ይህን ትምህርት ሲያጠናቅቁ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡
- የፋይናንስ አስተዳደርን ይግለጹ እና የንግድ ሥራ ዘላቂነት እና እድገትን በማረጋገጥ ረገድ ያለውን ወሳኝ ሚና ያብራሩ፡፡
- ዋና ዋና የፋይናንስ ንድፈ ሀሳቦችን እና ቃላትን ይለዩ እና ይግለጹ፡፡
ይህን የትምህርት መርጃ የመማር ዓላማ:
እርስዎ ባለቤትም ይሁኑ ሥራ አስኪያጅ ወይም ሰራተኛ የፋይናንስ አስተዳደርን መረዳት በንግድ ስራ ውስጥ ለሚሳተፍ ለየትኛውም መሰረታዊ ነው፡፡ ይህ ዕውቀት የሚከተሉትን የሚያደርጉበት አቅም ይፈጥርልዎታል፡
- ለንግድ ሥራዎ የፋይናንስ ጤናማነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በመረጃ የተደገፉ ውሳኔዎችን ማሳለፍ፡፡
- የንግድ ስራው እንዴት በትክክል እየተከናወነ እንደሆነና በገንዘብ ረገድ ምን አቋም ላይ እንደሚገኝ መረዳት፡፡
- ስለ የፋይናንስ ጉዳዮች በተመለከተ የበለጠ ውጤታማ ግንኙነት ማድረግ፡፡
- ለንግድ ስራው ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ እና የረጅም ጊዜ ስኬት አስተዋጽኦ ማድረግ፡፡
- የንግድ ሥራ ውድቀትን ሊያስከትሉ የሚችሉ የተለመዱ የፋይናንስ ወጥመዶችን ያስወግዱ፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች (ወሳኝ ክፍሎች/ደረጃዎች):
- የፋይናንስ ጤናማነት ምዘና: ይህ የንግድ ስራው በየትኛውም ጊዜ በገንዘብ አቋም ረገድ የት ላይ እንዳለ ማቅን ይመለከታል፡፡ ምዘናው የንግድ ስራውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ለመረዳት በመደበኛነት የፋይናንስ መረጃን መገምገምን ይይዛል፡፡ ይህ አንድ ዶክተር ለታካሚው ምርመራ /ቼክ አፕ/ እንደሚያደርገው አይነት ነው፡፡
- የፋይናንስ ውሳኔ አሰጣጥ: የፋይናንስ አስተዳደር ወሳኝ የንግድ ሥራ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የሚያገለግል መረጃ እና ማዕቀፍ ይሰጣል፡፡ ይህም የሚከተሉትን ያጠቃልላል:
- የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች: ምን ንብረቶች መገዛት አለባቸው? (ለምሳሌ፡ አዲስ መሳሪያዎች፣ ቴክኖሎጂዎች)፡፡
- የገንዘብ ምንጭ ውሳኔዎች: ገንዘብ ከየት ማግኘት ይቻላል? (ለምሳሌ፡ ብድሮች፣ የባለቤቱ ካፒታል፣ ባለሀብቶች)፡፡
- የስራ እንቅስቃሴ ውሳኔዎች: የዕለት ከእለት ፋይናንስን ማስተዳደር የሚቻለው እንዴት ነው? (ለምሳሌ፡ የዋጋ ትመና ስትራቴጂዎች፣ የንብረት አስተዳደር፣ ወጪዎችን መቆጣጠር)፡፡
- የወደፊት ዕቅድ ዝግጅት (የገንዘብ ዕቅድ ዝግጅት): ይህ የፋይናንስ ግቦችን መወሰንን እና ግቦቹን ለማሳካት ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀትን ይይዛል፡፡ ዕቅዱ የወደፊት ፍላጎቶችና ዕድሎችን በመገመት የንግድ ሥራው ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
- ወደ ገንዘብ መቀየርን ማረጋገጥ (የገንዘብ ፍሰት አስተዳደር): የንግድ ስራው እንደ የአገልግሎት ክፍያዎችን እና ደመወዝ መክፈል የመሳሰሉ የአጭር ጊዜ ግዴታዎችን ለማሟላት በእጁ ላይ በቂ ገንዘብ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፡፡ ትርፋማነት አስፈላጊ ቢሆንም ነገር ግን የእለት ከእለት ህልውናን ለማስቀጠል “ገንዘብ ወሳኝ ነው”፡፡