Course Content
የገንዘብ/ፋይናንስ አስተዳደር

ጥያቄ 1: የንግድ ስራዬ አዲስ ከሆነና ለትንበያ ታሪካዊ ዳታ ከሌለኝስ?

መልስ 1: አዳዲስ የንግድ ድርጅቶች በገበያ ጥናት (ፍላጎትን፣ የተፎካካሪ ዋጋን መረዳት)፣ የኢንዱስትሪ መለኪያዎች (ከተመሳሳይ የንግድ ድርጅቶች የተወሰደ ዳታ) እና በባለሙያ አስተያየት (ልምድ ያላቸው ስራ ፈጣሪዎችን ማናገር) ላይ በእጅጉ ይመሰረታሉ፡፡ በጥብቅ ግምቶች ይጀምሩ እና ትክክለኛ ዳታ እያገኙ ሲሄዱ ያስተካክሉ፡፡

 

ጥያቄ 2: በጀቴ ትርፍ ያሳያል፣ ነገር ግን የገንዘብ እጥረት አጋጥሞኛል፡፡ ለምን?

መልስ 2: ይህ የተለመደ ጉዳይ ነው! ትርፍ (ከገቢ መግለጫዎ/በጀትዎ የሚገኝ) ገቢዎች በጊዜ ሂደት ከወጪዎች መብለጣቸውን ያሳያል፡፡ የዱቤ ሽያጭ ሸጠው (ገቢው ተገኝቷል ነገር ግን ገንዘቡ እስካሁን አልተሰበሰበም) ወይም ከፍተኛ የንብረት ግዢዎች ፈጽመው (ወጪዎቹ ሙሉ በሙሉ አልተረጋገጡም ነገር ግን ገንዘቡ ተከፍሏል) ሊሆን ይችላል፡፡ ሁልጊዜም የገንዘብ ፍሰት ትንበያዎን ከበጀትዎ ጋር አብረው ይከታተሉ፡፡

 

ጥያቄ 3: የገንዘብ ዕቅዴን እና በጀቴን በየ ምን ያክል ጊዜ መገምገም እና ማሻሻል አለብኝ?

መልስ 3: በትክክል የተገኙትን ውጤቶች ከታቀዱት አሀዞች ጋር ለማነጻጸር (የልዩነት ትንተና) በጀትዎን ቢያንስ በየወሩ ወይም በየ ዕሩብ ዓመቱ ቢገመግሙ ይመከራል፡፡ አጠቃላይ የገንዘብ ዕቅድዎን በየዓመቱ ወይም በንግድ ስራዎ ላይ መሰረታዊ ለውጦች ሲፈጠሩ (ለምሳሌ፡ አዲስ ምርት መጀመር፣ ዋና ዋና ገበያዎችን መቀየር) መገምገም አለብዎ፡፡

 

ጥያቄ 4: ትክክለኛ ውጤቶቼ ከበጀቴ እጅግ የተለዩ ቢሆኑስ?

መልስ 4: አይሸበሩ! ይህ በተለይም ለአዳዲስ የንግድ ስራዎች የተለመደ ነው፡፡ ልዩነቱ ለምን እንደተፈጠረ ለመለየት የልዩነት ትንተናን ይጠቀሙ፡፡ ሽያጮች አነስተኛ የሆኑት ያልተጠበቀ ውድድር በመኖሩ ምክንያት ነው? ወጪዎች በአቅራቢ ዋጋ መጨመር ምክንያት ከፍተኛ ሆነዋል? የወደፊት ትንበያዎችዎን እና በጀትዎን ለማስተካከል እና የስራ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ይህን ትንተና ይጠቀሙ፡፡

 

ጥያቄ 5: ተለዋዋጭ ወጪዎቼን ለመገመት እየተቸገርኩ ነው፡፡ ማንኛውም ጠቃሚ ምክሮች አሏችሁ?

መልስ 5: አንድ ምርት ከማምረት ወይም አንድ አገልግሎት ከማቅረብ ጋር ተያያዥ በሆኑት ቀጥተኛ ወጪዎችዎ ላይ ያተኩሩ፡፡ ለምሳሌ፡ ለሶላር የምግብ ማብሰያ ይህ ለአንድ የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶች እና ማብሰያውን በመገጣጠም ላይ ለሚሳተፍ ሰራተኛ የሚከፈል ወጪ ነው፡፡ ሁሉንም የአንድ ምርት ወጪዎች ለመለየት የምርት ሂደቱን ከፋፍለው ያስሉ፡፡

Scroll to Top