የጉዳይ ጥናት 1:- የዋጋ ትመና ሞዴል
ዮሀንስ እና የሶላር ማብሰያዎቹ
ዮሀንስ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል የሶላር ማብሰያ ያዘጋጃል፡፡ ቀጥተኛ ወጪው (ቁሳቁሶች፣ የመገጣጠሚያ የጉልበት ዋጋ) በምርት ብር 1300 ነው፡፡ የተገመተ ወርሀዊ የስራ ማስኬጃ ወጪው (የቤተ ሙከራ ኪራይ ድርሻሻ መሳሪያዎች፣ አንዳንድ ገበያዎች) ብር 6000 ነው፡፡ በመጀመሪያ በወር 20 ምርቶችን እንደሚሸጥ ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡
ችግር: ዮሀንስ ለሶላር ማብሰያዎቹ ዋጋ ማውጣት ያለበት እንዴት ነው?
ወጪ-ሲደመርን መተግበር:
- ቀጥተኛ ወጪ በምርት = 1300 ብር
- ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎች በብር = 6000 ብር / 20 ምርቶች = 300 ብር
- ጠቅላላ ወጪ በምርት = 1300 + 300 = 1600 ብር
ዮሀንስ 25% ትርፍ ማግኘት ቢፈልግ: 1600 * 0.25 = 400 ብር
ወጪ-ሲደመር ዋጋ = 1600 + 400 = 2000 ብር
ሌሎች ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት:
ውድድር: በአዲስ አበባ ውስጥ ሌሎች መሰረታዊ የሶላር ማብሰያዎች ከ1900 – 2300 ብር አካባቢ ይሸጣሉ፡፡ የዮሀንስ ብር 2000 ዋጋ ተወዳዳሪ ነው፡፡
ጥቅም: የሆንስ ምርቱ ቤተሰቦች ለከሰል የሚያወጡትን ወጪ በእጅጉ እንደሚቆጥብላቸው (ወደ 300-400 ብር/ወር አካባቢ) ያውቃል፡፡ ይህን እንደ ጥቅም ሊገልጽ ይችላል፡፡
የመጀመሪያ ስትራቴጂ: ዮሀንስ 2000 ብርን እንደ መደበኛ ዋጋው አድርጎ ለመጠቀም ይወስናል፡፡ ሆኖም ለመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ደንበኞችን ቀደም ብሎ ለመሳብ እና መልካም ስሙን ለማጎልበት የማስተዋወቂያ ወደ ገበያ ዘልቆ መግቢያ ዋጋ 1850 ብር ያስከፍላል፡፡ በተጨማሪም ደንበኞች ሁለት ማብሰያዎች ከገዙ አነስተኛ ቅናሽ ለማቅረብ ያቅዳል (የጅምላ/ጥቅል ሽያጭ አይነት)፡፡
የጉዳይ ጥናት 2: የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ትንተና
ሰላማዊት ርካሽ የሰው ሰራሽ ከሰል ማሸጊያ ታጠናለች
ሰላማዊት በአሁኑ ወቅት ከሰሎቿን የምትሸጠው በ28 ብር/ኪግ ሲሆን ወርሀዊ ቋሚ ወጪዎቿ 2400 ብር ናቸው፡፡ የትርፍ መዋጪ ህዳጓ 8 ብር/ኪግ ሲሆን የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥቧ 300 ኪግ/ወር ነው፡፡ ሰላማዊት ለከሰሏ ተለዋዋጭ ወጪዋን በኪግ በ2 ብር (ከ20 ብር ወደ 18 ብር) የሚቀንስላት አዲስ፣ ርካሽ የከሰል ማሸጊያ ታገኛለች፡፡ የከሰሎቿ ጥራት እና የሚነዱበት ጊዜ ርዝመት እንዳለ ነው፡፡
ችግር: ይህ የተለዋዋጭ ወጪ መቀነስ በገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥቧ ላይ ተጽእኖ የሚፈጥረው እንዴት ነው?
ትንተና:
ቋሚ ወጪዎቿ አንድ አይነት ሆነው ይቀጥላሉ: 2400 ብር
የመሸጫ ዋጋዋ ተመሳሳይ ሆኖ ይቀጥላል: 28 ብር/ኪግ
አዲስ ተለዋዋጭ ወጪ በኪግ = 18 ብር
አዲስ የትርፍ መዋጮ ህዳግ በምርት = ኤስፒ – አዲስ ቪሲ = 28 ብር – 18 ብር = 10 ብር/ኪግ
የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ (ምርቶች/ኪግ) = ቲኤፍሲ / አዲስ የሲኤም ምርት = 2400 ብር / 10 ብር/ኪግ = 240 ኪግ
የውሳኔ ነጥብ: ሰላማዊት ተለዋዋጭ ወጪዎቿን በመቀነስ የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥቧ ላይ ከ300 ኪግ ይልቅ 240 ኪግ ከሰል በመሸጥ ትደርሳለች፡፡ ይህ ማለት በእያንዳንዱ ወር ወዲያውኑ ትርፍ ማግኘት ትጀምራለች፣ ወይም ልክ እንደ በፊቱ ትንሽ ምርቶችን በመሸጥ ተመሳሳይ ትርፍ ማግኘት ትችላለች፡፡ ሰላማዊት አዲሱ የከሰል ማሸጊያ በረጅም ጊዜ ውስጥ በከሰሏ ጥራት ላይ ተጽእኖ እንደማይፈጥር ማረጋገጥ አለባት፡፡