-
የማህበረሰብ አድልዎዎች ምንድን ናቸው፤ በሴት ስራ ፈጣሪዎች ላይ እንዴት ተጽእኖ ይፈጥራሉ?
መልስ፡ የማህበረሰብ አድልዎዎች የሴቶች የአመራር ችሎታዎችን የሚጠራጠሩ የማይቀየሩ አመለካከቶች ሲሆኑ ተአማኒነትን እና ለኔትወርክ ተደራሽነትን ሊገድቡ ይችላሉ፡፡
-
ሴቶች የገንዘብ ድጋፍ ውሱንነትን እንዴት መፍታት ይችላሉ?
መልስ፡ ሴቶች ከማይክሮፋይናንስ ተቋማት ጋር ትብብር ሊፈጥሩ ወይም በልዩ ሁኔታ በሴቶች ለሚመሩ የንግድ ድርጅቶች ለተዘጋጁ እርዳታዎች ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡
-
የባህል ተቃውሞ ምንድን ነው፤ ይህን እንዴት መፍታት ይቻላል?
መልስ፡ የባህል ተቃውሞ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመቀበል ማመንታት ሲሆን ለባህል አግባብነት ያላቸው መፍትሄዎችን በማዘጋጀት ሊፈታ ይችላል፡፡
-
የምክር ኔትወርኮች ሴት ስራ ፈጣሪዎችን እንዴት ሊረዷቸው ይችላሉ?
መልስ፡ የምክር ኔትወርኮች ችግሮችን ለማለፍና የንግድ ሥራን ለማሳደግ መመሪያ፣ የድጋፍ ምንጮችና ድጋፍ ያቀርባሉ፡፡
-
ለሴቶች ለስራዎች ቅደም ተከተል እንዲሰጡና ጊዜያቸውን ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲጠቀሙ የሚረዷቸው መሳሪያዎች ምንድን ናቸው?
መልስ፡ እንደ የቅደም ተከተል መስጫ ማትሪክስ እና የድርጊት እቅዶች ያሉ መሳሪያዎች የቤተሰብና የንግድ ሥራ ኃላፊነቶችን ለማመጣጠን ይረዳሉ፡፡
-
ሴቶች በወንድ የበላይነት ወደሚመሩ የአቅርቦት ሰንሰለቶች ዘልቀው መግባት የሚችሉት እንዴት ነው?
መልስ፡ ሴቶች በፍትሀዊ ስምምነቶች ላይ ለመደራደርና ወጪዎችን ለመቀነስ በሴቶች ከሚመሩ የብረት ሥራ ማህበራት ወይም የአካባቢ ድርጅቶች ጋር ትብብር መፍጠር ይችላሉ፡፡
-
በንጹህ ማብሰያ ዘርፍ ውስጥ የዋጋ ተመጣጣኝነት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
መልስ፡ የዋጋ ተመጣጣኝነት መፍትሄዎች/ምርቶች አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ተደራሽ መሆናቸውን በማረጋገጥ የተቀባይነት ደረጃዎችን ያሳድጋል፡፡
-
ግብረ መልስ ማግኛ ምንድን ነው፤ ለምን ያስፈልጋል?
መልስ፡ ግብረ መልስ ማግኛ ምርቶችን ለማጥራትና የተጠቃሚ ፍላጎቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ የሚያሟሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የደንበኛ አስተያየቶችን ይሰበስባል፡፡
-
የንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ሊረዳቸው የሚችለው እንዴት ነው?
መልስ፡ የንግድ ሥራ ሞዴል ረቂቅ የንግድ ሥራ ሀሳቦችን ለይቶ ለማወቅ፣ ዋና ዋና ችግሮችን ለመለየት እና መፍትሄዎችን ከደንበኛ ፍላጎቶች ጋር ለማስማማት ይረዳል፡፡
-
ለሴት ስራ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ውጤት የሚያስገኙ ስራዎች ምንድን ናቸው?
መልስ፡ ከፍተኛ ውጤት የሚያስገኙ ስራዎች እንደ አገልግሎት ያላገኙ ገበያዎች ላይ ማተኮር ወይም ለእድገት የደጂታል ፕላትፎርሞችን ማጠናከር በመሳሰሉ ስትራቴጂዎች ላይ ያተኩራሉ፡፡