ጽዎታዎችን ያማከለ ከባቢ የመፍጠር ስልጠና

ከዚህ በታች የቀረቡት ሴት ስራ ፈጣሪዎችን የንግድ ስራ በሚጀምሩበት ወይም በሚያሳድጉበት ወቅት ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ችግሮችን እንዲገልጹና እንዲፈቱ ለመርዳት ታስበው የተዘጋጁ የተግባር ቴምፕሌቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ቴምፕሌቶች ተማሪዎችን እንቅፋቶችን በመለየት፣ ተጽእኗቸውን በመተንተን እና ችግሮቹን የሚፈቱባቸውን የተግባር ስትራቴጂዎች በማዘጋጀት ረገድ መመሪያ ይሰጧቸዋል፡፡

 

  1. የችግር መለያ ቴምፕሌት

ይህ ቴምፕሌት ሴት ስራ ፈጣሪዎችን የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በብልሀት እንዲለዩና እንዲመድቡ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የችግር መለያ

ስም: ____________________________
የንግድ ሥራ ሀሳብ: ___________________________

 

ምሳሌ

የችግር ምድብ

ልዩ ችግር

በንግድ ሥራ ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ

ሊሰሩ የሚችሉ መፍትሄዎች

የማህበረሰብ አድልዎዎች

የባህላዊ አሰራሮች የአመራርነት ችሎታዎችን መጠራጠር

ተአማኒነትን እና ለኔትወርኮች ተደራሽነትን መገደብ

የድጋፍ ኔትወርኮችን ማሳደግ፣ የስኬት ታሪኮችን ማብራራት

የገንዘብ ድጋፍ ተደራሽነት ውሱንነት

የብድር ማስያዣ ወይም የፋይናንስ እውቀት አለመኖር

እድገትና ሀብቶችን ማግኘትን ይገድባል

ከማይክሮፋይናንስ ተቋማት ጋር ትብብር መፍጠር

የቤተሰብ ኃላፊነቶችን ማመጣጠን

በልጅ እንክብካቤ ስራዎች የተነሳ የጊዜ እጥረት ማጋጠም

ለንግድ ሥራ የሚሰጥ ትኩረትን መቀነስ

የጊዜ አጠቃቀም መሳሪያዎችን መጠቀም፣ ስራዎችን መመደብ

በወንድ የበላይነት የሚመሩ የአቅርቦት ሰንሰለቶች

በፍትሀዊ ስምምነቶች ላይ ለመደራደር ወይም የድጋፍ ምንጮችን ለማግኘት መቸገር

የአቅርቦት ሰንሰለት ውጤታማነትን መገደብ

በሴቶች ከሚመሩ ህብረትሥራ ማህበራት ጋር ትብብር መፍጠር

የምክርና ኔትወርኮች አለመኖር

የመመሪያ ወይም ሙያዊ ግንኙነቶች ውሱን መሆን

የችግር አፈታትና ውሳኔ አሰጣጥን መገደብ

የስራ ፈጣሪ ቡድኖችን መቀላቀል፣ አማካሪዎች መፈለግ

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም የባህል ተቃውሞ

በባህላዊ አሰራሮች የተነሳ አዳዲስ መፍትሄዎችን ለመቀበል ማመንታት

የመቀበል ደረጃዎችን ማዘግየት 

የግንዛቤ ፈጠራ ዘመቻዎችን ማካሄድ፣ መፍትሄዎችን ማስማማት

 

መመሪያዎች:

  • በእያንዳንዱ ምድብ ስር ልዩ ችግሮችን ይዘርዝሩ፡፡
  • እያንዳንዱ ችግር በንግድ ሥራዎ ላይ የሚፈጥረውን ተጽእኖ ይተንትኑ፡፡
  • እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ሊሰሩ የሚችሉ መፍትሄዎችን ያሰላስሉ፡፡

መመሪያ: ይህን ቴምፕሌት የሚያጋጥሙዎትን ችግሮች በግልጽ ለማወቅ እና ችግሮቹን የሚፈቱ የተግባር መንገዶች ለማጥናት ይጠቀሙበት፡፡

