ጽዎታዎችን ያማከለ ከባቢ የመፍጠር ስልጠና
  • የዋጋ ተመጣጣኝነት: አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን በማዘጋጀት ለሴት ሥራ ፈጣሪዎችና ደንበኞች ተደራሽ መሆናቸውን የማረጋገጥ ችሎታ ነው፡፡

 

  • የመቀበል እንቅፋቶች: ደንበኞችን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወይም አሰራሮችን እንዳይቀበሉ የሚገድቡ እንደ ከፍተኛ ወጪዎች ወይም የባህል ተቃውሞ የመሳሰሉ ችግሮች ናቸው፡፡

 

  • የባህል ተቃውሞ: ስር በሰደዱ ልማዶች ወይም ለውጥን በመጠራጠር የተነሳ አዳዲስ መፍትሄዎችን ለመቀበል ማመንታት ሲሆን ለባህል አግባብነት ያላቸው ዲዛይኖች ማዘጋጀትን ይፈልጋል፡፡

 

  • የግብረ መልስ መቀበያ: ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማጥራትና ለማሻሻል ከደንበኛ አስተያየቶችን የመቀበል ሂደት ነው፡፡

 

  • የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅ: ከተወሰኑ ኢንዱስትሪዎች ጋር የተያያዙ ችግሮችን፣ መፍትሄዎችን፣ የገቢ ማግኛ መንገዶችን እና የወጪ መዋቅሮችን ለይቶ ለማወቅ የሚያገለግል ባለ አንድ ገጽ መሳሪያ ነው፡፡

 

  • የምክር ኔትወርኮች: ሴቶችን በስራ ፈጣሪነት ላይ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዲፈቱ ለመርዳት መመሪያ፣ ምክርና ድጋፍ የሚያቀርቡ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ናቸው፡፡

 

  • የማይክሮፋይናንስ ተቋማት: አገልግሎት ለተነፈጉ ማህበረሰቦች በተለይም ለሴት ሥራ ፈጣሪዎች አነስተኛ ብድሮች ወይም እርዳታዎችን የሚሰጡ ድርጅቶች ናቸው፡፡

 

  • የማህበረሰብ አድልዎዎች: የሴቶችን የንግድ ድርጅቶችን የመምራት ወይም የፋይናንስ ውሳኔዎች የማሳለፍ ችሎታዎች በተመለከተ ያሉ የማይቀየሩ ወይም በቅድሚያ የታመነባቸው አመለካከቶች ናቸው፡፡

 

  • የአቅርቦት ሰንሰለት ችግሮች: በወንድ የበላይነት ወደሚመሩ የአቅርቦት ሰንሰለት ዘልቆ የመግባት ችግሮች ሲሆኑ በዋናነት በሴቶች ከሚመሩ የህብረት ሥራ ማህበራት ጋር ህብረት መመስረትን ይፈልጋሉ፡፡

 

  • የጊዜ አጠቃቀም: ለስራዎች ቅደም ተከተል የመስጠት እና የቤተሰብ ኃላፊነቶችን ከንግድ ሥራ ግቦች ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ የማመጣጠን ስራ ነው፡፡
Scroll to Top