የአመራርና የባለድርሻ አካል ተሳትፎ

የድርድር ማቀጃ

ዓላማ: ይህ ሌላኛውን ወገን ከማናገርዎ በፊት የሚሞሉት አንድ ገጽ ወርክሺት ነው፡፡ ወርክሺቱ ሀሳቦችዎን በማደራጀት በድርድር ወቅት ጫና ሲያጋጥም ግቦችዎን ወይም ገደቦችዎን አለመርሳትዎን ያረጋግጣል፡፡

እንዴት እንደሚጠቀሙት: የትኛውንም አስፈላጊ ድርድር ከማድረግዎ በፊት ይህን ማቀጃ ለመሙላት 30 ደቂቃዎች ይውሰዱ፡፡ ዋና ዋና እርምጃዎች የሚከተሉትን ማካተት አለባቸው:

  • ተመራጭ ውጤቴ (ምን እንደምፈልግ)
  • መሄጃ ነጥቤ (ዝቅተኛው የምቀበለው)
  • BATNAዬ (ድርድር ከሌለ ምን እንደማደርግ)
  • የእነሱ ፍላጎቶች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ (ምን እና ለምን እንደሚፈልጉ የማስበው) ሊሆን የሚችል የእነሱ BATNA
  • ላቀርብ የሚችላቸው ሊሳኩ የሚችሉ የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጉ አማራጮች

 

የአቅራቢ ስምምነት ማረጋገጫ ዝርዝር

ዓላማ: ይህ የማረጋገጫ ዝርዝር ከአቅራቢ ጋር ስምምነት በሚያጠናቅቁበት ወቅት በዋና ዋና ዝርዝሮች ላይ መደራደርዎን እና መስማማትዎን አለመስርሳትዎን ያረጋግጣል፡፡ በዋጋ ላይ በቃል መስማማት በቂ አይደለም፡፡

እንዴት እንደሚጠቀሙት: ይህን በድርድር ወቅት ወይም ውል ከመፈራረምዎ በፊት እንደ መመሪያ ይጠቀሙበት፡፡ ትክክለኛ መዘርዝሮችና የጥራት ደረጃዎች:

  • ምርት/አገልግሎት: ትክክለኛ መዘርዝሮችና የጥራት ደረጃዎች
  • ዋጋ: የአንድ ዕቃ ዋጋ እና የትኛውም የቅናሽ ሁኔታዎች
  • የክፍያ ስምምነቶች: ክፍያ የሚከፈለው መቼ ነው? (ምሳ፡ በማስረከብ ወቅት፣ ከ30 ቀናት በኋላ)፡፡
  • ርክክብ: እቃዎቹ የሚረከቡት መቼ፣ የት እና እንዴት ነው? ትራንስፖርት የሚከፍለው ማን ነው?
  • የጥራት ጉዳዮች: ምርቶቹ ግድፈት ያለባቸው ቢሆኑ ምን ይሆናል? (ለምሳሌ፡ መመለስ፣ መቀየር)፡፡
  • የውል ርዝመት: ስምምነቱ ምን ያክል ጊዜ ይቆያል?
Scroll to Top