Course Content
ምእራፍ 3፡ ደንበኛን ያማከለ ትኩረት
ፍቺ/ትርጉም ደንበኛን ያማከለ ትኩረት ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ደንበኞች በጥልቀት የመገንዘብ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚያሟላና ችግሮቻቸውን የሚፈቱ መፍትሄዎችን የማዘጋጀት አሰራር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ ዘርፍ አውድ ይህ ደንበኞችን በስነ ህዝብ (ምሳ፡ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ገቢ)፣ ባህሪ (ምሳ፡ የምግብ ማብሰያ ልማዶች፣ የማገዶ ምርጫዎች) እና ልዩ ፍላጎቶች (ምሳ፡ ለገጠር አባወራዎች የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ ለከተማ ነዋሪዎች አመቺነት) ላይ ተመስርቶ ደንበኞችን መክፈልን ይይዛል፡፡ ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ በመከተል ስራ ፈጣሪዎች መፍትሄዎቻቸው አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን፣ ተደራሽ መሆናቸውን እና ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
0/12
በተግባር የመጀመሪያ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅዎን ማዘጋጀት – በአማርኛ

ዓላማ: የችግር መለያ ወርክሺት ቴምፕሌቱን ለግምታዊ ወይም ለእውነተኛ ዓለም ኩነት ይጠቀሙ፡፡

መመሪያዎች

  1. የደንበኛ ምድብ ይምረጡ (ምሳ፡ የገጠር አባወራዎች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ቤተሰቦች)፡፡
  2. ዋና ዋና ችግሮችን በመለየት፣ በማረጋገጥ እና ከመፍትሄዎ ጋር በማስማማት ወርክሺትዎን ያጠናቁ፡፡
  3. የተጠናቀቀ ወርክሺትዎን ለግምገማ ያስገቡ፡፡

የግምገማ መስፈርት

  • የተለዩ ዋና ዋና ችግሮች: የሚዘረዘሩ ግልጽና አግባብነት ያላቸው ችግሮች (4 ነጥቦች)፡፡
  • የማረጋገጫ ሂደት: የተገለጹትን ችግሮች ለማረጋገጥ ጥቅም ላይ የዋሉ ዘዴዎች (4 ነጥቦች)፡፡
  • መፍትሄን ማስማማት: መፍትሄው ችግሮቹን እንዴት እንደሚፈታ የተሰጠው ማብራሪያ ቅደም ተከተል ያለውና ውጤት ተኮር መሆን (4 ነጥቦች)፡፡
  • አጠቃላይ ሙሉነት: የወርክሺቱ ሁሉም ክፍሎች በጥንቃቄ መሞላት (2 ነጥቦች)፡፡

ጠቅላላ ውጤት: 14 ነጥቦች

የተመደበ ሰዓት: 30 ደቂቃዎች

 

 

Scroll to Top