Course Content
የገንዘብ/ፋይናንስ አስተዳደር

የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅት ምንድን ነው?

የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅት ለንግድ ስራው የገንዘብ ግቦችን የመወሰን እና እነዚህን ለማሳካት ዝርዝር ፍኖተ ካርታ ወይም ስትራቴጂ የማዘጋጀት አጠቃላይ ሂደት ነው፡፡ ይህ የንግድ ስራውን ወቅታዊ የገንዘብ ሁኔታን መመልከትን፣ የአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ ዓላማዎችን መግለጽን፣ እና እዚያ ለመድረስ የሚያስፈልጉ ሀብቶችና ድርጊቶችን መወሰንን ይይዛል፡፡ የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅት ወደፊት አሻግሮ መመልከት እና ስትራቴጂያዊ ነው፡፡ ዕቅዱ ለሚከተሉት አይነት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፡ “የንግድ ስራው በገንዘብ ረገድ በአንድ፣ በሶስት ወይም በአምስት ዓመታት ውስጥ ምን ላይ እንዲገኝ ነው የምንፈልገው?” እና “ይህ እውን እንዲሆን ምን እርምጃዎችን መውሰድ አለብን?”

የበጀት ምደባ ምንድን ነው?

የበጀት ምደባ የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅት የበለጠ ልዩና የአሀዝ ክፍል ነው፡፡ በጀት የንግድ ስራው ገንዘቡን (ወጪዎቹን) እንዴት ለማውጣት እንደሚያስብ እና በተወሰነ ጊዜ ውስጥ በተለይም በወር፣ በዕሩብ ዓመት ወይም በዓመት ውስጥ እንዴት ገንዘብ (ገቢ) ለማግኘት እንደሚያስብ የሚገልጽ ዝርዝር ዕቅድ ነው፡፡ በጀት የገንዘብ ግቦችን ከገንዘብ ዕቅድ ወደ የተግባር አሀዞች እንዲተረጎም ያደርጋል፡፡ የበጀት ምደባ ሀብቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ስለመመደብ፣ ትክክለኛ አፈጻጸምን ከዕቅዱ አንጻር መከታተል እና እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ስለማድረግ ነው፡፡ በጀት የቁጥጥርና የውሳኔ አሰጣጥ መሳሪያ ነው፡፡

የወጪ ምደባ  

የወጪ ምደባ የንግድ ስራው ለስራ እንቅስቃሴዎቹ የሚያወጣቸውን ሁሉንም ወጪዎች የመለየት እና የመተንተን የአሰራር ሂደት ነው፡፡

የወጪ ምደባ ግብ እያንዳንዱን ዕቃ ለማምረት፣ እያንዳንዱን አገልግሎት ለማቅረብ ወይም አጠቃላይ የንግድ ስራውን ለማንቀሳቀስ በትክክል ምን ያክል ገንዘብ እንደሚያስወጣ መወሰን ነው፡፡

የወጪ አይነቶች

  • ቋሚ ወጪዎች:- የሚያመርቱት ወይም የሚሸጡት ምርት ምርት ብዛት ምንም ይሁን ምን የማይቀየሩ እና ምንም ባያመርቱ ወይም ባይሸጡ እንኳን የሚከፍሏቸው ወጪዎች ናቸው፡፡
  • ተለዋዋጭ ወጪዎች:- በሚያመርቱት ወይም በሚሸጡት ምርት ብዛት ልክ በቀጥታ የሚቀያየሩ ወጪዎች ናቸው፡፡ ተጨማሪ ሽያጮች = ተጨማሪ ወጪ
  • ቀጥተኛ ወጪዎች:- የተወሰነ ምርት/አገልግሎቶች ከማምረት ጋር በቀጥታና በልዩ ሁኔታ የሚያያዙ ወጪዎች ናቸው፡፤ ቀጥተኛ ወጪዎች በባህሪያቸው በአብዛኛው ተለዋዋጭ ወጪዎች ቢሆኑም ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ቋሚ ወጪ ይሆናሉ፡፡
  • ቀጥተኛ ያልሆኑ (የስራ ማስኬጃ): በተወሰነ ምርት ወይም አገልግሎት በቀጥታ ሊታወቁ የማይችሉ ወጪዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ይልቅ እነዚህ ወጪዎች ለንግድ ስራው አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስፈላጊ ናቸው፡፡

ምሳሌ:-

ሰላማዊት ከበደ ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችና የባዮፊዩል ከሰሎች የምትሸጥበት አነስተኛ ሱቅ ለመክፈት ታቅዳለች፡፡ ይህን መለኪያ ለማሳካት የምታወጣቸው ወጪዎች የአነስተኛ ሱቁን ማቋቋሚያ ወጪዎች ይይዛሉ፡፡

ቀጥተኛ ወጪዎች: እነዚህ ወጪዎች በቀጥታ ከሚሸጠው ምርት ወይም ከሚቀርበው አገልግሎት ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡

  • የማብሰያ ምድጃዎቹን ከአቅራቢ መግዣ ወጪ: ይህ ሰላማዊት ከምትሸጠው ምርት ጋር በቀጥታ የተገናኘ በመሆኑ ቀጥተኛ ወጪ ነው፡፡
  • የባዮፊዩል ከሰሎቹን በኩንታል የመግዣ ወጪ፡ ይህም ሌላኛው የሚሸጠው ምርት በመሆኑ ምክንያት ቀጥተኛ ወጪ ነው፡፡
  • የማብሰያ ምድጃዎቹን እና የባዮፊዩል ከሰሎቹን ወደ ሱቅ ማምጫ የትራንስፖርት ወጪ፡ በቀጥታ ምርቱን ለሽያጭ ዝግጁ ከማድረግ ጋር የተገናኘ ነው፡፡
  • በሱቁ ውስጥ ለሚካሄደው ሽያጭ በቀጥታ እገዛ ለሚያደርግ ሰው የሚከፈል ደመወዝ (ተግባራዊ ከተደረገ)፡ ከሽያጩ ገቢ ከማግኘት ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡

ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎች: እነዚህ ከተወሰነ ምርት ወይም አገልግሎት ጋር በቀጥታ የማይገናኙ ወጪዎች ቢሆኑም ነገር ግን ለንግድ ስራው አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊ ናቸው፡፡

  • የቢሮ ኪራይ: ሰላማዊት ምርቷን የምትሸጥበት ቦታ ያስፈልጋታል፣ ነገር ግን ኪራዩ ከየትኛውም የማብሰያ ምድጃ ወይም የከሰል ማሸጊያ ጋር አይገናኝም፡፡
  • ለሱቁ የመብራት ማስገቢያ ወጪ: ለሱቁ ስራውን እንዲሰራ አስፈላጊ ቢሆንም ነገር ግን በቀጥታ የምርቱ አካል አይደለም፡፡
  • ለሱቁ መክፈቻ የማስታወቂያ በራሪ ወረቀቶች፡ ይህ በአጠቃላይ የንግድ ስራውን የሚያስተዋውቅ ቢሆንም አንድ እራሱን የቻለ ምርት አይደለም፡፡
  • የራሷ ደመወዝ/ወጪ (ለራሷ የምትከፍል ከሆነ): ይህ አጠቃላይ የንግድ ስራውን ለማስተዳደር ለራሷ የምትከፍለው ክፍያ ነው፡፡
  • የንግድ ስራ የፍቃድ ክፍያዎች: የንግድ ስራውን በህጋዊነት ለማንቀሳቀስ የሚከፈል ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡

የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅትና የበጀት ምደባ መመሪያ

ደረጃ 1: የSMART የገንዘብ ግቦች

  • ልዩ: በግልጽ ምን እንደሚፈልጉ ይግለጹ (ለምሳሌ፡ “በዓመት 1,000 የሶላር የምግብ ማብሰያዎችን መገጣጠምና መሸጥ”)፡፡
  • ሊለካ የሚችል: አካሄድዎን እንዴት እንደሚከታተሉ ይወስኑ (ለምሳሌ፡ ሽያጮች፣ የትርፍ ህዳግ፣ የሰራተኛ ቆጠራ)፡፡
  • ሊሳካ የሚችል: የንግድ ስራው ከሀብቶችዎ አንጻር ተጨባጭ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡
  • ተገቢ: የንግድ ስራ ራዕይዎን ያስማሙ (ለምሳሌ፡ በዋጋ ተመጣጣኝ የማብሰያ ምድጃዎች)፡፡
  • በጊዜ የተገደበ: የጊዜ ገደብ ያስቀምጡ (ለምሳሌ፡ በ3 ዓመታት ውስጥ)፡፡

ደረጃ 2: ከንግድ ስራ ስትራቴጂ ጋር ማስማማት

  • ተልዕኮዎን (ለምሳሌ፡ ተመጣጣኝ ዋጋ ባላቸው የሶላር ማብሰያዎች መሪ መሆን) የሚደግፉ የገንዘብ ዒላማዎችዎን (ለምሳሌ፡ ዝቅተኛ ወጪዎች፣ ውጤታማ ምርት) ያረጋግጡ፡፡

ደረጃ 3: መሰረታዊ የገንዘብ ዕቅድ ረቂቅ ማዘጋጀት

  • ወደ SMART ግቦችዎ የሚያደርሱዎትን ስትራቴጂዎችና እርምጃዎች ይግለጹ (ቁጥሮች ብቻ ሳይሆን ሀብቶችዎን እንዴት እንደሚያስተዳድሩ)፡፡

ደረጃ 4: ገቢና ወጪዎችን መተንበይ

  • ታሪካዊ መረጃ: ያለፈ ጊዜ ቁጥሮችን ካሉ ይጠቀሙ፡፡
  • የገበያ ጥናት: ፍላጎትን፣ የዋጋ ትመናን፣ የደንበኛ መሰረትን ይለኩ፡፡
  • የሽያጭ መስመር: ከመሪዎች ጋር የሚያደርጓቸውን ውይይቶች ይገምቱ፡፡
  • የኢንዱስትሪ መለኪያዎች እና የባለሙያ ምክር: ተመሳሳይ የንግድ ስራዎች ወይም አማካሪዎችን ይመልከቱ፡፡

ደረጃ 5: የበጀት እና የገንዘብ ፍሰት ትንበያ ማዘጋጀት

  • የበጀት ክፍሎች:
    ገቢ: ሁሉም የሚጠበቁ የገቢ ማግኛ መንገዶች፡፡
    • ወጪዎች: ወጪዎችን – ቀጥተኛ (ከተወሰነ ምርት/አገልግሎቶች ጋር የተገናኘ) ቀጥተኛ ያልሆኑ (የስራ ማስከቴጃ) በማለት ይዘርዝሩ፡፡
  • የገንዘብ ፍሰት ትንበያ:
    ገቢ ፍሰቶች: ገንዘቡ በትክክል የሚመጣው መቼ እንደሆነ (ለምሳሌ፡ አስቸኳይ ሽያጮች፣ የብድር ገቢዎች)
    • ወጪ ፍሰቶች: ክፍያዎች የሚከፈሉት መቼ እንደሆነ (ለምሳሌ፡ ለአቅራቢዎች፣ ለኪራይ፣ ለደመወዝ)፡፡
Scroll to Top