የአመራርና የባለድርሻ አካል ተሳትፎ

የጉዳይ ጥናት: ዮሀንስ ድጋፍ ይፈልጋል

የዮሀንስ የሶላር ማብሰያ የንግድ ስራ በአዲስ አበባ ውስጥ የተወሰነ መሰረት እየያዘ ነው፡፡ በፈጠራና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስለሚመራ ለአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ጀማሪዎች አነስተኛ እርዳታዎችና የቴክኒክ ድጋፍ ስለሚያቀርብ የመንግስት ኢኒሺየቲቭ ይሰማል፡፡ ለማመልከት መደበኛ ማመልከቻ ማስገባት እና ከዚያም የንግድ ስራ እቅዱን ለኃላፊዎች ጉባኤ ማቅረብ አለበት፡፡ ዮሀንስ መሀንዲስ እና ስለ ምርቱ ለማብራራት ምቾት የሚሰማው ቢሆንም ለመንግስት ኃላፊዎች ሀሳቡን ለማቅረብ ሀፍረት ይሰማዋል፡፡ በአግባቡ ስላልተደራጀ የንግድ ስራ ገንዘቡ ከባድ ጥያቄዎችን ቢጠይቁኝስ ወይም እንደሱ አይነት ወጣት ስራ ፈጣሪን በቁምነገር ባይቀበሉስ የሚል ፍርሀት ይፈጠርበታል፡፡

 

የውይይት ጥያቄዎች/ፈተናዎች:

  1. በዚህ ኩነት ላይ ዮሀንስ ሊያሳምናቸው የሚገቡ ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት እነ ማን ናቸው? እነዚህ በባለድርሻ አካላት ማትሪክሱ ውስጥ የቱ ጋር መግባት አለባቸው?
    ሀ. ደንበኞቹ – ማርካት፡፡ ለ. የሚኒስቴር ጉባዔ እና የመንግስት ኃላፊዎች – ዋና ዋና ተዋናዮች፡፡ ሐ. ሌሎች ስራ ፈጣሪዎች – ክትትል
    መ. የዩኒቨርሲቲ የክፍል ጓደኞች – መረጃ ማግኘት

ትክክለኛው መልስ: ለ – የሚኒስቴር ጉባዔ እና የመንግስት ኃላፊዎች ከፍተኛ ተጽእኖ እና ከፍተኛ ፍላጎት፡፡ ጉባኤው እና የመንግስት ኃላፊዎች በባለድርሻ አካል ማትሪክስ ውስጥ “ዋና ዋና ተዋናዮች” ስለሆኑ በቅርበትና ሙያዊነት እንዲሳተፉ መደረግ አለባቸው፡፡

  1. ዮሀንስ ማመልከቻውን ከማስገባቱ በፊት ማዘጋጀት ያለበት ሶስት አስፈላጊ ነገሮች ምንድን ናቸው?
    ሀ. የምርቱን አጭር ቪዲዮ፣ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ማስፈንጠሪያዎች እና የተፎካካሪዎቹ ዝርዝር
    ለ. ጠንካራ የንግድ ስራ እቅድ፣ መሰረታዊ የፋይናንስ መግለጫዎች እና እንዴት ምርቱ የአረንጓዴ ፈጠራውን እንደሚደግፍ፡፡ ሐ. የትምህርት ማስረጃ፣ የግል ታሪክ፣ እና የድጋፍ ደብዳቤ፡፡ መ. የምርቱን ምሳሌ እና መዘግየትን ለማስቀረት ቀሪውን መዝለል፡፡

 ትክክለኛው መልስ: ለ – እድሎቹን ለማሳደግ ዮሀንስ የንግድ ስራ እቅድ ማዘጋጀት፣ የገንዘብ አጠቃላይ መረጃ (መሰረታዊም ቢሆን) እና ከመንግስት የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ግቦች ጋር ተያያዥነት ያለው ግልጽ የውጤት መግለጫ፡፡

  1. በገለጻው ወቅት ዮሀንስ እንደ ሙያተኛና ተአማኒ ለመታየት ምን አይነት ቋንቋ አቀራረብ መከተል አለበት?
    ሀ. ተያያዥነትና ወጣትነት እንዳለው ለማሳየት ተራ፣ ዘዬ – ከባድ ቋንቋ መጠቀም፡፡ ለ. ኃላፊዎቹን ለማሳመን የምህንድስና ሙያዊ ቃላትን በመጠቀም በቴክኒክ ቋንቋ መናገር፡፡ ሐ. ግልጽ፣ በራስ መተማመን ያለበትና የአክብሮት ቋንቋ በመጠቀም የመማር ጉጉትና ዝግጁነት እንዳለው ማሳየት፡፡ መ. ገለጻውን አጭር ማድረግ እና ጥያቄዎችን በዝርዝር መመለስን ማስቀረት፡፡

ትክክለኛው መልስ: ሐ – ዮሀንስ በግልጽና በራስ መተማመን ድምጽ ለማውራት፣ አክብሮት ለመስጠት፣ ራዕይና ቁርጠኝነቱን ለመግለጽ እና ለመማርና ድጋፍ ዝግጁ የሆነ ሰው እንደሆነ ለማሳየት ማለም አለበት፡፡

Scroll to Top