Course Content
የገንዘብ/ፋይናንስ አስተዳደር

ይህ ትምህርት ሲጠናቀቅ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ:

  1. የSMART መስፈርትን በመጠቀም ግልጽ የአጭር እና የረጅም ጊዜ የገንዘብ ግቦችን ማዘጋጀት፡፡
  2. ለዘላቂ እድገት የገንዘብ ዓላማዎችን ከአጠቃላይ የንግድ ስራ ስትራቴጂ ጋር የማስማማት አስፈላጊነትን ማብራራት፡፡
  3. ከንግድ ስራ ፍላጎቶች ጋር የሚስማማ መሰረታዊ የገንዘብ ዕቅድ በማዘጋጀት ውስጥ የሚካተቱ ዋና ዋና ደረጃዎችን መግለጽ፡፡
  4. ለስራዎችና የገንዘብ ፍሰት ትንበያዎች ድጋፍ የሚያደርግ የተጨባጭና የተግባር የንግድ ስራ በጀት ክፍሎችን መረዳት፡፡

 

ይህን የትምህርት መርጃ የመማር ዓላማ:

የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅትና የበጀት ምደባ ስለ ቁጥሮች ማለት ሳይሆን ለንግድ ስራዎ አቅጣጫ ስለመስጠትና መቆጣጠር የተመለኩ ናቸው፡፡ ይህን የትምህርት መርጃ መማር የሚከተሉትን ለማድረግ ያስችልዎታል፡-

  • የንግድ ስራዎን በማስተዳደር ረገድ ምላሽ ሰጪ ከመሆን ይልቅ ንቁ እንዲሆኑ፡፡
  • ስለ ሀብት ምደባ (ገንዘብ ምን ላይ እንደሚከፈል) በመረጃ የተደገፉ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ፡፡
  • የንግድ ስራ አፈጻጸምዎን ከግቦቹ አንጻር እንዲቆጣጠሩ እና መሻሻል ያለባቸውን ቦታዎች እንዲለዩ፡፡
  • ለወደፊት የገንዘብ ፍላጎቶች እና እድሎች እንዲዘጋጁ (ለምሳሌ፡ ማስፋፋት፣ አዲስ ምርት መጀመር)፡፡
  • የረጅም ጊዜ የንግድ ስራ ስኬትና ዘላቂነት እድሎችን እንዲያሳድጉ፡፡
  • የገንዘብ ዕቅዶችዎን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለባለድርሻ አካላት (ለምሳሌ፡ ባለሀብቶች፣ አበዳሪዎች፣ የቡድን አባላት) እንዲገልጹ፡፡

 

ዋና ዋና የትምህርት ነጥቦች (ወሳኝ ክፍሎች/ደረጃዎች):

  1. ግብ መወሰን (አቅጣጫ መስጠት): የንግድ ስራው በገንዘብ ረገድ ምን ማሳካት እንደሚፈልግ በግልጽ መግለጽ፡፡ ያለ ግቦች የዕቅድ ዝግጅት ዓላማ ቢስ ነው፡፡
  2. ስትራቴጂያዊ ማስማማት (ተያያዥነትን ማረጋገጥ): የገንዘብ ግቦቹ የተዘጋጁት በባዶ ሳይሆን በቀጥታ አጠቃላይ የንግድ ስራ ስትራቴጂውን (ለምሳሌ፡ እድገት፣ ወደ ገበያ ዘልቆ መግባት፣ ፈጠራ) በቀጥታ በሚደግፍ መልኩ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
  3. የሀብት ምደባ (የገንዘብ አጠቃቀምን ማሳደግ): ውሱን የገንዘብ ሀብቶችን (ጥሬ ገንዘብ፣ ብድር) የተወሰኑትን ግቦች ለማሳካት እንዴት በጥሩ ሁኔታ እንደሚጠቀሙ መወሰን፡፡ በጀት ለዚህ የመጀመሪያው መሳሪያ ነው፡፡
  4. ትንበያ (ስለ ወደፊት መገመት): ስለ የወደፊት ገቢዎች፣ ወጪዎች እና የገንዘብ ፍሰቶች በሳል ግምቶችን ማዘጋጀት፡፡ ይህ ተጨባጭ እቅዶችና በጀቶችን ለማዘጋጀት ወሳኝ ነው፡፡
  5. በጀት ማዘጋጀት (የድርጊት ዕቅድ): የሚጠበቀውን ገቢ እና ወጪ የሚገልጽ ዝርዝር የገንዘብ ፍኖተ ካርታ (በጀት) ማዘጋጀት፡፡
  6. የገንዘብ ፍሰት አስተዳደር (መጣራትን ማስቀጠል): የበጀት ምደባ ወሳኙ ክፍል የንግድ ስራው ሁልጊዜም ግዴታዎቹን ለማሟላት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ የገንዘብ ፍሰቱን መተንበይ ነው፡፡
Scroll to Top