የፋይናንስ ትንተና እና የእድገት ዕቅድ ዝግጅት

የገቢ መግለጫ ምንድን ነው?

ፍቺ/ትርጉም: የገቢ መግለጫ አንድ የንግድ ድርጅት በተወሰነ ጊዜ (ለምሳሌ፡ ወር፣ ዕሩብ ዓመት ወይም ዓመት) ውስጥ ምን ያክል ገንዘብ እንዳገኘና እንዳወጣ የሚያሳይ የፋይናንስ ሪፖርት ነው፡፡ መግለጫው ሁለት አስፈላጊ ነገሮችን ይነግርዎታል፡

  • ገቢ (ሽጮች): ይህ የንግድ ድርጅቱ ምርቶች ወይም አገልግሎቶችን ከመሸጥ ያገኘው የገንዘብ መጠን ነው፡፡
  • ወጪዎች: ይህ የተሸጡ ዕቃዎች ወጪን፣ ኪራይን፣ ደመወዝ፣ አገልግሎቶችን፣ ወዘተ ጨምሮ የንግድ ድርጅቱ የኩባንያውን ስራ ለማስኬድ ያወጣው ወጪ ነው፡፡

 

በገቢ መግለጫ ውስጥ የሚካተቱ ዋና ዋና ቃላት

በትርፍና ኪሳራ ሂሳብ ውስጥ የሚያዩዋቸውን አስፈላጊ ቃላት እንከፋፍል፡

  • ገቢ (ሽያጮች): የትኛውም ወጪዎች ከመቀነሳቸው በፊት ከእቃዎች ወይም አገልግሎቶች ሽያጭ የሚገኘው ጠቅላላ ገቢ ነው፡፡
    • ቀመር: ገቢ=በምርት የመሸጫ ዋጋ × የተሸጡ ምርቶች ብዛት
  • የተሸጡ ዕቃዎች ወጪ(COGS): በአንድ የንግድ ድርጅት የሚሸጡ ዕቃዎችን ለማምረት የሚከፈሉ ቀጥተኛ ወጪዎች ናቸው፡፡ ይህ በቀጥታ ለማምረቻ የዋሉ ጥሬ ዕቃዎችን እና የጉልበት ዋጋ ወጪዎችን ይቀጥላል፡፡ ለዮሀንስ ይህ የሶላር ማብሰያ ማብሰያ አካሎች ወጪ ነው፡፡ ለሰላማዊት ይህ የንጹህ የማብሰያ ምድጃዎች እና የባዮፊዩል ከሰሎች እቃዎች መግዣ ወጪ ይሆናል፡፡
  • ጠቅላላ ትርፍ: አንድ ኩባንያ ምርቶቹን ከማምረቻና መሸጫ ጋር ተያያዥ ወጪዎቹን (COGS) ከቀነሰ በኋላ የሚያገኘው ትርፍ ነው፡፡ ይህ ለንግድ ስራዎ ዋና ዋና ትርፋማነት በመጀመሪያ መታየት ያለበት አስፈላጊው ነው፡፡
    • ቀመር: ጠቅላላ ትርፍ=ገቢ−COGS
  • የስራ ማስኬጃ ወጪዎች (OPEX): የንግድ ድርጅቱን ስራ ለማስኬድ የሚከፈሉ እንደ የሱቅዎ/ቤተ ሙከራዎ ኪራይ፣ አገልግሎቶች፣ ገበያ፣ የሰራተኞች ደመወዝ እና አስተዳደራዊ ወጪዎች የመሳሰሉ መደበኛ ወጪዎች ናቸው፡፡ ይህ የእነዚህ ሁሉም የስራ ማስኬጃ ወጪዎች ድምር ነው፡፡
  • ከወለድና ግብር በፊት የሚገኙ ገቢዎች (EBIT) / የስራ ትርፍ: ወለድና ግብሮችን ሳይጨምር ከአንድ ኩባንያ ዋና ዋና የንግድ ስራ እንቅስቃሴዎች የሚገኝ ትርፍ ነው፡፡ ይህ የንግድ ስራ እንቅስቃሴዎችዎ ምን ያክል በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ እንደሆነ ያሳያል፡፡
    • ቀመር: EBIT=ጠቅላላ ትርፍ−የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች
