የአመራርና የባለድርሻ አካል ተሳትፎ

ባለድርሻ አካል: በንግድ ስራዎ ድርጊቶች ላይ ተጽእኖ ሊፈጥር ወይም ሊፈጠርበት የሚችል ማንኛውም ሰው፣ ቡድን ወይም ድርጅት ነው፡፡

ተቆጣጣሪ አካል: በተወሰነ ቦታ ውስጥ ሕጎችና ደንቦችን (ለምሳሌ፡ የአካባቢ ጥበቃ፣ የንግድ ፍቃድ አሰጣጥ) የማዘጋጀት እና የማስፈጸም ኃላፊነት የተሰጠው የመንግስት ድርጅት ነው፡፡

የባለድርሻ አካል ተሳትፎ: ችግሮቻቸውን ለመረዳት እና አዎንታዎ ግንኙነቶችን ለመመስረት ከባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት የማድረግ ሂደት ነው፡፡

ሕግ ማክበር: ትእዛዝ፣ ደረጃ ወይም ሕግ የማክበር ድርጊት ነው፡፡

 

ዋና ዋና የመንግስት ባለድርሻ አካላት:

  1. የአካባቢ/ወረዳ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ: ለንግድ ምዝገባና ፍቃድ አሰጣጥ፡፡
  2. የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን (ERCA): ለግብር ምዝገባ (የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር)፡፡
  3. የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን (EPA): የንግድ ስራዎ የአካባቢ ተጽእኖ ሊፈጥር የሚችል ማምረት ወይም ቆሻሻን የሚይዝ ከሆነ፡፡
  4. የአካባቢ ቀበሌ አስተዳደር: ለጠቅላላ አስተዳደራዊ ድጋፍ እና የማህበረሰብ ግንኙነቶች፡፡

 

ምሳሌ: ሰላማዊት የንግድ ስራ ፍቃዷን ታገኛለች

ሰላማዊት ሀዋሳ ውስጥ ሱቋን ከመክፈቷ በፊት የንግድ ፍቃድ እንደሚያስፈልጋት ታውቃለች፡፡

ባለድርሻ አካላት መለየት: የከተማውን የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ማሰተፍ ያለባት ዋና ተቆጣጣሪ አካል እንደሆነ ትለያለች፡፡

  • ንቁ ጥናት፡ በአካል ከመሄድ ይልቅ ለቢሯቸው ደውላ ምን ሰነዶች እንደሚያስፈልጓት ትጠይቃለች፡፡ መታወቂያ፣ የሱቋ የኪራይ ስምምነት ማስረጃ እና ሁለት የፓስፖርት ፎቶዎች እንደሚያስፈልጓት ታውቃለች፡፡
  • ዝግጅት: ሁሉንም ሰነዶቿን በንጹህ ማህደር ውስጥ ታዘጋጃለች፡፡ ስለ ንግድ ስራዋ እንዴት በግልጽ እና በአጭርሱ እንደምታብራራ ታስባለች፡ “ማህበረሰባችንን ከቤት ውስጥ የሚወጣውን ጭስ ለመቀነስ እና ለከሰል የሚያወጣውን ወጪ እንዲቆጥብ ለመርዳት የተረጋገጡ ንጹህ የማብሰያ ምድጃዎችና ባዮፊዩል የምሸጥበት ሱቅ እየከፈትኩ ነው፡፡”
  • ሙያዊ ተሳትፎ: ወደ ቢሮ ስትሄድ ሙያዊ አለባበስ ትለብሳለች፡፡ መጠበቅ ቢኖርባት እንኳ ትሁትና ታጋሽ ነች፡፡ ከኃላፊ ጋር በምትነጋገርበት ወቅት ስለ ንግድ ስራዋ በአጭሩ እና በአክብሮት ታብራራለች፡፡ ኃላፊው ለመርዳት ዝግጁ በመሆኑ የምዝገባ ሂደቷን ሳትዘጋጅ ብትመጣ ሊሆን ከሚችለው ይልቅ የበለጠ በተሳለጠ ሁኔታ ታጠናቅቃለች፡፡
Scroll to Top