የአመራርና የባለድርሻ አካል ተሳትፎ

የጉዳይ ጥናት: የሰላማዊት ሱቅ ቡድን ያስፈልገዋል

ሰላማዊት አነስተኛ ብድር አግኝታ ሀዋሳ ውስጥ ንጹህ የማብሰያ ምድጃ መሸጫ ሱቅ ለመክፈት ተዘጋጅታለች፡፡ ከማህበረሰቧ ውስጥ ሁለት ሴቶችን ትቀጥራለች፡፡ አንደኛዋ (ሀና ብለን እንጥራት) በአነስተኛ የችርቻሮ ሱቅ ላይ ልምድ ያላት ሲሆን ሌላኛዋ (ሳራ ብለን እንጥራት) በጣም የተደራጀች በመሆኗ ትታወቃለች፡፡ አሁን ሰላማዊት መሪያቸው ትሆናለች ነገር ግን ከዚህ በፊት ማንንም ሰው አስተዳድራ አታውቅም፡፡ ከመጀመሪያ ሳምንት ሙከራ (ምስረታ) በኋላ ችግሮች መፈጠር ይጀምራሉ፡፡ ሀና ከደንበኞች ጋር ጥሩ ግንኙነት ቢኖራትም የተዋከበች በመሆኗ ሽያጮችን መመዝገብ ትረሳለች፡፡ ሳራ በንብረት ቆጠራ ላይ በአግባቡ የተደራጀች ብትሆንም ነገር ግን አይናፋርና ደንበኞችን ለማናገር የምትፈራ ነች፡፡፡ ሁለቱ አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ መበሳጨት ይጀምራሉ፣ ከዚያም በየግላቸው ለሰላማዊት ቅሬታቸውን ማቅረብ ይጀምራሉ፡፡ ቡድኑ በግልጽ ያለው በግጭት ደረጃ ላይ ነው፡፡

 

የውይይት ጥያቄዎች/ፈተናዎች:

  1. እንደ የቡድን መሪ ሰላማዊት አሁን ማድረግ ያለባት እጅግ አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው?
    ሀ. ሽያጭ የሚያመጣው የደንበኞች አገልግሎት ስለሆነ ለሀና መወገን፡፡
    ለ. በአግባቡ መደራጀትና መመዝገብ አስፈላጊ ስለሆነ ለሳራ መወገን፡፡
    ሐ. ገለልተኛ መሆን፣ ሁለቱንም በንቃት ማዳመጥ እና ችግሮቹን በጋራ ለመፍታት ቡድኑን መሰብሰብ፡፡
    መ. ግጭቱን ችላ ማለት እና ለቡድኑ በራሱ እንዲፈታው መተው፡፡

ትክክለኛው መልስ: ሐ – ሰላማዊት ገለልተኛ መሆን፣ ሁለቱንም ወገኖች በንቃት ማዳመጥ እና ቡድኑ አለመግባባቱን ገንቢ በሆነ መልኩ እንዲፈታ ለማስቻል ውይይት ማመቻቸት አለባት፡፡

Scroll to Top