የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ትንተና ጠቅላላ ገቢዎችዎ ከጠቅላላ ወጪዎችዎ ጋር እኩል የሚሆኑበትን ነጥብ ለመወሰን የሚረዳዎ የገንዘብ ስሌት ነው፡፡ በተመሳሳይ አገላለጽ ይህ ማለት ትርፍም ሆነ ኪሳራ ሳይኖርብዎ ሁሉንም ወጪዎችዎን ለመሸፈን መሸጥ ያሉብዎ ምርቶች ብዛት (ወይም ማግኘት ያለብዎ የገቢ መጠን) ነው፡፡ አንዴ የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብን ካለፉ በኋላ በእያንዳንዱ ተጨማሪ ሽያጭ ትርፍ ማግኘት ይጀምራሉ፡፡
ሀ. የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ ቀመሮች
የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ በምርቶች፡ ይህ ምን ያክል ምርቶች መሸጥ እንዳለብዎ ይነግርዎታል፡፡
ቀመር: የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ (ምርቶች) = ቋሚ ወጪዎች / (የአንድ ምርት የመሸጫ ዋጋ -የአንድ ምርት ተለዋዋጭ ወጪ)
ተካፋዩ (የምርት የመሸጫ ዋጋ – የምርት የተለዋዋጭ ወጪ ዋጋ) በተጨማሪም በምርት የመዋጮ ህዳግ ተብሎ ይታወቃል፡፡
ለ. የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ በሽያጭ ገቢ:
ይህ ከሽያጮች ማግኘት ያለብዎትን ገቢ መጠን ይነግርዎታል፡፡
ቀመር: የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ (የሽያጭ ገቢ) = ቋሚ ወጪዎች / ((የአንድ ምርት የመሸጫ ዋጋ -የአንድ ምርት ተለዋዋጭ ወጪ) / የአንድ ምርት የመሸጫ ዋጋ)
ተካፋዩ የመዋጮ ሕዳግ ሬሺዮ ነው፡፡
በአማራጭነት አንዴ በምርት የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብዎን ካገኙ በኋላ የሚከተለውን ማስላት ይችላሉ፡
የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ (የሽያጭ ገቢ) = የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ (ምርቶች) * የአንድ ምርት የመሸጫ ዋጋ
ምሳሌ 1: የዮሀንስ – የሶላር የምግብ ማብሰያዎች
- ቋሚ ወጪዎች (ኤፍሲ) በወር:
- የቤተ ሙከራ ኪራይ: 3000 ብር
- የመሳሪያዎች ጥገና/የእርጅና ዋጋ መቀነስ: 500 ብር
- መሰረታዊ ገበያ: 500 ብር
ጠቅላላ ወርሀዊ ቋሚ ወጪዎች = 4000 ብር
- በሶላር የምግብ ማብሰያ:
- የመሸጫ ዋጋ (ኤስፒ) በምርት: 1950 ብር (ከዋጋ ትመና ሞጁል ምሳሌ የተወሰደ)
- ተለዋዋጭ ወጪ (ቪሲ) በምርት (ቁሳቁሶች፣ ቀጥተኛ የጉልበት ዋጋ): 1500 ብር (ከዋጋ ትመና ሞጁል ምሳሌ የተወሰደ)
- ስሌቶች:
- የመዋጮ ህዳግ በምርት = ኤስፒ – ቪሲ = 1950 ብር – 1500 ብር = 450 ብር
- የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ (ምርቶች) = ጠቅላላ ቋሚ ወጪዎች የመዋጮ ህዳግ በምርት
= 4000 ብር / 450 ብር/ምርት = 8.89 ምርቶች
ዮሀንስ ምርቶቹን በከፊል መሸጥ ስለማይችል የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ ላይ ለመድረስ በወር 9 የሶላር ማብሰያዎችን መሸጥ አለበት፡፡
የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ (የሽያጭ ገቢ) = የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ነጥብ (ምርቶች) * ኤስፒ
= 9 ምርቶች * 1950 ብር/ምርት = 17,550 ብር
ዮሀንስ ሁሉንም ቋሚ ወጪዎቹን ለመሸፈን በወር 17,550 ብር የሽያጭ ገቢ ማግኘት አለበት፡፡ እያንዳንዱ ከ9ኛው ምርት በኋላ የሚሸጥ ምርት (ለምሳሌ፡ 10ኛው ምርት) በቀጥታ 450 ብር የትርፍ መዋጮ ያደርጋል፡፡