የ24 ዓመቱ የአዲስ አበባ ነዋሪ የኮሌጅ ተመራቂ የሆነችው ነብያት ሁልጊዜም የአካባቢና የማህበረሰብ ችግሮችን የመፍታት ህልም አላት፡፡ በአካባቢ ሳይንስ የዲግሪ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ የጭስ ልቀቶችን ለመቀነስ እና የምግብ አበሳሰል ውጤታማነትን ለማሻሻል ታስበው የተዘጋጁ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው፣ ለአካባቢ ተስማሚ ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችን አምርታ የምታቀርብበት የንግድ ስራ ለመጀመር ትወስናለች፡፡

ዓላማዋ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ቤተሰቦችን በባህላዊ የምግብ ማብሰያ ዘዴዎች የተነሳ የሚያጋጥሟቸውን ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች እና ተያያዥ የጤና ስጋቶች መፍታት ነው፡፡ ሆኖም እንደ ወጣት ሴት ሥራ ፈጣሪ ነብያት ዝግጁነቷን እና የፈጠራ ችሎታዋን የሚፈታተኑ የተለያዩ ችግሮች ያጋጥሟታል፡፡
ነቢያትን ካጋጠሟት የመጀመሪያ መሰናክሎች ውስጥ አንደኛው የማህበረሰብ አድልዎዎች ናቸው፡፡ ቤተሰቧና ማህበረሰቧ የንግድ ድርጅት የመምራት ችሎታዋን ከመጠራጠር ባለፈ በአብዘኛው በገንዘብ አያያዝና የሥራ ፈጣሪነት የስራ ፍላጎቶችን ማሳካት በመቻል ችሎታዋ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ እነዚህን የማይቀየሩ አመለካከቶች ለመፍታት ነብያት አንድ የአካባቢ የሴት ሥራ ፈጣሪዎች ቡድንን ትቀላቀል እና ምክር ከማግኘት በተጨማሪ ተመሳሳይ ችግሮች ካጋጠሟቸው ሌሎች ሴቶች ጋር ተሞክሯቸውን ትጋራለች፡፡ ይህ ኔትወርክ በራስ መተማመኗን ማሳደግ ብቻም ሳይሆን የሥራ ፈጣሪነት ምህዳርን የምትጠቀምበት ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ይሰጣታል፡፡

ሌላኛው ከፍተኛ ችግር የገንዘብ ድጋፍ ተደራሽነት ውሱንነት ነው፡፡ ነብያት ምንም የብድር ማስያዣ የሌላት የቅርብ ተመራቂ እንደመሆኗ ከመደበኛ ባንኮች ብድር የማግኘት ችግር ያጋጥማታል፡፡ የገንዘብ ድጋፍ ተደራሽነት ማቀጃን በመጠቀም በሴት ሥራ ፈጣሪዎች ላይ ትኩረት የሚያደርጉ የማይክሮፋይናንስ ተቋማትና የመንግስት እርዳታዎችን ትለያለች፡፡ የፋይናንስ እውቀቷን ለማሻሻል በአውደ ጥናቶች ላይ ትሳተፍ እና ለተለያዩ ፕሮግራሞች ማመልከቻዎችን ታስገባለች፡፡ በሁለት ወራት ውስጥ ዕቃዎች ለመግዛትና ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎቿን ማምረት ለመጀመር የሚያስችላት አነስተኛ እርዳታ ታገኛለች፡፡

