መመሪያዎች: እያንዳንዱን መግለጫ ያንብቡ እና በግንዛቤዎ ወይም ችሎታዎ እርግጠኛ ከሆኑ በሳጥኑ ላይ በሀቀኝነት ምልክት ያድርጉ፡፡
ንድፈ ሀሳቦችን መገንዘብ:
- [ ] የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅትና የበጀት ምደባን በራሴ ቃላት መግለጽ እችላለሁ፡፡
- [ ] SMART የገንዘብ ግቦችን የመወሰን አስፈላጊነትን እረዳለሁ፡፡
- [ ] የገንዘብ ዓላማዎችን ከአጠቃላይ የንግድ ስራ ስትራቴጂ ጋር ማስማማት ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ማብራራት እችላለሁ፡፡
- [ ] የቋሚና ተለዋዋጭ ወጪዎችን ልዩነት አውቃለሁ፡፡
- [ ] የገንዘብ ፍሰት ትንበያ ለምን ከትርፍ/ኪሳራ በጀት ጋር እንደሚለይ እና ለምን እንደሚያስፈልግ እረዳለሁ፡፡
- [ ] የልዩነት ትንተና እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ማብራራት እችላለሁ፡፡
ክህሎቶችን መተግበር:
- [ ] ለንግድ ስራ SMART የገንዘብ ግብ ማዘጋጀት እችላለሁ፡፡
- [ ] የገቢና ወጪ ትንበያ የተለመዱ ዘዴዎችን መዘርዘር እችላለሁ፡፡
- [ ] መሰረታዊ የገቢና ወጪ በጀት ቴምፕሌትን መሙላት እችላለሁ፡፡
- [ ] መሰረታዊ የገንዘብ ፍሰት ትንበያ ቴምፕሌትን መሙላት እችላለሁ፡፡
- [ ] በቀላል የጉዳይ ጥናት ላይ ተመስርቼ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የገንዘብ ችግሮችን መለየት እችላለሁ፡፡.
ዋና ዋና የትምህርት ነጥቦች
የሚከተሉት ከዚህ ትምህርት የተወሰዱ ዋና ዋና ማስታወሻዎች ናቸው፡
- የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅት ስትራቴጂያዊ ፍኖተ ካርታዎ ሲሆን የበጀት ምደባ ዝርዝር፣ የአሀዝ የድርጊት ዕቅድዎ ነው፡፡
- የSMART ግቦች (ዓላማ ተኮር፣ ሊለካ የሚችል፣ ሊሳካ የሚችል፣ ተገቢ፣ በጊዜ የተገደበ) ለውጤታማ የገንዘብ ዒለማዎች ወሳን ነው፡፡
- የገንዘብ ዓላማዎችዎ ለዘላቂ እድገት ከአጠቃላይ የንግድ ስራ ስትራቴጂዎ ጋር መስማማት አለባቸው፡፡
- ትንበያ (ገቢ፣ ወጪዎች፣ የገንዘብ ፍሰት) ለወደፊት ለመዘጋጀት ብልህ ግምት ማስቀመጥ ነው፡፡
- በጀት ሀብቶችን እንዲመድቡና አፈጻጸማቸውን እንዲቆጣጠሩ ይረዳዎታል፡፡
- የገንዘብ ፍሰት ትንበያ መጣራትን ለማስተዳደር እና ሁልጊዜም በቂ ገንዘብ ያልዎ መሆኑን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡
ገንዘብን በማስተዳደር ረገድ ንቁ መሆን የረጅም ጊዜ የንግድ ስራ ስኬትዎን እድሎች ያሳድጋል፡፡.