 

  1. የማህበረሰብ አድልዎዎች መግለጫ ቴምፕሌት

ይህ ቴምፕሌት ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የማህበረሰብ አድልዎዎችና የማይቀየሩ አመለካከቶችን እንዲገልጹና እነዚህን የሚፈቱ ስትራቴጂዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የማህበረሰብ አድልዎዎች መግለጫ

ስም: ____________________________
የንግድ ሥራ ሀሳብ: ___________________________

 

ምሳሌ

አድልዎ/የማይቀየር አስተሳሰብ 

ይህ በእኔ/የንግድ ሥራዬ ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚፈጥር

የመፍትሄ ስትራቴጂዎች

“ሴቶች ጥሩ መሪዎች አይደሉም”

በራስ መተማመንና ተአማኒነትን ይጎዳል

የአመራርነት ስኬቶችን ማብራራት፣ ማረጋገጫዎችን ማሳየት

“ሴቶች ገንዘብ ማስተዳደር አይችሉም”

ለገንዘብ ድጋፍ እድሎች ተደራሽነትን ይገድባል

የፋይናንስ እውቀትን ማሻሻል፣ የገንዘብ አጠቃቀም ክህሎቶችን ማሳየት

“ሴቶች ከንግድ ሥራ ይልቅ ለቤተሰብ ቅድሚያ መስጠት አለባቸው”

የጥፋተኝነት ስሜት ይፈጥራል ወይም ከስራ ድርሻዎች መካከል ለመምረጥ ጫና ይፈጥራል

ሁለቱንም የሥራ ድርሻዎች የማመጣጠን ጥቅምን መግለጽ፣ አመቺ ዝግጅቶችን ማድረግ

“ሴቶች በወንድ የበላይነት በሚመሩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ቦታ የላቸውም”

ከኔትወርኮች ወይም እድሎች መገለልን ያስከትላል

ከሌሎች ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር ህብረት መመስረት፣ የኢንዱስትሪ ቡድኖችን መቀላቀል

 

መመሪያዎች:

  • ያጋጠሙዎትን ወይም እንደሚያጋጥሙዎት የሚገምቷቸው የማህበረሰብ አድልዎዎችን ይለዩ፡፡
  • እነዚህ አድልዎዎች በንግድ ስራዎ ወይም አመለካከትዎ ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚፈጥሩ ይግለጹ፡፡
  • እነዚህን አድልዎዎች የሚፈቱባቸውን እና ዝግጁነትዎን የሚያዳብሩባቸውን ስትራቴጂዎች ያዘጋጁ፡፡

መመሪያ: ይህን ቴምፕሌት የማይቀየሩ አመለካከቶችን አሳምነው ለማለፍና በስራ ፈጣሪነት ጉዞዎ ላይ በራስ መተማመንዎን ለማዳበር ይጠቀሙበት፡፡

 

  1. የገንዘብ ድጋፍ ተደራሽነት ማቀጃ

ይህ ቴምፕሌት ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን የገንዘብ ድጋፍ ተደራሽነት ውሱንነትን የሚፈታ እቅድ ለማጥናትና ለማዘጋጀት ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የገንዘብ ድጋፍ ተደራሽነት ማቀጃ

ስም: ____________________________
የንግድ ሥራ ሀሳብ: ___________________________

 

