የፋይናንስ ትንተና እና የእድገት ዕቅድ ዝግጅት

የራስ መማሪያ – ደረጃ በደረጃ የአሰራር ሂደት:

  • ከዚህ ይጀምሩ: ትርፋማነትዎን ለመረዳት በገቢ መግለጫ ይጀምሩ፡፡
  • ቴምፕሌቱን ያጠናቁ: ለገቢ መግለጫ፣ ባላንስ ሺት እና የገንዘብ ፍሰት መግለጫ የንግድ ስራዎን ዳታ ለመመዝገብ የቀረቡትን ቴምፕሌቶች ይጠቀሙ፡፡
  • ቀጣይ: እያንዳንዱን መግለጫ ለማዘጋጀት እና ዋና ዋና ሬሺዮዎችን ለማስላት ደረጃ በደረጃ መመሪያዎቹን ይከተሉ፡፡
  • የጉዳይ ጥናቱን ይገምግሙ: ንድፈ ሀሳቡን ከእውነተኛው አለም አሰራር ጋር ለማገናኘት ንድፈ ሀሳቦቹ እንዴት እንደ ዮሀንስ እና ሰላማዊት ባሉ ስራ ፈጣሪዎች ላይ እንደሚተገበሩ ይመልከቱ፡፡

የትምህርቱ ዓላማዎች: ይህን ትምህርት ካጠናቀቁ በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ:

  • የገንዘብ መግለጫ፣ ባላንስ ሺት እና የገንዘብ ፍተን መግለጫን ዓላማ እና ክፍሎች መግለጽ እና መረዳት፡፡
  • ለንጹህ የማብሰያ ንግድ ስራዎ መሰረታዊ የፋይናንስ መግለጫዎችን ማዘጋጀት፡፡
  • የንግድ ስራ ትርፋማነትዎን፣ መጣራት መቻልዎን እና አለመክሰርዎን ለመመዘን ዋና ዋና የፋይናንስ ሬሺዮዎችን ማስላትና መተርጎም፡፡
  • ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ለመለየት የንግድ ስራዎን የፋይናንስ ጤናማነት መተንተን፡፡

ዓላማ: የፋይናንስ ትንተና ዓላማ ስለ አንድ ኩባንያ አፈጻጸም ግንዛቤ ለማግኘት እና የተሻሉ ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የፋይናንስ ዳታን መጠቀም ነው፡፡ ለአንድ ስራ ፈጣሪ ይህ የንግድ ስራዎ እንዴት እየተካሄደ እንደሆነ፣ ገንዘብዎ ወደ የት እየሄደ እንደሆነ እና ለእድገት እንዴት ጥሩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፉ ለመረዳት ጠቃሚ መሳሪያ ነው፡፡  

 

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:

  • የፋይናንስ መግለጫዎችን መረዳት: ሶስቱ ዋና ዋና መግለጫዎች የገቢ መግለጫ (ትርፍና ኪሳራ)፣ ባላንስ ሺት እና የገንዘብ ፍሰት መግለጫ ናቸው፡፡

የሬሺዮ ምድቦች: በሶስት ዋና ዋና የትንተና አይነቶች ማለትም፡ ትርፋማነት (ምን ያክል ትርፍ እንደሚያገኙ)፣ መጣራት (የአጭር ጊዜ ክፍያዎችን መክፈል መቻል) እና አለመክሰር (የረጅም ጊዜ እዳዎን መክፈል መቻል) ላይ እናተኩራለን፡፡

Scroll to Top