  • የተጣራ ትርፍ (የተጣራ ገቢ): ከጠቅላላ ገቢ ላይ ግብሮችና ወለድን ጨምሮ ሁሉም ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚገኘው ጠቅላላ ትርፍ ነው፡፡ ይህ “የሥረኛው መስመርዎ” – በትክክል ያገኙት ገቢ ነው፡፡
    • ቀመር: የተጣራ ትርፍ=የስራ ትርፍ−ወለድ−ግብሮች
  • የወለድ ወጪ: ኩባንያው ለተበደረው ገንዘብ (ለምሳሌ፡ ብድሮች ወይም እዳ) የሚከፍለው ወጪ ነው፡፡ ዮሀንስ ማሽን ለመግዛት ገንዘብ የሚበደር ከሆነ በዛ ብድር ላይ የሚከፍለው ወለድ የወለድ ወጪ ነው፡፡
  • የግብር ወጪ: በኩባንያው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ላይ ተመስርቶ እንደ ግብር ለመንግስት የሚከፈል ገንዘብ ነው፡፡
  • የእርጅና ዋጋ መቀነስ እና አሞርታይዜሽን: የሚዳሰሱ ንብረቶች ዋጋን የሚቀንሱ (የእርጅና ዋጋ መቀነስ፣ ለምሳሌ፡ የማስረከቢያ መኪና ዋጋ በጊዜ ሂደት እየቀነሰ መሄድ) እና የማይዳሰሱ ንብረቶች ዋጋን የሚቀንሱ (አሞርታይዜሽን፣ ለምሳሌ፡ የባለቤትነት መብት ዋጋ መቀነስ) የገንዘብ ያልሆኑ ወጪዎች ናቸው፡፡ ለእነዚህ በየወሩ በጥሬ ገንዘብ አይከፍሉም ነገር ግን የንብረቶችዎን በእርጅና ዋጋ መቀነስ ይወክላሉ፡፡
    • የቀጥተኛ መስመር የእርጅና ዋጋ መቀነስ ቀመር: የእርጅና ዋጋ መቀነስ ወጪ=የንብረት የአገልግሎት ዘመን/የአገልግሎት ዋጋ −ቀሪ የአገልግሎት ዋጋ ​
  • ከወለድ፣ ግብሮች፣ በእርጅና ዋጋ መቀነስ እና አሞርታይዜሽን በፊት የሚገኙ ገቢዎች (EBITDA): ወለድን፣ ግብሮችን፣ የእርጅና ዋጋ መቀነስን እና አሞርታይዜሽንን ሳይጨምር የአንድ ኩባንያ አጠቃላይ የፋይናንስ አፈጻጸም መለኪያ ነው፡፡ ይህ ኩባንያዎ የገንዘብ ያልሆኑ ወጪዎችን ወይም የፋይናንስ ወጪዎችን ታሳቢ ከማድረግዎ በፊት ከስራዎቹ ምን ያክል ገንዘብ እንዳገኘ በተመለከተ ጥቅል ሀሳብ ይሰጥዎታል፡፡
    • ቀመር: EBITDA=ስራ ትርፍ (EBIT)+የእርጅና ዋጋ መቀነስ+አሞርታይዜሽን
  • የተያዙ ገቢዎች: የትኛውም ተከፋዮች ለባለቤቶቹ ከተከፈሉ በኋላ በኩባንያው ውስጥ የሚቀመጠው የተጣራ ገቢ ክፍል ነው፡፡ ገንዘቡ መልሶ በንግድ ስራ ላይ ኢንቨስት ሊደረግ ይችላል፡፡
    • ቀመር: የተያዙ ገቢዎች=የመጀመሪያ የተያዙ ገቢዎች+የተጣራ ትርፍ−ተከፋዮች

 

ደረጃ በደረጃ: የገቢ መግለጫዎን ማዘጋጀት

እንዴት እንደሚያደርጉ: የገቢ መግለጫዎን ለማዘጋጀት በተወሰነ ጊዜ ሽያጮችዎ እና ወጪዎችዎ ላይ መረጃ መሰብሰብ ይኖርብዎታል፡፡

ደረጃ 1: ጊዜዎን ይምረጡ፡

የገቢ መግለጫዎን ማዘጋጀት የፈለጉት ለወር፣ ለእሩብ ዓመት ወይም ለሙሉ ዓመት ስለመሆኑ ይወስኑ፡፡ ለአዲስ የንግድ ድርጅቶች በወርሀዊ ወይም የዕሩብ ዓመት መጀመር በአብዛኛው ቀላል ነው፡፡

 