ምሳሌ  

የገንዘብ ድጋፍ ምንጭ

የብቁነት መስፈርት

የማግኛ ደረጃዎች

የጊዜ ሰሌዳ

የማይክሮፋይናንስ ተቋማት

አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች፣ በሴቶች የሚመሩ የንግድ ድርጅቶች

ማመልከቻ ማስገባት፣ በስልጠና ላይ መሳተፍ

1ኛ ወር

የመንግስት እርዳታዎች

ሴት ሥራ ፈጣሪዎች፣ በንጹህ የማብሰያ ዘርፍ ላይ ማተኮር

ፕሮግራሞችን ማጥናት፣ ፕሮፖዛል ማዘጋጀት

2ኛ ወር

የቡድን የገንዘብ ድጋፍ ፕላትፎርሞች

የፈጠራ ሀሳቦች፣ ጠንካራ በኦንላይን መገኘት

ዘመቻዎች ማዘጋጀት፣ በማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ማስተዋወቅ

3ኛ ወር

የአካባቢ የህብረት ሥራ ማህበራት

አባልነትን መሰረት ያደረጉ፣ ማህበረሰብ ተኮር ኢኒሺየቲቮች

በስብሰባዎች ላይ መሳተፍ፣ የንግድ ሥራ ሀሳብ ማቅረብ

1ኛ ወር

 

መመሪያዎች:

  • ሊሳኩ የሚችሉ የገንዘብ ድጋፍ ምንጮችን እና የብቁነት መስፈርታቸውን ይለዩ፡፡
  • እያንዳንዱን የድጋፍ ምንጭ ማግኛ ደረጃዎችን ይግለጹና የጊዜ ሰሌዳዎችን ይወስኑ፡፡

መመሪያ: ለሴት ሥራ ፈጣሪዎች ወይም የተገለሉ ማህበረሰቦች በልዩ ሁኔታ በተዘጋጁ የገንዘብ ድጋፍ አማራጮች ላይ ያተኩሩ፡፡

 

  1. የጊዜ አጠቃቀምን እና የቤተሰብ ኃላፊነትን ማመጣጠኛ ማቀጃ

ይህ ቴምፕሌት ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን የቤተሰብ ኃላፊነቶችን ከንግድ ሥራ ህልሞች ጋር እንዲያመጣጥኑ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የጊዜ አጠቃቀምን እና የቤተሰብ ኃላፊነትን ማመጣጠኛ ማቀጃ

ስም: ____________________________
የንግድ ሥራ ሀሳብ: ___________________________

 

ምሳሌ  

ስራ

የቅደም ተከተል ደረጃ (ከፍተኛ/መካከለኛ/አነስተኛ)

አስፈላጊው ጊዜ

የምደባ አማራጮች

የንግድ ሥራ ዕቅድ ዝግጅት

ከፍተኛ

10 ሰዓቶች/ ሳምንት

የጥናት ቡድን አባላት መመደብ

የቤተሰብ ኃላፊነቶች

ከፍተኛ

20 ሰዓቶች/ ሳምንት

ስራዎችን ለቤተሰብ አባላት ማከፋፈል

የኔትወርክ መፍጠሪያ ዝግጅቶች

መካከለኛ

5 ሰዓቶች/ ሳምንት

ከአካል ዝግጅቶች ይልቅ በቨርቹዋል ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ

የገበያ ዘመቻዎች

ከፍተኛ

8 ሰዓቶች/ ሳምንት

ለፍሪላንሰሮች መስጠት

 

መመሪያዎች:

  • ሁሉንም ከንግድ ስራዎና ከቤተሰብ ኃላፊነቶችዎ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥራዎች ይዘርዝሩ፡፡
  • የቅደም ተከተል ደረጃዎችን በመመደብ ለእያንዳንዱ ሥራ የሚያስፈልገውን ጊዜ ይገምቱ፡፡
  • ከፍተኛ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ስራዎች ነጻ ጊዜ ለማግኘት የመመደብ አማራጮችን ያጥኑ፡፡

መመሪያ: ጤናማ የሥራ-ህይወት ምጣኔን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ከፍተኛ ውጤት በሚያስገኙ ስራዎች ላይ ማተኮርዎን ለማረጋገጥ እንደ የቅደም ተከተል መስጫ ማትሪክሶች ያሉ መሳሪያዎችን ይጠቀሙ፡፡

 

  1. ለባህል አግባብነት ማረጋገጫ ዝርዝር

ይህ የማረጋገጫ ዝርዝር መፍትሄዎች ከአካባቢ ባህሎችና ምርጫዎች ጋር በሚስማማ መልኩ መዘጋጀታቸውን፣ የባህል ተቃውሞን የሚፈቱ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡

