያት እና ልዩ ችግሮች በአግባቡ ተገልጸዋል (4 ነጥቦች)፡፡
  • ተስማሚ መፍትሄዎች: መፍትሄዎች የእያንዳንዱን ምድብ ልዩ ፍላጎቶች ይፈታሉ (4 ነጥቦች)፡፡
  • አጠቃላይ የተሟላ መሆን: ሁሉም የቴምፕሌቱ ክፍሎች በጥንቃቄ ተሞልተዋል (2 ነጥቦች)

ጠቅላላ ውጤት: 14 ነጥቦች

የተመደበ ሰዓት: 20 ደቂቃዎች

Scroll to Top