Course Content
የገንዘብ/ፋይናንስ አስተዳደር

የ22 ዓመቷ ሰላማዊት ከበደ የምትኖረው ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን በትርፍ ጊዜዋ ባህላዊ ምድጃዎችን ትሸጣለች፡፡ ነገር ግን ህልሟ ከዚያም ያለፈ ነው፡፡ ለቤተሰብ ደህንነት አስተማማኝ የሆኑ፣ ለጤና የተሻሉና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችን እና የባዮፊዩል ከሰሎችን የምትሸጥበት ሱቅ ለመክፈት ትፈልጋለች፡፡ ግቧ የንግድ ስራ መስራት ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ወጣት ሴቶች አርአያ መሆን ነው፡፡

ምንም እንኳን መደበኛ የንግድ ስራ ልምድ የሌላት፣ ከማህበራዊ ጫና ጋር እየታገለችና ለካፒታል ተደራሽነቷ ውሱን ቢሆንም ሰላማዊት ለዓላማዋ ቁርጠኛ ነች፡፡ ሀሳቧን እውን ለማድረግ ባለ አምስት ደረጃ የገንዘብ እቅድ ዝግጅት እና የበጀት ምደባ ሂደት ለመከተል ትወስናለች፡፡

ሰላማዊት ግልጽና አጭር ግብ በማዘጋጀት ትጀምራለች፡፡

“በቀጣዮቹ 3 ወራት ውስጥ 15 ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችን እና 100 ኪግ ከሰሎችን እሸጣለሁ፣ 2 የማህበረሰብ ገለጻዎችን አካሂዳለሁ፣ እንዲሁም ከሽያጮች 10,000 ብር አገኛለሁ፡፡”

ስትራቴጂዋ በዋጋ ተመጣጣኝ ንጹህ የምግብ ማብሰያ ምርቶችን ማቅረብ እና በማህበራሰቧ ውስጥ ያላትን እምነት ማጎልበት ነው፡፡ የሚከተሉትን ለማድረግ ታቅዳለች፡

  • ዕቃዎችን በጥሩ ዋጋዎች ለመግዛት
  • ተወዳዳሪ የሽያጭ ዋጋ ለማቅረብ
  • ከበጀቷ ውስጥ ከፊሉን ለገለጻዎችና ስምሪቶች ለመክፈል
     የመጀመሪያ ትርፎች ትንሽ ሊሆኑ እንደሚችሉ፣ ነገር ግን የማህበረሰብ ዕምነት ማግኘት ለረጅም ጊዜ እድገት ወሳኝ እንደሆነ ታውቃለች፡፡

ሰላማዊት ቀላል ዕቅዷን ታብራራለች:

  • የመጀመሪያ ገንዘብ: ከቁጠባዎች እና ከአነስተኛ የቤተሰብ ብድር የሚገኝ ብር 10,000፡፡
  • የአቅርቦት ምንጭ: ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው፣ አስተማማኝ አቅራቢዎች ማግኘት
  • ሽያጭና ገበያ: ኔትወርኳን፣ መልዕክቷን እና የገለጻ ዝግጅቶችን መጠቀም
  • ስራዎች: የኪራይ ወጪን ለመቆጠብ ከቤት ውስጥ መጀመር
  • የስጋት ቁጥጥር: ፍላጎትን ለመፈተሸ በትንሽ ዕቃዎች መጀመር

 

ሰላማዊት ገቢዋን እና ወጪዎቿን ትተነብያለች

  • ገቢ: 5 ምድጃዎች × 800 ብር = 4,000 ብር
  • ቋሚ ወጪዎች: ኪራይ 1,000 + አገልግሎቶች 200 + ደመወዝ 2,500 = 3,700 ብር
  • ተለዋዋጭ ወጪዎች: ቁሳቁሶች (5 × 500) 2,500 + ከሰሎች 210 + ገበያ 500 = 3,210 ብር
  • ጠቅላላ ወጪዎች: 3,700 + 3,210 = 6,910 ብር
  • የተጣራ ውጤት: 4,000 – 6,910 = –2,910 ብር (ኪሳራ)

መመሪያዎች: ይህን የጉዳይ ጥናት በጥንቃቄ ያንብቡ እና የሚከተሉትን ከአንድ በላይ ምርጫዎች የሚይዙ ጥያቄዎች ይመልሱ፡፡  

 

ጥያቄ 1: በቀጣዮቹ 3 ወራት ውስጥ ለንግድ ስራዋ የሰላማዊት ዋነኛ የአጭር ጊዜ ግብ ምንድን ነው?

ሀ) ትልቅ የችርቻሮ ሱቅ መክፈትና ሰራተኞች መቅጠር፡፡  

ለ) 15 ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችን እና 100 ኪግ ከሰሎችን መሸጥ፣ 2 የማህበረሰብ ገለጻዎችን ማካሄድ፣ እና ከሽያጮች 10,000 ብር ገቢ ማግኘት፡፡

ሐ) ከፍተኛ የባንክ ብድር ማግኘት እና የምርት መስመሯን ማስፋት፡፡  

መ) በትርፍ ጊዜዋ ባህላዊ ምድጃዎችን በመሸጥ ላይ ብቻ ማተኮር፡፡

 

ትክክለኛው መልስ: ለ) 15 ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችን እና 100 ኪግ ከሰሎችን መሸጥ፣ 2 የማህበረሰብ ገለጻዎችን ማካሄድ፣ እና ከሽያጮች 10,000 ብር ገቢ ማግኘት፡፡

 

ጥያቄ 2: በሰላማዊት የገንዘብ ትንበያ መሰረት የዚህ ጊዜ ጠቅላላ የተገመቱ ወጪዎቿ ምን ያክል ናቸው?

ሀ) ብር 4,000

ለ) ብር 3,700

ሐ) ብር 3,210

መ) ብር 6,910

 

ትክክለኛው መልስ: መ) ብር 6,910

 

ጥያቄ 3: የሰላማዊት የመጀመሪያ ገንዘብ ለማግኘት የመጀመሪያው የገንዘብ ምንጯ ምንድን ነው?

ሀ) ከፍተኛ የባንክ ብድር  

ለ) ቁጠባና አነስተኛ የቤተሰብ ብድር  

ሐ) የመንግስት ዕርዳታዎች  

መ) የውጭ ሸሪኮች ኢንቨስትመንቶች

 

ትክክለኛው መልስ: ለ) ቁጠባና አነስተኛ የቤተሰብ ብድር

 

ከጉዳይ ጥናቱ የተወሰዱ ዋና ዋና ማስታወሻዎች:

  • ለአዳዲስ የንግድ ስራዎችም የSMART ግቦችን መወሰን እና መተንበይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና እድሎችን ለመለየት ይረዳል፡፡
  • የገንዘብ ፍሰት በተለይም በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ላይ አስፈላጊ ነው፡፡ አንድ የንግድ ድርጅት በወረቀት ላይ ትርፋማ ሊሆን ነገር ግን ገቢ የገንዘብ ፍሰቱ ከወጪ የገንዘብ ፍሰቱ ጋር ካልተጣጣመ ገንዘብ ሊያጥረው ይችላል፡፡
  • በእቅዶች ላይ መደበኛ ክትትልና ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

ይህ የጉዳይ ጥናት የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅትና የበጀት ምደባ የተግባር ትግበራን ይገልጻል፡፡ አሁን እንዴት ይህን በራስ መማሪያ ሞጁል ደረጃ በደረጃ እንደሚጠቀሙ እንመልከት፡፡

Scroll to Top