የቤተሰብ ኃላፊነቶችን ከንግድ ሥራ ህልሞቿ ጋር ማመጣጠን ለነብያት ሌላኛው እንቅፋት ነበር፡፡ ነብያት የቤተሰቧ ዋነኛ ተንከባካቢ በመሆኗ በአብዛኛው ውጥረት ያጋጥማታል፡፡ ጊዜዋን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመጠቀም የጊዜ አጠቃቀም እና የቤተሰብ ኃላፊነትን ማመጣጠኛ ማቀጃ ትጠቀማለች፡፡ ነብያት እንደ የምሳሌ ሙከራዎችን ማካሄድና የደንበኛ ግብረ መልስ መሰብሰቢያ ክፍለ ጊዜዎች፣ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ለቤተሰብ አባላት መመደብ እና ለስራ ሰዓቶች ግልጽ ገደቦችን ማስቀመጥ ከፍተኛ ውጤት ለሚያስገኙ ስራዎች ቅድሚያ በመስጠት የቤት ውስጥ ኃላፊነቶቿን ሳትዘነጋ የንግድ ሥራዋን በማሳደግ ላይ ለማተኮር ችላለች፡፡
በወንድ የበላይነት ወደሚመሩ የአቅርቦት ሰንሰለቶች ዘልቆ መግባትም ሌላ ችግር ይፈጥርባታል፡፡ ለምድጃዎቿ እንደ የብረት አካሎችና የመለጠፊያ እቃዎች የመሳሰሉ ጥሬ እቃዎችን ለማግኘት ከሰጣት ሴት ጋር በፍትሀዊ ስምምነቶች ላይ ለመደራደር ቸልተኛ ከሆኑ አቅራቢዎች ፈተና ይገጥማታል፡፡ ከችግር መለያ ቴምፕሌት መነሳሻ በመንደፍ እቃዎችን ለማግኘትና በተሻሉ ዋጋዎች ላይ ለመደራደር ከአንድ በሴቶች ከሚመራ ህብረት ስራ ማህበር ጋር ትብብር ትመሰርታለች፡፡ ይህ ትብብር ወጪዎቿን እንድትቀንስ ብቻ ሳይሆን የአቅርቦት ሰንሰለቷን ውጤታማ በሆነ መልኩ እንድታጠናክር ያስችላታል፡፡

ለአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ያለው የባህል ተቃውሞም ሌላኛው እንቅፋት ነበር፡፡ ብዙ የከተማ ቤተሰቦች ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችን ለመቀበል ቸልተኛ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ስር በሰደዱ ልማዶች የተነሳ ባህላዊ ክፍት ወይም ማገዶ ቆጣቢ ያልሆኑ ምድጃዎችን ይመርጣሉ፡፡ ነብያት ይህን ችግር ለመፍታት ምርቷን ከደንበኞች ፍላጎቶች ጋር ለማስማማት ለባህል አግባብነት ማረጋገጫ ዝርዝርን ትጠቀማለች፡፡ ነብያት ምድጃዎቿ እንዴት ከባህላዊ ድስቶች ጋር ያለ ምንም እንከን እንደሚሰሩ ለማሳየት የምግብ አበሳሰል የተግባር ገለጻዎችን ከማካሄድ ባለፈ የምድጃዎቿን የዋጋ ተመጣጣኝነትና የጤና ጥቅሞች ታብራራለች፡፡ ለባህል አግባብነት ያለው ማሸጊያና የምርት ምልክት በመጠቀም ቀስ በቀስ ከትኩረት ደንበኞቿ እምነት ታገኛለች፡፡
በመጨረሻም ነብያት የምክር ኔትወርኮችን የመፍጠር አስፈላጊነትን ትገነዘባለች፡፡ በምክርና የኔትወርክ ዝግጅት ዕቅድ አማካኝነት ንጹህ የማብሰያ ምርቶችን ከሚያስተዋውቁ የኢንዱስትሪ ማህበራት፣ የማህበረሰብ መሪዎች እና ኤንጂኦዎች ጋር ግንኙነት ትፈጥራለች፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች ተደራሽነቷን እንድታሰፋ፣ በትብብሮች አማካኝነት ወጪዎቿን እንድትቀንስ እና የገበያ ተአማኒነትን እንድታገኝ ያስችሏታል፡፡
በስድስት ወራት ውስጥ ነብያት ንጹህ የማብሰያ ምድጃ የንግድ ሥራዋን በስኬት በመጀመር 500 ምድጃዎችን ለከተማ ቤተሰቦች ትሸጣለች፡፡ ጽናቷ እና እንደ የችግር መለያ ቴምፕሌት፣ የገንዘብ ድጋፍ ማግኛ ማቀጃ እና ለባህል አግባብነት ማረጋገጫ ዝርዝር ያሉ መሳሪያዎችን በስትራቴጂ/ስልት መጠቀሟ ምርቷን በተመጣጣኝ ዋጋ እንድታቀርብ፣ ተደራሽ እንድታደርግና ለባህል አግባብነት ያለው እንድታደርግ ያስቻላት ከመሆኑም በተጨማሪ በማህበረሰቧ ውስጥ ያሉ ሴቶችን አቅም እንድታጎለብት ያስችላታል፡፡ የነብያት ታሪክ ሴት ስራ ፈጣሪዎችን በልዩ ሁኔታ የሚያጋጥሟቸው ችግሮችን ለመፍታት የዝግጁነት፣ አርቆ አሳቢነትና ደንበኛን ያማከለ አቀራረብ አቅምን ማሳያ ነው፡፡
