Course Content
የገንዘብ/ፋይናንስ አስተዳደር

መመሪያዎች: የSMART መስፈርትን በመጠቀም የገንዘብ ግቦችዎን ለመግለጽ እያንዳንዱን ክፍል ይሙሉ፡፡

መመሪያ ለማግኘት የቀረቡትን ምሳሌዎች ይመልከቱ፡፡

የSMART የገንዘብ ግብ ቴምፕሌት

የንግድ ድርጅቴ ስም: ________________________________________________

ቀን: ________________________________________________

  1. ዓላማ ተኮር:

በትክክል ማሳካት የሚፈልጉት ምንድን ነው? (በጣም ግልጽና አጭር ያድርጉ)

ምሳሌ: “በዓመት 1,000 የሶላር የምግብ ማብሰያዎችን መሸጥ፡፡”

የእርስዎ መልስ:________________________________________________

  1. ሊለካ የሚችል:

ስኬትዎን የሚለኩት እንዴት ነው? (የአሀዝ መለኪያዎች ወይም ቁጥሮችን ይጠቀሙ!)

ምሳሌ: “ከሶላር የምግብ ማብሰያዎቹ ሽያጭ 20% የተጣራ ትርፍ ማግኘት፡፡”

የእርስዎ መልስ:________________________________________________

 

  1. ሊሳካ የሚችል:

ይህ ግብ ከወቅታዊ ሁኔታዎ አንጻር ተጨባጭ ነው? በአሁኑ ወቅት ምን ሀብቶች (ገንዘብ፣ የሰው ሀይል፣ መሳሪያዎች፣ ክህሎቶች) አሉዎ ወይም መግዛት ያስፈልግዎታል? ምን ችግሮች ወይም እንቅፋቶች ሊያጋጥሙዎ ይችላሉ፣ እንዴትስ ሊፈቷቸው ይችላሉ?

የእርስዎ መልስ:________________________________________________

  1. ተገቢ:

ይህ ግብ ከሰፊ የንግድ ስራ ራዕይዎ፣ ተልዕኮዎ ወይም የረጅም ጊዜ ዓላማዎችዎ ጋር የሚስማማው ወይም ድጋፍ የሚያደርገው እንዴት ነው? ይህ ግብ ለአጠቃላይ ስኬትዎ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የእርስዎ መልስ:________________________________________________

  1. በጊዜ የተገደበ:

ይህን ግብ በትክክል የሚያሳኩት መቼ ነው? (ግልጽ፣ ተጨባጭ የጊዜ ገደብ ያስቀምጡ)

ምሳሌ: “ከአሁን ጀምሮ በ3 ዓመታት ውስጥ፡፡”

የእርስዎ መልስ:________________________________________________

የተጠናቀቀ የSMART ግብዎ:

(ሁሉንም በአንድ ወይም ሁለት ግልጽ፣ አጭር አረፍተ ነገሮች ያጠቃሉ)፡፡

“በጊዜ [የተገደበ ጊዜዎ] በምክንያት [ሊሳኩ የሚችሉና ተገቢ ማረጋገጫዎች] በማድረግ [ሊለካ የሚችል መስፈርትዎ] አሳካለሁ [ልዩ ግብዎ]፡፡”

የእርስዎ መልስ:________________________________________________

ምሳሌ:  “በ3 ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ 1,000 የሶላር የምግብ ማብሰያዎችን በመሸጥና 20% የተጣራ ትርፍ በማግኘት ቤተሙከራዬን እና ቴክኒሺያኔን አጠናክራለሁ እንዲሁም ተመጣጣኝ ንጹህ ኢነርጂ በማቅረብ መሪ ለመሆን ራዕዬ ድጋፍ እንዲያደርግልኝ የአካባቢ የገንዘብ ምንጮችን አጠናለሁ፡፡”

 

ዋና ዋና መለኪያዎችና የወጪ ትንበያ

ወደ ግቦችዎ እየቀረቡ መሆኑን የሚያመለክቱ ዋና ዋና የማረጋገጫ ነጥቦችዎን ወይም ዋና ዋና ስኬቶችዎን ለይተው ይወቁ፡፡ ለእያንዳንዱ መለኪያ ተያያዥ ወጪዎችን ያስሉ፡፡

መለኪያ 1: ________________________________________________ (ትኩረት የተደረገበት ቀን: ______)

 

ተያያዥ ወጪ

ምሳሌ: የሰላማዊት የመጀመሪያ መለኪያ በመጀመሪያው ዓመት ውስጥ የ500 የሶላር የምግብ ማብሰያዎች ሽያጭን ማሳካት ነው፡፡

ተያያዥ ወጪዎች/ ትንበያ፡ ጥሬ ዕቃዎች፣ የሽያጭ ኮሚሽን፣ የገበያ ዘመቻ ወጪ፡፡

መለኪያ 2: ________________________________________________ (ትኩረት የተደረገበት ቀን: ______)

ተያያዥ ወጪዎች/ትንበያ

Scroll to Top