ደረጃ 2: ጠቅላላ ገቢዎን ያስሉ

  • የንግድ ድርጅትዎ የሶላር የምግብ ማብሰያዎች፣ ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎች፣ የባዮፊዩል ከሰሎች ወይም የትኛውንም ተያያዥ አገልግሎቶች በመረጡት ጊዜ ውስጥ ከመሸጥ ያገኘውን ሁሉንም የገንዘብ መጠን ይደምሩ፡፡
  • ለምሳሌ፡ ጀማል በጥር ወር 50 የሶላር የምግብ ማብሰያዎችን እያንዳንዳቸውን በ2000 ብር ይሸጣል፡፡ ስለሆነም የጥር ወር ጠቅላላ ገቢው 50×2000=ብር 100,000 ይሆናል፡፡

 

ደረጃ 3: የተሸጡ እቃዎች ወጪዎን (COGS) ያስሉ

  • የሸጧቸውን ምርቶች ቀጥተኛ ወጪዎች ይደምሩ፡፡ ይህ የጥሬ እቃዎች ወይም የእቃዎች መግዣ ወጪን፣ እና የትኛውንም እነዚህን በመገጣጠም ላይ የተሳተፈ ሰራተኛ ወጪን ያጠቃልላል፡፡
  • ለምሳሌ ለጀማል: እያንዳንዱ የሸጠው የሶላር ማብሰያ ብር 1200 (ለአካሎችና ገጣሚ ሰራተኛ) ወጪ አስወጥቶታል፡፡ ስለዚህ የ50 የምግብ ማብሰያዎች COGS 50×1200=ብር 60,000 ይሆናል፡፡

 

ደረጃ 4: ጠቅላላ ትርፍዎን ያስሉ

  • ከጠቅላላ ገቢዎ ላይ COGSን ይቀንሱ፡፡
  • ለምሳሌ ለጀማል: ጠቅላላ ትርፍ=ብር 100,000 (ገቢ)−ብር 60,000(COGS)=ብር 40,000.

 

ደረጃ 5: የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችዎን ይዘርዝሩ እና ይደምሩ

  • የንግድ ስራዎን ለማስኬድ የተከፈሉ የተሸጡ ዕቃዎች ቀጥተኛ ወጪ ያልሆኑ ሁሉንም ወጪዎች ያስቡ፡፡
  • ለምሳሌ፡ ሰላማዊት ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችን እና የባዮፊዩል ከሰሎችን የምትሸጥበት ትንሽ ሱቅ ለመክፈት ታቅዳለች፡
    • የሱቅ ኪራይ: ብር 5,000
    • ለትርፍ ሰዓት ረዳት የሚከፈል ደመወዝ: ብር 3,000
    • የገበያ በራሪ ወረቀቶች: ብር 500
    • አገልግሎቶች (ኤለሌክትሪክ፣ ውሀ): ብር 1,000
    • ጠቅላላ የስራ ማስኬጃ ወጪዎች = 5,000+3,000+500+1,000=ብር 9,500.

 

ደረጃ 6: ከወለድና ግብር በፊት ገቢዎችዎን (EBIT) ያስሉ

  • ጠቅላላ የስራ ማስኬጃ ወጪዎችዎን ከጠቅላላ ትርፍዎ ላይ ይቀንሱ፡፡
  • ለምሳሌ (የሰላማዊትን ኩነት በታሰበው ብር 25,000 ጠቅላላ ገቢ ይቀጥሉ): EBIT=ብር 25,000(ጠቅላላ ትርፍ)−ብር 9,500(የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች)=ብር 15,500.

 

ደረጃ 7: የወለድና የግብር ወጪዎችን ያስሉ (ተግባራዊ ከተደረገ)

  • ብድሮች ካሉብዎ የትኛውንም የወለድ ክፍያዎች ይቀንሱ፡፡
  • የትኛውንም የግብር ወጪዎች ይቀንሱ (በዚህ ላይ መጀመሪያ ላይ የሂሳብ ባለሙያ ሊያማክሩ ይችላሉ)፡፡
  • ለምሳሌ (የሰላማዊትን ይቀጥሉ): ሰላማዊት በወር ለብድር ወለድ ብር 500 እና ለግብር ብር 1,000 ብትከፍል፡
    • የተጣራ ትርፍ=ብር 15,500(EBIT)−ብር 500(ወለድ)−ብር 1,000(ግብሮች)=ብር 14,000፡፡

 

Scroll to Top