 

ቴምፕሌት: ለባህል አግባብነት ማረጋገጫ ዝርዝር (የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅን ይመልከቱ)

ስም: ____________________________
የንግድ ሥራ ሀሳብ: ___________________________

  • የአካባቢ የምግብ አበሳሰል ልማዶችን ለመረዳት የዳሰሳ ጥናቶች ወይም ቃለ መጠይቆች ያካሂዱ፡፡
  • ምርትዎን ከባህላዊ የምግብ አበሳሰል ዘዴዎች ጋር እንዲስማማ አድርገው ያዘጋጁ (ለምሳሌ፡ የምድጃ ክዳን መግጠም)፡፡
  • ለባህል አግባብነት ያለው ማሸጊያና የምርት ምልክት ይጠቀሙ፡፡
  • ምርትዎ እንዴት ለአካባቢ የምግብ ዝግጅቶች እንደሚሰራ ለማሳየት ገለጻ ያካሂዱ፡፡
  • የምርትዎን ለባህል ተስማሚነት ለማጥራት ምርትዎን ቀደም ብለው ከተጠቀሙ ተጠቃሚዎች ግብረ መልስ ይሰብስቡ፡፡

መመሪያዎች:

  • እያንዳንዱን ዝርዝር አንዴ ካጠናቀቁ በኋላ እንደተጠናቀቀ ምልክት ያድርጉበት፡፡
  • ይህን የማረጋገጫ ዝርዝር ምርትዎ ከትኩረት ደንበኞች ጋር የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ ይጠቀሙት፡፡

መመሪያ: ግምቶችን ይተዉ—የባህል ምርጫዎችን በጥናትና ግብረ መልስ አማካኝነት ያረጋግጡ፡፡

 

  1. የምክርና ኔትወርክ ማዘጋጃ ዕቅድ

ይህ ቴምፕሌት ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን የምክር ኔትወርኮችን እና የሙያ ግንኙነቶችን እንዲመሰርቱ ይረዳቸዋል፡፡

ቴምፕሌት: የምክርና ኔትወርክ ማዘጋጃ ዕቅድ

ስም: ____________________________
የንግድ ሥራ ሀሳብ: ___________________________

 

ድርጅት/ግለሰብ

የግንኙነቱ ዓላማዎች

የድርጊት ደረጃዎች

የጊዜ ሰሌዳ

የአካባቢ የሴት ሥራ ፈጣሪዎች ቡድን

ምክር ማግኘትና ተሞክሮ መጋራት

በስብሰባዎችና ውይይቶች ላይ መሳተፍ

1ኛ ወር

የኢንዱስትሪ ማህበር

ለኢንዱስትሪ ግንዛቤዎችና የድጋፍ ምንጮች ተደራሽ መሆን

አባልነትን መቀላቀል፣ በአውደ ጥናቶች ላይ መሳተፍ

2ኛ ወር

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም

የገንዘብ ድጋፍና የፋይናንስ ምክርን ማረጋገጥ

የምክር የጊዜ ሰሌዳ መያዝ፣ ማመልከቻ ማስገባት

3ኛ ወር

የማህበረሰብ መሪ

እምነትን ማዳበርና ለባህል አግባብነትን ማስተዋወቅ

በግንዛቤ ፈጠራ ዘመቻዎች ላይ መተባበር

2ኛ ወር

 

መመሪያዎች:

  • ምክር ወይም ድጋፍ ሊሰጡዎ የሚችሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦችን ይለዩ፡፡
  • ከእነዚህ ጋር መገናኛ የድርጊት ደረጃዎችን ያብራሩና የጊዜ ሰሌዳዎችን ይወስኑ፡፡

መመሪያ: ኔትወርኮችን መመስረት ችግሮችን ለመቅረፍና ለድጋፍ ምንጮች ተደራሽ ለመሆን ወሳኝ ነው፡፡

Scroll to Top